Get Mystery Box with random crypto!

የልቤ ድርሰት የብዕር ጠብታ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yelbedrset — የልቤ ድርሰት የብዕር ጠብታ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yelbedrset — የልቤ ድርሰት የብዕር ጠብታ
የሰርጥ አድራሻ: @yelbedrset
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.12K
የሰርጥ መግለጫ

Well come😊
✍ትኩረት ነጥቦች
፩ ፦ግጥም ፪፦ድርሰት ፫፦ፍልስፍና
፬፦ስዕል ፭፦ሙዚቃ ፮፦ስሜት ፯፦ፎቶ
✍አላማ
~> በዚህ ቻናል አዳማጭ ያጡ ልቦችን እናንኳኳለን ከዝምታው አለም እንዲወጡ ፣ የልባቸውን ድርሰት የብዕራቸዉን ጠብታ እንዲያጋሩ ፣ የዉስጥ እረፍት እንዲያገኙ እና ወደ ወደፊት ህልማቸው አንድ እርምጃ እንዲጠጉ ማድረግ ነው። inbox @amanytz
የሁሉም ሰው ልብ ደራሲ ነው!!❤

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-29 14:50:54 #ተከታታይ_ልብ_ወለድ_ታሪክ
.
.
.
.
#የኔ_ታሪክ!

ክፍል - ፴፰
.
.
.
"የልብ እርቀት እንጅ የቦታ እርቀት ፍቅርን አይገድብም!!"
.
.
..አማኑኤል ጓደኛዉን ገድለው እርሱን ሳይገሉ የተዉበት ምክኒያት እጅግ አበሳጨው። ሃዘኑ መራር ሆነ!!

በሃገረ ኢትዮጵያ ያለው የዘር ጥላቻና ወገንተኝነት በየአካባቢው ያለ ብጥብጥና የሰው ነብስ መርከስ አማኑኤልንና ታሪኩን የተለያየ እጣ አዉቶላቸው አማኑኤልን ከሞት ሲያተርፈው ታሪኩን ወደ መቃብር ልኮታል።

ናፍቆትና መልአክ የፍየል ግምባር በምታክለው ከተማ አማኑኤል አፈላልጎ ማግኘት አልከበዳቸዉም በተለይ በተፈጠረው በታሪኩ እልፈት ምክኒያት ሁሉም ሰው አማኑኤልን ያዉቀዋል። ሁለት ሶስት ቦታዎች እንዳጠያየቁ የአማኑኤልን መገኛ ጓደኛው ማረፉን ተከትሎ መቃብሩ ስር እንደማይጠፋ ተነግሯቸው ወደዚያው አመሩ..በቦታው ሲደርሱ አማኑኤል እና ብሩክን አገኞቸው። አማኑኤል በማልቀስ አይኑ ቡዝዝዝ ብሎ አንገቱን ደፍቶ ስለነበር ከፊቱ መተው እስኪቆሙ አላየቸዉም ነበር።

ናፍቆ ጎንበስ ብላ ቀኝ እጇን ዘርግታ አማኑኤልን ቀና አደረገችውና..'የኔ ጌታ..?' አለችው አይኗ እንባ ሞልቶ..አማኑኤልም አይኑን በደንብ ገለጠው..ሊያምን አልቻለም..ተኝቶ እየሃለመ መሰለው...'ና..ናፍቆት..?' አለ ድምፁ ስልል ብሎ..'አቤት የኔ አለም መጥቸልሃለሁ..!' ስትለው..ተጠመጠመባት..ተቃቅፈው ያለቅሱ ጀመር..

መልአክና ብሩክ ብቻቸዉን እንተዋቸው ብለው በመጠቃቀስ ከመቃብር ስፍራው በታች ወደሚገኘው ወንዝ ወረዱ..
.
.
.
እናቱ ወይዘሮ መብራቴም በድንጋጤ ታመው አድረው ልጃቸው እዛው መቃብር እዳለቀቀ ሲሰሙ ምሳ ቢጤ ቋጥረው ወደ መቃብር ስፍራው አመሩ።
.
.
.
አለም'ባንተ እና ኮነሬል ማንያዘዋል ልክ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ሲል ከአማኑኤል ቀየ ደረሱ..ጊዜ ሳያጠፉ ያቀዱትን እቅድ አማኑኤልን በማፈላለግ ጀመሩት..እቅዳቸዉን አለም'ባንተ ያዉጣው እንጅ ከእቅዳቸው በተለየ ኮነሬል ማንያዘዋል የማያዉቁት ሌላ ሴራ አስቧል። የተስማሙበት እቅድ ኮነሬል ማንያዘዋል ስልጣናቸዉን ተጠቅመው አማኑኤልን ግምባር ተሰላፊ ወታደር ዉስጥ ማስገባትና በዘመቻ ወቅት የጠላት ወገን ነው ተብሎ እንዲገደል ማድረግና ናፍቆትን ከአለም'ባንተ ጋር አጋብቶ ወደ ዉጭ ሃገር መላክ ነው።

ኮነሬል ማን ያዘዋል በከተማው የሚገኙ ወታደሮችን አፈላልጎ ቀየዉን ዞር ዞር ብለው አጠያይቀው በተነገራቸው መሰረት ወደ መቃብር ስፍሳው አመሩ..በቦታው ሲደርሱ አማኑኤልና ናፍቆት ተቃቅፈው እያለቀሱ አዩዋቸው። ተጠግተው ከበቧቸው..

ሰው በተመሳሳይ ሰዓት ጥልቅ ሃዘን እንዲሁም ምሉዕ ደስታ ሊሰማው ይችላል! አማኑኤልም እየተሰማው ያለው እንዲያ ነውና..ናፍቆት ትልቅ እረፍት ተሰማት በእቅፉ ሽሽግ አለች ልቧ በደስታ ሰከረ.. ከዚህ ስሜታቸው የኮነሬል ማንያዘዋል ቁጣ ያዘለ 'ናፍቆት' የሚል ጥሪ አነቃቸው..ተደናግጠው የከባቸዉን ጋንታ አዩ..'ባንዴ ነገሩ ተነፍቆ ከመገናኘት ወደ አስጨናቂ ሁኔታ ተቀየረ..

ኮነሬል ማንያዘዋል ወደ ወታደሮቹ ዞር ብሎ 'ያዙት ያሄን አመዳም!' አላቸው..ቀጥታ ከናፍቆት እቅፍ መንጭቀው አንጠለጠሉት..ናፍቆት ከመሬት እየተንከባለለች ዉይይይይ አለች..ሌላኛው ወታደር እርሷንም አፏን ይዞ አንጠለጠላት..አማኑኤል ግን በመታከት ስሜት ዝም አለ..አለም'ባንተ መንፈሱ በደስታ ሞላ ከመጀመሪያው ያሰበዉን ለማድረግ እንደሚችል እርግጠኛ ሆነና በወገቡ የያዘዉን ሽጉጥ አወጣና በእጁ ያዘ..

