Get Mystery Box with random crypto!

ጠብታ የሕይወት ትምህርት አንድ ወጣት የዩንቨርሲቲ ተማሪ ከፕሮፌሰር መምህሩ ጋር መናፈሻ | የማለዳ ብስራት

ጠብታ

የሕይወት ትምህርት

አንድ ወጣት የዩንቨርሲቲ ተማሪ ከፕሮፌሰር መምህሩ ጋር መናፈሻ ውስጥ ቁጭ ብለው ያወራሉ፡፡ ፕሮፌሰሩ ከተማሪዎች ሁሉ ይህን ተማሪ በጣም ስለሚወደው እንደ ጓደኛው አድርጎ ነው የሚያየው፡፡ ፊትለፊታቸው ጫማውን አውልቆ የመናፈሻውን ፅዶችና ሳሮችን የሚያስተካክል ሰራተኛ አለ:: ተማሪው የጽዳት ሰራተኛውን እያየ ለፕሮፌሰሩ:- “ፕሮፍ ዛሬ አንተም እኔም ደብሮናል፤ ለምን ያኛውን ሰውዬ ‹ትሪክ› አንሰራውም? ያወለቀውን ጫማ እንደብቅበትና ጫማዎቹን ሲያጣቸው እንዴት እንደሚበረግግ እዛ ጋር ደበቅ ብለን እንመልከተው” ይለዋል። ፕሮፌሰሩም፡ “ወጣቱ ጓዴ ምንም እንኳ ቢደብረን ድሃዎችን እያሰቃየን እኛ መደሰት የለብንም፡፡ ባይሆን እኛ ገንዘብ አለን በገንዘባችን የበለጠ ደስታን ማግኘት እንችላለን፤ ሂድና ቀስ ብለህ ሰውዬው ሳያይህ ባወለቀው ጫማዎች ውስጥ ገንዘብ ከተህበት ና፤ ከዛም ተደብቀን የሚሆነውን እናያለን” አለው፡፡ ተማሪው ፕሮፌሰሩ እንዳለው ቀስ ብሎ የሰውዬው ጫማ ውስጥ በርካታ ገንዘብ ከቶበት መጣና ከእሱ ጋር ደበቅ ብለው የሰውዬውን ሁኔታ መከታተል ጀመሩ፡፡

ሰውዬው ፅዳቱን ጨርሶ ኮቱን ለበሰና ጫማውን ለማድረግ ሲታገል ይቆረቁረውና ጎንበስ ብሎ ጫማውን ሲያራግፈው ብሮችን ያገኛል፡፡ ደነገጠ!! ዙሪያውን ቢያይ ማንም የለም፤ ደግሞ ደጋግሞ ቀኝና ግራ ሲመለከት ማንም ሰው የለም፡፡ በአግራሞት አንገቱን እየነቀነቀ ገንዘቡን ኪሱ ውስጥ ከከተተው በኋላ ሁለተኛ እግሩ ጫማውን ለማድረግ ሲያነሳ በተመሳሳይ ገንዘብ ያገኛል፤ አሁንም አላመነም!! በጉልበቱ ተንበረከከ አንገቱንም ወደ ሰማይ ቀና አደርጎ ጮክ ብሎ...“ጌታዬ የሚስቴን መታመም አውቀህ ነው አይደል? ካንተ ሌላ ማንም እንደማይረዳት አውቀህ ነው አይደል? የልጆቼን ዳቦ ማጣት አይተህ ነው አይደል? ምስጋና ይግባህ ጌታዬ” አለ፡፡

ተማሪው የሰውዬውን ሁኔታ ሲመለከት ልቡን ነካው:: አይኑ እንባ አቀረረ፡፡ ፕሮፌሰሩም “ቅድም ካሰብከው ‹ትሪክ› ይልቅ አሁን የተሻለ ደስታ እንዳገኘህ አልጠራጠርም” አለው:: ተማሪው እንባውን እየጠረገ... “ፕሮፌሰር እስከዛሬ ካስተማርከኝ ሁሉ እንደዚህ ያለ ትምህርት አስተምረኸኝ አታውቅም፤ በህይወቴ የማልረሳውን ትምህርት ነው ያስተማርከኝ፤ ለካ እውነትም ከመቀበል ይልቅ መስጠት የተሻለ ነው” በማለት መለሰለት፡፡

በሕይወት ጉዟችን ከማን ጋር እንደምንገናኝ አናውቅም፡፡ በመንገዳችን ሁሉ ብዙ የሕይወት ዘመን ትምህርት የሚሰጡን ሁኔታዎች ሊያጋጥሙን ይችላሉ፡፡ የማንንም የሕይወት መንገድ በእርግጠኝነት ማወቅ አንችልም፡፡ ሰዎች ምን አይነት ሕይወት እያሳለፉ እንደሆነ በእርግጠኝነት ማወቅ አንችልም፡፡ ስለሆነም በአገኘንው አጋጣሚ ሁሉ የሰዎችን ቁስል እየነካካን ሰዎችን ከመጉዳት ይልቅ ቀርበን እንረዳቸው፡፡ ከዚያ ምን ማድረግ እንዳለብን እንወስናለን፡፡ በሰዎች ሕይወት ለመቀለድና ለመሳለቅ አንሞክር። ሰዎችን ለመፈረጅ አንቸኩል!!

ለቻናሉ አዲስ የሆናቹ Join በማድረግ ተቀላቀሉ

@yemaledabisrat
@yemaledabisrat
@yemaledabisrat