Get Mystery Box with random crypto!

ከመልካም ወጣትነት ወደ ለየለት ዕብደት ከተድላ ደስታ ወደ ልቅሶና ዋይታ መልካም የነበረው ወጣት በ | ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለመናፍቃንና ለአህዛብ መልስ አላት!

ከመልካም ወጣትነት ወደ ለየለት ዕብደት ከተድላ ደስታ ወደ ልቅሶና ዋይታ
መልካም የነበረው ወጣት በዕብዶች፣ አጭበርባሪዎችና ዕውራን መሪዎች እየተጭበረበረና እያበደ ወደ ገደል እየገባ ነው።
በኦርቶዶክሳዊ እምነቱ ለዘመናት በሥነ ምግባር ታንጾ ደስተኛ የነበረው ትውልድ ወደ ለየለት ዋይታና ልቅሶ እየገባ ነው።

ዕውራን መሪዎቻቸው በዘረፉት ገንዘብ እየሳቁና እየተሳለቁ ትውልዱን ግን እየሳቁበትና እየተሳለቁበት፣ ብሎም እያሳቀቁት ነው።
ዛሬ ላይ ሃይማኖት-አልባ የሆነው የትናንቱ የአውሮፓውያኑ የፕሮቴስታንት እንቅስቃሴ መጀመሪያ ላይ እንደዚህ ነበር። አሁን ላይ በሥነ ምግባር ጉድለት በዓለም ላይ አንደኛ ሆኗል። የአምልኮ ቦታዎቻቸው እየተዘጉ ነው። ትውልዱ የዕለት ከዕለት ኑሮው ገደብ አልባ ኃጢአት መሥራት ላይ ያተኮረ ነው።

ምክንያቱ ደግሞ ዕውራን መሪዎች በባዶ ቅዠት ስለመሯቸው ነው። መጨረሻ ላይ እንደተጭበረበሩ ሲገባቸው የአምልኮ ቦታቸውን ሽጠው ለጭፈራና ለዳንኪራ መሰብሰቢያ አደረጉት።
የእኔ ትውልድ መልካም ወጣትም የነገ እጣ ፈንታው ይኼው ነው።
እጅግ በጣም ያሳዝናል።

“ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ።”
— ማቴዎስ 15፥14