ይሄ ሁሉ ሲሆን መልአክና ብሩክ አላዩም አልሰሙም በመቃብሩ ስፍራ የነበሩ አንዳንድ ሰዎች እንኳ ወታደሮቹን ሲያዩ እግሬ አዉጭኝ ብለው ወተዋል..

መቼም በሃገረ ኢትዮጵያ ፈጣሪ እራሱ እንደ ወታደር አይ'ፈራም! የሆኑ ጣዖቶች ነው እሚመስሉን መግባቢያቸው ዱላ የሆነ..ለመንግስት ዘብ የቆሙ..በራሳቸው ስልጣን የሌላቸው..ያላመኑበትን ነገር ስለታዘዙ ብቻ የሚያደርጉ..የመስዕዋት ልጆች ናቸው።

አማኑኤልን ጨምድደው ከያዙት ወታደሮች መካከል አንዱ ኮነሬል ማንያዘዋልን እያየ..'ኮነሬል ቀጥታ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዉሰደው ዎይስ ሌላ ቦታ አለ?' ብሎ ጠየቀው..ኮነሬሉም..'አይ ፖሊስ ጣቢያ አይሄድም..!' አለ..

አማኑኤል ከሚሰሙት ተደራራቢ ስሜቶች በላይ ቁጣው ገንፍሎ ወጣ አይኑ ደም ለበሰና..'አንተን ብሎ ኮነሬል! ቱ! ማዕረግ አሰዳቢ ወራዳ ነህ!' አለው..ይሄኔ ኮነሬል ማንያዘዋል ቱግ አሉና ዘለው አነቁት..'አንተ ዲቃላ ደግሞ ስለ ማዕረግ ምን ታዉቅና ነው! ስለ ወታደር ምን አይተህ ነው አፍክን ሞልተህ እምትናገር!' ሲለው..አማኑኤል የፌዝ ሳቅ ሳቀና..'የኔ ጀግና አባት ኮነሬል ሰዉነት አዳሙ ለሃገሩ ተዋድቆ በክብር ላገኘው ኮነሬልነት ህይወቱን ለከፈለለት ወታደርነት አንተ እንደማትገባ አዉቃለሁ!!' አለው..
ኮነሬል ማንያዘዋል እጃቸዉን ከአማኑኤል አንገት ላይ አነሱ..የሰሙትን አላመኑም..'ምን? አንተ እዉነት የኮነሬል ሰዉነት አዳሙ ልጅ ነህ? አይ አይሆንም የስም መመሳሰል ነው!' አይናቸው እንባ ሞላ..እንደ መዉደቅ ተንገዳገዱ..
'ወይ ጉዴ ወይ የምድር መጥበብ!' አማኑኤልን ትኩር ብለው አዩትና..'እዉነት አንተ የጓዴ የሰዉነት አዳሙ ልጅ ነህ!?' አለው..ይሄኔ ወይዘሮ መብራቴ ከኋላ ደርሳ ኑሮ ከማህል ገብተው..'አዎ ጀግናው እሩሩሁ የሰዉነት አዳሙ ልጅ ነው! የኔ ልጅ ነው!' አሉ ኮነሬል ማንያዘዋል ላይ አፍጠው..

ኮነሬል ማንያዘዋል ጉልበቱ ከዳውና ተንበረከከ..ለቅፅበት በሃሳብ ወደ ፲፱፺፫ መጨረሻዎቹ ወደዚያ ክፉ ምሽት ወደ ኦጋዴን አቀና..ሁለቱ ጓደኞቹ አብርሃምና ሰዉነት የሞቱበት ቀን ከፊቱ ላይ ድቅን አለ..አሁን ያለበትን ሲያስብ ከአዕምሮው በላይ ሆነበት..እንባዉን ጠረገና የለበሰዉን ኮፍያ አዉልቆ..'አንች መብራቴ ነሽ?..እኔን አላዎቅሽኝም?..ማንያዘዋል'ኮ ነኝ የሰዉነት ጓደኛ..! ለሶስት ካፈቀሩሽ ዉስጥ አንዱ..!' ድምፁ ተቆራረጠ..
ወይዘሮ መብራቴ ክው አሉ..ኮነሬል ሰዉነት አብዝቶ ስለ ጓደኞቹ ያወሯት ስለነበር እንዲሁም የ'ርሷን ልብ ለማሸነፍ ያደረገዉን ጥረት አስታዉሰው ፈገግ እንደማለት አሉና በመገረም ከኮነሬል ማንያዘዋል ጋር ተቃቀፉ..

ወታደሮቹን ጨምሮ ናፍቆትና አማኑኤል እየሆነ ያለው ግራ ገባቸው ዝም ብለው ማየታቸዉን ቀጠሉ..

አለም'ባንተም ግራ ቢገባዉም ነገሩ ከጄ ሳይወጣ ብሎ ሽጉጡን አቀባበለና ድምፁን ከፍ አድርጎ..'ድራማው እዚህ ላይ ይብቃ!!' አለና ሽጉጡን ወደ ሰማይ አንዴ ከተኮሰበት በኋላ አፈሙዙን ወደ ናፍቆት አዞረው..

መልአክና ብሩክ የተኩሱን ድምፅ ሰምተው ካሉበት በረው ቦታው ላይ ተከሰቱ..
.
.
.

..ይቀጥላል..

Aman YTZ
@amanYTZ23

join and share
@YelbeDrset
@YelbeDrset

inbox me @amanYTZ23
145 viewsAman YTZ, 11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 12:03:39 #ተከታታይ_ልብ_ወለድ_ታሪክ
.
.
.
.
#የኔ_ታሪክ!

ክፍል - ፴፯
.
.
..ናፍቆት ከቤት ከመዉጣቷ በፊት በተለያየ ጊዜ ሰው ስጦታ የሰጣትን የብር ሃብል፣ ብራስሌት፣ ጉትቻ እና የእናቷን የወርቅ ሐብል ጠራቅማ ይዛ ነበር።
.
.
.
የያዘቻቸዉን የብርና የወርቅ ምርቶች በየሱቁ ተዟዙራ ሸጠች እና ወደ አዲስ አበባ ተፈተለከች። ከአዲስ አበባ ጎንደር የፕሌን ትኬት ቆርጣ ስምንት ሰዓት አካባቢ ጎንደር ገባች እና ከኤርፖርት ወደ አዞ አቀናች። አዞ ላይ ሰዎችን ጠያይቃ ስልክ በመዋስ ወደ መልአክ ደወለችለት። መልአክ የሰማዉን ማመን ቢከብደዉም ናፍቆት ወደ ነገረችው ቦታ ሄደ..

