Get Mystery Box with random crypto!

​​ቡሄበሉ ቡሄ በሉ (፪) - - ሆ ልጆች ሁሉ - - ሆ የኛማ ጌታ - - ሆ የዓለም ፈጣ | የመዝሙር ደብተር™

​​ቡሄበሉ

ቡሄ በሉ (፪) - - ሆ ልጆች ሁሉ - - ሆ
የኛማ ጌታ - - ሆ የዓለም ፈጣሪ - - ሆ
የሰላም አምላክ - -ሆ ትሁት መሀሪ -ሆ
በደብረ ታቦር - - ሆ የተገለጠው - ሆ
ፊቱ እንደ ፀሐይ - ሆ በርቶ የታየው -ሆ
ልብሱ እንደብርሃን -ሆ ያንፀባረቀው -ሆ

ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና(፪)
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን(፪)

ያዕቆብ ዮሐንስ-ሆ እንዲሁም ጴጥሮስ-ሆ
አምላክን አዩት - - ሆ ሙሴ ኤልያስ - ሆ
አባቱም አለ - - ሆ ልጄን ስሙት - - ሆ
ቃሌ ነውና - - ሆ የወለድኩት - - ሆ

አዝ======

ታቦር አርሞንኤም-ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ
ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው- ሆ
ሰላም ሰላም - - ሆ የታቦር ተራራ - - ሆ
ብርሀነ መለኮት - ሆ ባንቺ ላይ አበራ -ሆ

አዝ======

ሙሉ መዝሙሩን ለማግኘት ከስር ይጫኑ

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

<< ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል >>
መዝ፹፰፥፲፪

እንኳን ለደብረ ታቦር / ቡሄ
በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።