መልእክና ናፍቆት ለብዙ ደቂቃ ያህል ተቃቅፈው አለቀሱ! መልአክ ድጋሚ አያታለሁ ብሎ አላሰበም ነበር እርሷም እንደዛው..እስከ ዘጠኝ ሰዓት ተኩል አካባቢ ቁጭ ብለው አወሩ ናፍቆት ወደ የት መሄድ እንደምትፈልግ እና ምን አድርጋ እንደመጣች አባቷ ያለፍቃዷ ሊያጋባት እንደነበር ሁሉንም አንድ ሳታስቀር አብራራችለት።

መልአክም የአማኑኤልን ሁኔታ መጨረሻ እስካየበት ቀን ድረስ እና አማኑኤል የነገረዉን ነገር ሁሉ ነገራት..ናፍቆትም 'የኔ ጌታ በኔ እንክብካቤ እንዲያገኝ እንደ እረሳኝ አስመሰለ! እኔን ለመጠበቅ የቆርቆሮ ቤት ተከራይቶ ከ'ናቱ እርቆ እዚ ተቀመጠ!..እያለች አለቀሰች። እንባዋን ጠራርጋ አማኑኤል ተከራይቶ ሲኖርበት ወደነበረው ወደ ቀበሌ ፲፬ ከመልአክ ጋር አቀናች በቦታው ግን አማኑኤልን አላገኙትም! ከአካራዮቹ መቸ እንደ ለቀቀ ጠይቀው ከወጡ በኋላ ወደ አገር ቤቱ ሄጄ መፈለግ አለብኝ አለች ናፍቆት..

መልአክ የተጓዘችዉን እርቀት በማየት እሚስደስታትን ለማድረግ እንደሚረዳት ቃል ገብቶላት ወደ ቤት ሄደው አድረው በጠዋቱ ወደ አማኑኤል ቀየ እንደሚሄዱ አስረዳት ናፍቆት ግን በሃሳቡ አልተስማማችም በአዳሪ መኪናም ቢሆን ከአማኑኤል ቀየ ገብቸ ማደር አለብኝ ብላ ድርቅ በማለቷ መልአክ ብቻዉን ወደ ቤቱ ሄዶ የተወሰነ ብር ካምፕ ካሉ ጓደኞቹ ተበድሮ ባንክም ላይ ያለችዉን ገንዘብ አዉጥቶ ልክ አስር ሰአት ከሩብ ላይ ከናፍቆት ጋር አራዳ መናህሪያ መኪና ያዙ..
.
.
.
አለም'ባንተ አልሞተም! ጭቅላቱ ላይ የደቀነዉን ሽጉጥ አፈ ሙዙን ወደ ሰማይ አቃንቷ ነበር የተኮሰው! ግን በህይወት አለ ማለትም አይቻልም ምክኒያቱም ቂጡን ጥሎ ነብሱን መስዕዋት እስከማቅረብ ድረስ እሚያፈቅራት ልጅ በራሱ ላይ መሳሪያ ደቅኖ ጥላው ሄዳለች የተኩስ ድምፅ ሰምታ እንኳ ዞራ አላየችዉም!!

ጥላቻ ለፍቅር ልክ እንደ የብርሃን ጥላሎት ማለት ነው። እንዲያዉም "ፍቅሩ ዉሸት ሊሆን ይችላል ጥላቻው ግን ሁሌም የእዉነት ነው!" የሚሉ አሉ እና እንኳን አፍቅሮ ላጣ እዲሁ ሰው ሲወድ እና ሲጠላ መጠኑ ይለያያል ሲወድ ገደብ አለው ሲጠላ ግን እስከጥግ ነው። በዚህ ትዉልድ ላይ የሆነ የጥላቻ መንፈስ ያንዧብብበታል! ለመፋቀር፣ አንድ ለመሆንና ለመማማር የራቀዉን ያክል ለጥላቻ፣ ለመከፋፈልና ለመቃቃር ቅርብ ነው። ሁሉም ሰው ዉስጥ የሆነ ቁጣ እና ሽንቁር አለ! ታዲያ "ቁጣ ልክ እንደ የመሬት ስበት ነው! ትንሽ ግፊት ብቻ ነው እሚፈልገው!!" እንዲሉ ማንኛዉም ነገር ለአመፅ እና ለብጥብጥ ይገፋናል።

የአለም'ባንተ ፍቅር የጣዖት ፍቅር ይባላል። ጤናማ የሰው ልጅ ፍቅር ያፈቀሩት ሰው ባይጋራው እንኳ ወደ ጥላቻ እማይቀየር ነው። ጤናማ ፍቅር ወይ ማፍቀሩን እሚቀጥል ወይ ደግሞ እንደ ትምህርት አይቶ ልቡን አጀግኖ እረስቶ ህይወቱን ያለ ዛ ሰው እሚኖር ነው። ፍቅር እንደ ሞረድ ነው! ወይ ይስላል ወይ ይሸርፋል! መሸረፉም መሳሉም ግን እንደ አያያዛችን ይወሰናል።

አለም ባንተ ናፍቆት ጥላው ከሄደችበት ቦታ ላይ በወገቡ ተዘርሮ ብዙ ቆየ። እሚያለቅሰው እንባ እንደ ሌለ ተሰማው። ብዙ ሃሳቦችን አወጣ አወረደ ልቡ በጨለማ ተከበበች የበረዶ ግግር ሰርታ የበረዶ ድንጋይ ሆነች።

ከአንድ ሰዓት በላይ ተዘርሮ ከቆየበት በመነሳት ወደ ኮነሬል ማንያዘዋል በመደወል ወዳሉበት አመራ። አይኖቹ እልህና ቁጣን ይረጫሉ በአዕምሮው እሬሱን ሊያጠፋ ሲሞክርና ናፍቆት አኳኋን እና ጥላው መሄዷ ያቃጭልበታል። ክፉ ነገርን አስቧል።
.
.
.
ናፍቆትና መልአክ ከመሸ ከአማኑኤል ቀየ ደረሱ ባንዱ ሆቴል ዳብል አልጋ ከያዙ በኋላ እራታቸዉን በሉ። ናፍቆት ከኑን በሙሉ በጉዞ ስላሳለፈች እና አማኑኤልን ያገኘችው ያህል 'የሚተነፍሰዉን አየር ተነፈስኩኮ!' እያለች ተረጋግታ ተኛች።
.
.
.
አለም'ባንተ ከኮነሬል ማንያዘዋል ጋር ቁጭ ብሎ ሁሉንም ነገር አብራራለት! ኮነሬል ማንያዘዋል በቁጣ ተነስተው ናፍቆትን ለማሳደድ ቢያስቡም አለም'ባንተ አረጋጋቸው እና ነገሩን ከስሩ ለመንቀል ማድረግ ያለባቸዉን ነገርም ባቀደው መሰረት አስረዳቸው! በዚያ ተስማምተው በኮነሬል ማን ያዘዋል የግል ምድብ መኪና ወደ አዲስ አበባ አቀኑ..

ኮነሬል ማንያዘዋል እና አለም'ባንተ አዲስ አበባ ገብተው አመሻሹ ላይ ጎንደር ደረሱ..
.
.
.
አማኑኤል ካለፈው አመት ጀምሮ ዱላ ያራቀዉን ጭንቅላቱ በፋሻ ተጠቅልሎ ኩታ ለብሶ ከብሩክ ጋር የቤተክርስቲያን መቃብር ስፍራ ላይ ቁጭ ብለዋል። አማኑኤል ከሃዘኑ በላይ 'ለምን ተረፍኩ? ለምን እኔንም አልገደሉኝም!? እሚል ጥያቄ እረብሾታል።

ከብሩክ በቀር የቀየው ሰው በሙሉ የመቃብሩን ስፍራ ጥሎ ወደየ ቤቱ ሲሄድ የእጅ ስልኩን አዉጥቶ ቁልፎቹን ተጫነ እና ወደ 'ሰዎቹ' ደወለ..ከሶስትና አራት ጊዜ ሙከራ በኋላ ስልኩ ተነሳ..
'እናንተ አረመኔ ዉሾች!'
'ልታመሰግነን ነው የደወልክ!?'
'ምን ብየ ነው እማመሰግናቹህ! እናንተ ጨካኞች አይኔ እያየ እኮ ነው ጓደኛየን የገደላቹህት..!' ጉሮሮዉን ሳግ ተሰማው እንባው ዱብ ዱብ አለ..
'በል ለምን ተረፍኩ ለምን አልገደላቹህኝም ከሆነ ችግር የለዉም ከፈለክ እንገድልሃለን!'
'ኑ ኑ ግደሉኝ! እኔ ከወንድሜ ተለይቸ መትረፍ የለብኝም! ኑ ግደሉኝ! ቆይ ቆይ ግን ለምን ለምንድን ነው እኔን ያልገደላቹህኝ ለምን!!!' ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ..
'ተመስገን አትልም! ለማንኛዉን በህይወት የሌለውን አባትህ አመስግን የርሱ አብራክ ክፋይ መሆንህ አትርፎሃል! ድጋሚ ግን በኛ መንገድ አንዳናገኝህ!!' አለና ስልኩን ከአማኑኤል ጆሮ ላይ ዘጋበት..

አማኑኤል ስልኩን በሃይል መሬት ላይ አጋጭቶ ብትንትን አደረገውና አአአአአአአ ብሎ ጮኸ የታሪኩ መቃብር ላይ ተደፍቶ አለቀሰ..

ናፍቆት እና መልአክ በጠዋት ተነስተው ቁርስ ከበሉ በኋላ ወደ ፍለጋ ተሰማሩ..
.
.
.

..ይቀጥላል..

Aman YTZ
@amanYTZ23

join and share
@YelbeDrset
@YelbeDrset

inbox me @amanYTZ23
203 viewsAman YTZ, 09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 16:57:48 #ተከታታይ_ልብ_ወለድ_ታሪክ
.
.
.
.
#የኔ_ታሪክ!

ክፍል - ፴፮
.
.
.
"ፍቅር እና ሞት ሁለት ያልተጋበዙ እንግዳዎች ናቸው። ፍቅር ልብን ሲወስድ ሞት ደግሞ የልብን ምት ይወስዳል!!"
.
.
..ታሪኩና አማኑኤል አመሻሽ ላይ በቀያቸው አቅራቢያ ወደ ሚገኘው ተራራማ ስፍራ በማቅናት የመሳሪያ አቅርቦት ከጠየቋቸው ሰዎች ጋር ተገናኙ። ቦታው ዞዋራ እሚባል አይነት ስለሆን የህግ ቅጥረኞች ሆነ የቀየው ሰው አይሄድበትም! በድብቅ ለሚሰሩ ስራዎች እሚያገለግል ስፍራ ነው።

አንድ ሰው መሳሪያሲሸጥ እንዲህ ወስዶ አቀብሎ ብር መቀበል ሳይሆን መሳሪያዉን አቀባብሎ ወደ ሰማይ ተኩሶ መስራቱን አረጋግጦ ነው እሚሸጥ። አማኑኤልና ታሪኩ 'ሰዎቹን' በቦታው አግኝተው ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ መሳሪያዉን አስረከቧቸው 'ሰዎቹ' መካከል መሪያቸው ብቻ ነው አማርኛ እሚናገር ሌሎቹ ሌላ ቋንቋ ነው እሚናገሩ..
ታሪኩ ወደ መሪያቸው እያየ.. 'ከቀየው ብዙ ስላልራቅን መሳሪያዎቹን አንድ ባንድ መሞከር አስፈላጊ አይመስለኝም! በደንብ ተመልከታቸው እና እሚያጠራጥሩህን ብቻ ሞክራቸው! አጠቃላይ ዋጋቸውም ፫ መቶ ፶ ሺ ብር ነው! ገንዘቡን በካሽ አሁን መክፈል ይኖርባቹሃል!!' አለው..ይሄኔ 'ሰዎቹ' ተያይተው ሳቁና ከ'ሰዎቹ' መካከል አንዱ ክላሹን አንስቶ አቀባበለና በተሰባበረ አማርኛ..'ገንዘቡ ይሶጣቹሃል መሴሪያዎቹን ግን ሎሙን አንቶ ላይ አንሞክርብህም!' አለና አከታትሎ የታሪኩ ደረት ላይ የጥይት ጋጋታ አዘነበበት..
.
.
.
ናፍቆትና አለም'ባንተ ተፋጠው ቁመዋል። አለም'ባንተ ጭንቅላቱ ላይ የደቀነዉን ሽጉጥ እንዲያዎርድ ደጋግማ ብትለምነዉም አልሰማት አለ።
'አለም እባክህን እንዲህ አታድርግ እባክህ..!
'እሽ ምን ላድርግ!? እማፈቅራት ሴት የሌላ ስትሆን ዝም ብየ ልይ ወይንስ ያለፍቃዷ አስገድጀ ላግባት! መሄድሽም ለኔ ስሜት ሳይኖርሽ ባገባሽም ሁለቱም ይጎዱኛል!'
'ታዲያ ይሄ ነው መፍትሄው?ተው እንዲህ አታድርግ እኔንም በፀፀት እንድኖር አትድርገኝ!'
'እንዲያዉም ጥሩ ነው! እምትፀፀች ከሆነማ አደርገዋለሁ ቢያንስ በፀፀትም ቢሆን ታስቢኛለሻ! ምን አልባትም በሌላኛው ህይወት ቀድሜ በመሄዴ ቀድሜ አጊንቸሽ የኔ አድርግሽ ይሆናል!!'
'አለም እንደዛ አትበል አሁን ሽጉጡን ጣለዉና ቁጭ ብለን እናዉራ!'
'ምንድን ነው እምናወራ?! እሽ ታፈቅሪኛለሽ የኔ ትሆኛለሽ ልብሽ ሳይሸፍት አብረሽኝ ትሆኛለሽ!'
'አለም ካሁን በፊት ነግሬሃለው! ከኔ የሌለኝን ነገር ልሰጥህ አልችልም! እባክህን በህይወቴ አንድ ደስተኛ እሚደርገኝ ነገር ብቻ ነው ያለኝ እርሱም አማን ነው! እና እርሱን ባንተ ሞት ላጣው አልፈልግም!!'

አለም'ባንተ ትንፋሽ ወሰደና ናፍቆትን እያየ..ድምፁን ከፍ አድርጎ.."ህይወትና ሞት!! ሁሉም ሰው ህይወትን ይወዳል ሞትን ግን ይጠላል! ምክኒያቱም ህይወት ጣፋጭ ዉሸት ናት! ሞት ደግሞ መራር እዉነት!" ለኔ ግን ህይወት መራር እዉነት ሆናብኛለች ሞት ደግሞ ጣፋጭ ዉሸት! ስለዚህ ለምን እኖራለሁ ፍቅሩን ለማያገኝ ህልሙ ለጎዳው ሰው ያም ሞት ነው ያም ሞት ነው።' አላትና የሽጉጡን ጥይት ሰቀለው..በአይኑ የእንባ ዘለላዎች ያለማቋረጥ ይወርዱ ጀመር..አይኑን በሃይል ጨፈነ..

ናፍቆትም..'በቃ ይሄ ስንብት ነው? ቻው ማለት ነው? ግን ይህን እወቅ ፍቅር በመስዕዋትነት ቢገለፅም! ላ'ፈቀሩት ሰው ከመሞት መኖር ይከብዳል!' አለችዉና አይኖቿ በእንባ ተሞሉ ፊቷን አዙራ ትራመድ ጀመር..

አለም'ባንተ በሃይል የጨፈነዉን አይኑን ሲገልጥ ናፍቆት ከ'ርሱ እርቃ ስትራመድ አየና መልሶ አይኑን ጨፍኖ የሽጉጡን ቃታ ያዘ..

ናፍቆት መንገዷን ቀጥላለች..ከኋላዋ የተኩስ ድምፅ አስተጋባ..ዞር ብላ ሳታይ እያለቀሰች እሮጠች..
.
.
.
ታሪኩ ደረቱ በመሳሪያ ድብደባ ወንፊት ሁኖ ተዘረረ..አማኑኤል በጣም ተደናግጦ ወደ ታሪኩ በመጠጋት አቀፈው እና ወደ ሰዎቹ እያየ አይኖቹ ደም ለብሰው..'እናንተ ዉሾች ምን ማድረጋቹህ ነው! ወይኔ ወንድሜ!' ብሎ ጮኸና ፊቱን ወደ ታሪኩ መልሶ..'ወንድሜ ወንድማለም..አለህ! አይሆንም! አይሆንም አአአአአአ..!' ወደ 'ሰዎቹ' ፊቱን ሲመልስ የ'ሰዎቹ' መሪ በሰደፍ ግንባሩን አለዉና ተዘረረ..አማኑኤል እራሱን ድንዝዝዝዝ አለዉና አይኑን ጨፈነ..
.
.
.
ወይዘሮ መብራቴ ልጃቸው ከመሸ ወቶ ሳይመለስ ሲቀር ወደ ብሩክ ደዉለው በመጥራት ከጎረቤቶቿ ጋር ፍለጋ ወጡ። ቀየዉን ተዟዙረው ቢፈልጓቸው ሊያገኟቸው አልቻሉም።

ብሩክ አማኑኤል ከታሪኩ ጋር ሊሆን እንደሚችል እና የመሳሪያ ሽያጭ ሊያደርጉ ከቀየው ወተው ሊሆኑ ይችላል ብሎ በማሰብ የታሪኩን ቤተሰቦች በማሳዎቅ ተሰባስበው ሰዎችን በማጠያየቅ ወደ ተራራማ ስፍራው ከወይዘሮ መብራቴ፣ ከታሪኩ አባትና ከሰፈር ሰዎች ጋራ አቀና።
በቦታው ደርሰው ሁሉም የያዙትን የመብራት ባትሪ ሲያበሩ ሁለት ተደራርበው የወደቁ ሰዎችን ተመለከቱ..

ወይዘሮ መብራቴ ዉይይይይይ ብለው እየጮሁ ወደ ወደቁት ሰዎች አመራች..ሁለቱም በደም ተነክረዋል..ለቅሶዉና እሪታው ተራራዉን አነቃነቀው..ቦታው በለቅሶ ድብልቅልቅ አለ..ብሩክ እየተንቀጠቀጠ ወደ ታሪኩና አማኑኤል ተጠጋ..ታሪኩን ሲያይ ደረቱ በጥይት ተበሳስቷል..አማኑኤል ደግሞ ከግምባሩ እንከ አይኑ በደም ተሸፍኖ በታሪኩ ስር ወድቋል..ሁለቱም አይንቀሳቀሱም..

ወይዘሮ መብራቴ ልጃቸዉን በደንብ አጥርተው ካዩት በኋላ ትንፋሻቸው ተቆራረጠ..ልባቸው ቀጥ ያለ ያህል ተሰማቸው..ተዘረሩ..
.
.
.
ህይወት..የእንቅልፍ አፍታ ናት..!
ሞት.. ደግሞ ከእንቅልፉ እሚያነቃን አስደንጋጭ ቅዠት ነው!!

"በመጨረሻም ፣ መላ ህይወት የመለያየት ተግባር ይሆናል፣ ግን በጣም የሚጎዳው ነገር ለመሰናበት እሚሆን ጊዜ አለመስጠቱ ነው።"


..ይቀጥላል..

Aman YTZ
@amanYTZ23

join and share
@YelbeDrset
@YelbeDrset

inbox me @amanYTZ23
253 viewsAman YTZ, 13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 18:42:57 #ተከታታይ_ልብ_ወለድ_ታሪክ
.
.
.
.
#የኔ_ታሪክ!

ክፍል - ፴፭
.
.
.
"በፍቅር መኖር ምክኒያት መስዕዋትነት ይወለዳል!"
.
.
..አለም'ባንተ ናፍቆት ወደ ቤተክርስቲያን በገባችበት ሰዓት እርሱም ቅጥር ግቢው ዉስጥ ነበር። በዉድም በግድም የግሉ እንድትሆን የቻለዉን ሁሉ ከፀሎት ጀምሮ እያደረገ ባለበት ሰዓት ናፍቆት ከደብሩ ገብታ እምታደርገዉን ሁሉ ይከታተል ስለነበር ቀጥታ የደም ስሯን ቆርጣ ስትዘረር እንደ ወፍ በሮ በመድረስ ከወደቀችበት አፋፍሶ አንስቶ ወደ ህክምና የወሰዳት..

ብዙዉን ጊዜ በረኪና ጠተው እራሳቸዉን ለማጥፋት እሚሞክሩ እና ደምስራቸዉን በስለት እሚቆርጡ ሰዎች ተሎ ህክምና ካገኙ ከሞት ይተርፋሉ..ናፍቆትም አልሞተችም..ተርፋለች..

ናፍቆት አይኗን ስትገልጥ በሰዎች ተከባለች..እንዳልሞተች በማወቋ ተናደደች..እንቅልፍ የመተኛት ፍላጎት ባይኖራትም ደም ስለፈሰሳት የድካም ስሜት ተጫናትና ተኛች..

አለም'ባንተ ናፍቆትን ከቤተክርስቲያን አዉጥቶ እስክትታከም ድረስ እንባው አላባራም ነበር።

አንዳንዴ በህይወታችን ያሉ ሰዎችን እስከነ ጭራሹ ልናጣቸው እንደምንችል ካላወቅን የነሱ ዋጋ ስናጣቸው ነው እሚገባን! ለዛም ነው ሰው ሲታመምና ሲሞት እሚጠላው ሁሉ እሚወደው። በህይወታችን ብዙ ሰዎች አሉ ታዲያ ከኒያ ሰዎች መካከል ልዩ ቦታ እምንሰጣቸው ሰዎች አሉ። እኒህ ልዩ ሰዎች ቢያስቀይሙን ወይ ብንጣላቸው "ይበልጥ እሚጎዳን የቅርብ ሰው ነው!" እምትለዉን አባባል ይዘን ለይቅርታ ልባችን ዘግተን የወደድናቸዉን ያህል ያለፈዉን ለመርሳት እየከነከነን እንደ ራቅናቸው እንኖራለን ታዲያ እኒህ ሰዎች ቢታመሙ ወይ ቢሞቱ ግን ሃዘናችን እና ፀፀታችን መቼም አይጣል ነው።

ልባቹህን ለጥላቻ ቦታ አትስጡት ሁሌም ይቅር ባይ ልብና ይቅርታ ጠያቂ አንደበትን ገንዘባቹህ አድርጉ። ጥላቻ የቁጣና የፀፀት ማዕከል ነው እሚያደርጋቹህ ይቅር ብላቹህ ግንኙነታቹህን እንደነበረው መመለስ ቢከብዳቹህ እንኳ ቢያንስ ቂምና መቃቃሩን ትታቹህ ነገሩን እርሱት ይቅርታ አድርጋቹህ ግንኙነታቹህን የእግዜር ሰላምታ ብቻ አድርጉት።
.
.
.
አማኑኤል ከታሪኩ ጋር ስራ ጀመረ። የመሳሪያ ግዥ ወይንም ሽያጭ ካለ ታሪኩና አማኑኤል ነው እሚያገበያዩት።

ስራው ህይወትን እስከማጣት ድረስ አደጋ ቢኖረዉም ትርፋማነቱ ጥሩ ስለሆነ አምርረው ነው እሚሰሩ። ታሪኩ ብዙ ወዳጆች ቢኖሩትም ጥቂት ጠላቶችም አሉት እኒህ ጠላቶቹን ያፈራቸው ጥራት በሌለው መሳሪያ አቅርቦት ፣ የስራ እድላቸዉን በመቀነስ እና 'ለጠላታችን መሳሪያ ሸጠ!' በማለት የያዙበት ቀን እሚጠብቅ ቂምና ጥላቻ አለ።

ለሁለት ሳምንታት ከሰሩ በኋላ ከማያዉቁት ሰው ስልክ ተደወለላቸዉና የተለያዩ መሳሪያዎች አቅርቦትና የተለያዩ ጥይቶችን ለመግዛት ሰው እንደጠቆማቸው በመንገር በሶስት ቀን ዉስጥ በፈለጉት ሂሳብ እንዲያቀርቡላቸው በማስረዳት ቀን ቀጠሯቸዉን ያዙ። በዚህ ስራ ላይ አማኑኤል ትልቅ ደስታ ተሰማው የተሻለ ገንዘብ ማግኘት እና ለእናቱ መካሻ የሆነ ነገር ለማድረግና ለናፍቆት ማፈላለጊያ ትንሽ መቆጠብ እንደሚያስችለው በማሰብ ከታሪኩ በይበልጥ በከተማዋ እየተዘዋወረ መሳሪያዎቹን አሰባሰበ..
.
.
.
ናፍቆት ሆስፒታል አድራ በአባቷ፣ በእናቷ፣ በአለም'ባንተ እና በመሰረት ታጅባ ወደ ቤቷ ተመለሰች። ኮነሬል ማንያዘዋል እና ወይዘሮ ሚሚ የልጃቸው እርምጃ እጁጉን ቢያስፈራና ቢያሳዝናቸዉም በጤና ስላላዩት ፀበል እንድትሄድ ወሰኑ..

ናፍቆት አለም'ባንተን ብቻዉን ስታገኘው አርምሞ የያዘችበትን ዝምታ ሰብራ በቁጣ ሰደበችው!
'ምን አገባህ! እንድኖር ካለፈቀዳቹህልኝ ቢያስ እንድሞት ተዉኝ! ትንሽ አይከብድህም! የሆዴን የዉስጤን ባዋይህ የህልሜ የደስታይ ድንኳን ሰባሪ ለመሆን ከፊት ስትሰለፍ ትንሽ አታፍርም! ፍቅር ላንተ ይሄ ነው በቃ!' ተንደገደገችበት..አለም'ባንተ ዝም ብሎ ሰማትና በተጋደመችበት ጥሏት ወጣ..
.
.
.
በወንድ እና በሴት ልጅ መካከል ያለ ግኑኝነት በወንድምና እህትነት እሚቀጥለው ሁለቱም የግላቸው ፍቅረኛ ሲኖራቸው ነው! ካልሆነ በሁለቱም ባይሆን እንኳ በአንዱ ጎን የፍቅር ስሜት ይኖራል። ሴቶች ላይ ብዙዉን ጊዜ የሚፈጠር ችግር አለ እርሱም ከልቡ ለቀረባቸው ወንድ ሁሉ ከልባቸው መቅረብ እና የተለየ ስሜት እንዳለው ሲገልፅ ደግሞ እንደማያዉቁት ሰው ማየት ትልቁ ችግራቸው ነው። ወንዱ ከልጂቱ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ እና ሁን ያለችዉን በመሆን አድርግ ያለችዉን ያደርጋል! ባዘነች ጊዜ ከጎኗ ነው! እሚያዝናናትም እርሱ ነው! የተለያዩ ነገሮችንም እምታገራው ለርሱ ነው ግን አታፈቅረዉም! እሚያደርገዉን ጥረት ሁሉ እንደ ተራ ወንድምነት ብቻ ያዩታል! ወንዱ ደግሞ አብሯት በሚያሳልፋቸው ሁኔታዎች ሁሉ ለርሱ ቦታ ያላትና ፍቅርን እንደምትጋራው ያስባል! ማሰቡም ስህተት ማለት አይቻልም! ምክኒያቱም እርሷ እምታደርጋቸው ድርጊቶች በሙሉ ይገፉታል በህልሙ እንዲያምን ያደርጉታል! ብዙዉን ጊዜ አብዛኛዉን ሴቶች ላይ ይህ ቅስም ሰባሪ ሁኔታ ይፈጠራል..

ወንዱ ደግሞ ትልቁ ችግሩ ስለተንከባከባት ጊዜ ስለሰጣት እና ስለቀረባት ስለቀረበችው ያፈቀረችው ይመስለዋል። ግንኙነቱን ግልፅ አያደርገዉም ዝም ብሎ ዙሪያ ጥምጥም ይሄዳል! ወይ ስሜቱን አይገልፅ ዝም ብሎ ጊዜዉን ያባክንና በልጅቱ አካባቢ ሌሎች ሲያንዣብቡ ወይ ታፈቅረኛለች ብሎ ሲያምን ስሜቱን ይገልፃል! ታዲያ የማይጠብቀው መልስ ሲያገኝ እንዲህ ሁኘላት፣ እንዲህ ብላኝ፣ በዚህ ወርጀላት በዚያ ወጥቸላት፣ እንደኔ እምትቀርበው ሰው ሳይኖር..፣ አታለለችኝ፣ ተጠቀመችብኝ..ቅብጥስ ይላል!! ምንአልባት ልጅቱ'ኮ በቃ እንዲሁ እንደ ወንድምነት አይታው አቅርባው ይሆናል ግን የርሱ ህልም እና ስሜት የፈጠረዉን ቅዠት በማመን በልጅቱ ላይ ጥላቻን ይይዛል ቂምን ያቅራል..!!

ከተቃራኒ ፆታ ጋር ያላቹህን ግንኙነት ግልፅ አድርጉት!! ሌላ ነገር እንዳለ እያወቃቹህ ዝም ብላቹህ የሰው ጊዜ አታባክኑ! ቅርርባቹህ የፍቅር ካልሆነ በስተቀር ወሰን ይኑረው! ስሜታቹህን እና ፍላጎታቹህን ግልፅ አድርጉ!!!
"ሰው ሲጠላቹህ ብቻ ሳይሆን ሲወዷቹህም 'ለም?' በሉ!!"
.
.
.
አለም'ባንተ ናፍቆት ማገገሟን ካወቀ በኋላ በበነገታው በጠዋቱ ወደ ቤቷ አምርቶ ከወይዘሮ ሚሚ በማስፈቀድ ከቤት ይዟት ወጣ..ናፍቆት አብራው የመሆን ፍላጎት ባይኖራትም ከቤት መዉጣት ስለምትፈልግ አብራው ወጣችና ከቤት መራቋን እንዳስተዋለች አለም'ባንተን ጥላ በሩጫ ተፈተለከች..አለም'ባንተ ተደናግጦ ይከተላት ጀመር..ከብዙ ሩጫ በኋላ ከሰው አይን የራቀ ስፍራ ላይ ደረሰባትና ያዛት..ጮኸች እሪሪሪ አለች..በአማኑኤል ይዠሻለሁ ዝም በይ ተረጋጊ እያለ አረጋጋትና..
'ናፍቆትየ መሮጥ አይጠበቅብሽም እኔ የተሻለ ሃሳብ አለኝ!' አለና በወገቡ የያዘዉን ሽጉጥ አዉጥቶ ከራሱ ጭንቅላት ላይ ደቀነው..
.
.
.

..ይቀጥላል..

Aman YTZ
@amanYTZ23

join and share
@YelbeDrset
@YelbeDrset

inbox me @amanYTZ23
291 viewsAman YTZ, 15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 18:45:03 #ተከታታይ_ልብ_ወለድ_ታሪክ
.
.
.
.
#የኔ_ታሪክ!

ክፍል - ፴፬
.
.
..አማኑኤል ጎንደር ላይ ጎስቋላ ህይወት እየኖረ ፍቅሩን ሲጠብቅ..አንድም ቀን ተስፋ መቁረጥ ሳይሰማው ጎዳናውን ሲመለከት ሲያማትር ከረመ..ፍቅር ገጣሚ ያደርግ የል..የተለያዩ ግጥሞችን ይፅፋል..ግጥሞቹ ሁሉም ስለ ናፍቆት ብቻ ናቸው..
.
.
ሁሌ እንዳዲስ
ትመጫለሽ ብየ በሰፊው ጎዳና
መንገዱን ስጠርግ እዉላለሁ መንገዱን ሳቃና
ዝናብ ሲዘንብ ደግሞ ሰንጥቀሽው ትመጭ እንደው እላለሁ
የዝናብ ልብስና መጠለያ ይዤ መንገዱን አያለሁ
ደግሞ ጠራራዋ ፀሐይ በረድ እስክትል ሳትጠብቂ
ትመጭ ይመስል ድጋሚ ከኔ ጎን ላትርቂ
በተስፋ ታድሸ ሁሌ እጠብቅሻለሁ
ምን እንዳስነካሽኝ እኔስ ምን አዉቃለሁ
ብቻ የበጋዉን ወላፈን የክረምቱን ቸነፈር ሳትፈሪ
አምናለሁ ነገ ትመጫለሽ ዛሬ ብትቀሪ
.
.
እያለ ይገጥማል ቃላት ይሰድራል..ድምፁ ለማቀንቀን ባይመችም ያቀነቅናል..ብዙ ሙዚቃዎችን እየዘፈነ እራሱን ያሰቃያል! የድምፃዊ ግርማ ተፈሪን ዘፍን ይዘፍናል..
"ፈተና ሆኖብኛል ፈተናም ሆኖብኛል
በሄድሽበት ልሂድ ሳላይሽ ያመኛል!
እንኳን ሳቅ ጭዋታሽ ቁጣሽም ናፍቆኛል
ስትሄጂ የኔ አለም ከፍቶኛል..!
.
.
የኔው ስቃይ ይባል የታቀፍኩት
ይታመማል ባዳ ከነገርኩት
ርቀሽኛል ይህን አዉቃለሁ
ስከተልሽ ሁሌ እኖራለሁ..!
.
..እያለ ያለቃቅሳል..

ሙዚቃ እሳት ነው! በፍቅር ለተጎዳ ሰው ከጥቅሙ ጎዳቱ ያመዝናል ምክኒያቱም ወደ ፊት እንዲራመድ አይረዳዉም እዛው በትዝታና በናፍቆት ተጎሳቁሎ "ፍቅርሽ ነው የጎዳኝ!" እያለ እንዲኖር ያደርገዋል።

አማኑኤል ናፍቆትን ጎንደር ላይ ሁኖ ከሚጠብቅ ወደ ቀየው ተመልሶ ገንዘብ አሰባስቦ እርሷን ፍለጋ ለመዉጣት አሰበ።

የአማኑኤል እናት ወይዘሮ መብራቴ እጅጉን አዘኑ በልጃቸው ሁኔታ ተከፉ አሳድገው ተምሮ ስራ ይዞ ይጦረኛል ሲሉ ተጃጅሎ ቀረ..ሁሌ እየደወሉ ቢያለቅሱበትም የሸፈተው ልቡ የናትን አንጀት መረዳት አቃተው። የወላድ መካን የሆኑ ያህል ተሰማቸው!!
.
.
.
አለም'ባንተ ከናፍቆት ጋር ፍቅርን ባይጋራም በፈለገው ሰዓትና ቀን ማግኘትና አብሯት መዋሉ ደስተኛ አድርጎታል! ከኮነሬል ማንያዘዋል ጋር ጥሩ ቅርርብ መስርተዋል ኮነሬል ማንያዘዋል አለም'ባንተን ለናፍቆት ለመዳር ሃሳብ ይዘዋል። አመቱ እያለቀ መሆኑን ተከትሎ በጥምቀት ጥር ወር ላይ ሰርጉን ለማድረግ አለም'ባንተን አማክረው እርሱም ፍቃዱን ሰቷቸዋል። የናፍቆትን ምላሽ ግን ቦታ የሰጡት አይመስሉም።
.
.
.
አማኑኤል ከሶስት አመት በኋላ ወደ ቀየው ተመለሰ። ተቆራርሶ ተቆራርሶ ሽራፊ ቦታ ላይ ካረፈው የናት ቤት ሰተት ብሎ ገባ። ወይዘሮ መብራቴ ልጃቸው ይመለስ እንጅ በጣም አዝነዉበታል።

አማኑኤል ከሶስት አመት በኋላ አብሮ አደግ ጋደኛዉን ብሩክን ለማግኘት በአቅራቢያው ወዳለ ደብር አቀና..
.
.
.
አለም'ባንተ ከናፍቆት ጋር እንደተለመደው ወክ አድርገው ሲመለሱ የትዳር ጥያቄዉን ተንበርክኮ አቀረበላት..የናፍቆት ምላሽ ግን ጥሩ አልነበረም በተንበረከከበት እያለቀሰች ጥላው ሄደች..አለም'ባንተም የሆነዉን ለኮነሬል ማንያዘዋል ደዉሎ አሳወቃቸው። እርምጃ እንደሚዎስዱ እና ሃሳብ እንዳይገባው አስረግጠው ነገረሩት። አለም'ባንተ ናፍቆትን የግሉ ለማድረግ መጓዝ ያለበትን መንገድ ምንም ለናፍቆት ባይመቻት እንኳ እርሷን የግሉ ለማድረግ ጨቅኖ ተነስቷል።
.
.
.
ናፍቆት የአለም'ባንተን የትዳር ጥያቄ ስታስብ ወደ ጤናው ሳይመለስ የተለየችዉን ፍቅሯን እያሰበች አለቀሰች! አለም'ባንተ 'እንዴት ያለሁበት ሁኔታ አይገባዉም!' ብላ አዘነችበት። ስልክ ቢደዉልላት አትመልስለትም! ከቤት መቶ ሊያዎራት ቢሞክርም ፊት አትሰጠዉም።

ኮነሬል ማንያዘዋል ጣልቃ ገብቶ ከወይዘሮ ሚሚ ጋር በመሆን አለም'ባንተን እንድታገባው ግፊትና ጫና አሳደሩባት።
.
.
.
ብሩክ እና አማኑኤል አብረው ነው እሚዉሉ ሁለቱ ብቻቸዉን በሚህኑበት ጊዜያት አማኑኤል ያሳለፈዉን እና ያለበትን ታሪክ ለብሩክ ይተርክለታል። አልፎ አልፎም ታሪኩን ያገኙታል።

ታሪኩ የትምህርትን ሃሳብ እርግፍ አድርጎ ትቶ የመሳሪያ ንግድ ድለላ ጀምሯል። የተለያዩ ሰዎች ጋር ይተዋወቃል ከጎንደር ተመልሶ ሙሉ ጤናዎን ካገኘ ጀምሮ ጊዜ ሳያቃጥል ብዙ ስራዎችን ሰርቷል።

የመሳሪያ ሽያጭ ድለላ ከወቅታዊ የሃገሪቱ ጉዳይ ጋር አዋጭና አደገኛ ስራ ነው። ታሪኩ የተሻለ ኑሮ በሚባል ደረጃ ህይወቱን አቃንቷ ነው እሚኖር። አማኑኤልን እና ብሩክን በሳምንት ሁለቴ ወይ ሶስቴ ያገኛቸዋል እና አማኑኤል ከታሪኩ ጋር ስራ የመስራት ሃሳብ አቅርቦለታል ግን የስራዉን አደገኝነት በማሰብ አልቀበለው ብሏል። ይሁን እንጂ አማኑኤል ታሪኩን ባገኘው ቁጥር አብርሄህ ካልሰራው እያለ ይጨቀጭቀዋል። ብሩክ በዚህ ሁኔታ ደስተኛ ባይሆንም የአማኑኤልን ነገር በሙሉ ስለሚያዉቅ ለመከልከል አልሞከረም። ፍላጎቱ እያለን ምንም ነገር አለማድረግ! አመቻል! መቼም ስሜቱ ያስጠላል በጣም ነው እሚያስከፋ!

ጓደኛቹህ እምትዎዱት ሰው የሆነ ችግር ላይ ሁኖ እርሱን ለመርዳት ማድረግ እምትችልት ነገር የለለ ሲሆን ዝም ብላቹህ ማየትና መስማት ምርጫ የሌለው አማራጫቹህ ሲሆን ከባድ ነው።
.
.
.
ናፍቆት ደስታ እራቃት ቀን ከሌት ማማረር ስራዋ ሆነ። በተለይ ቤት ዉስጥ እሚደረገዉን የሰርግ ዝግጅት ስታይ ታግታ የምትኖር መሰላት። ቀኑ እየመሸ ለአይን ያዝ ሲያደርግ ባቅራቢያዋ ወደሚገኝ ቤተክርስቲያን አመራችና የዉስጠኛው በር ላይ ተደፍታ ንስሃ ይመስል በዉስጧ ያለዉን ሁሉ ዘክዝካ ተናዘዘች እስኪደክማት አለቀሰች! በመጨረሻም..'ፈጣሪየ ሆይ በቀኝህ አዉለኝ አቤቱን ይቅር በለኝ!' አለችና በያዘችው ስለት የደምስሯን ቆረጠችው..
.
.
.

..ይቀጥላል..

Aman YTZ
@amanYTZ23

join and share
@YelbeDrset
@YelbeDrset

inbox me @amanYTZ23
286 viewsAman YTZ, 15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 12:55:17 #ተከታታይ_ልብ_ወለድ_ታሪክ
.
.
.
.
#የኔ_ታሪክ!

ክፍል - ፴፫
.
.
.
"ህይወት ስቃይ ነው። ከባድ ነው። አለም የተረገመ ነው። ግን ቢሆንም፣ መኖርን ለመቀጠል ምክንያቶችን ታገኛላቹህ።"
.
.
..መልአክ ለአማኑኤል ደዉሎ ካለበት ሄዶ ሊያገኘው እንደሚችል በመግለፅ ወደ ቀበሌ ፲፬ አመራ። አማኑኤል በከርካሳ ዶርሙ ዉስጥ ኩርምት ብሎ በተቀመጠበት በራፍ ሲንኳኳ ተነሳ..መልአክ ነበር..መልአክ ወደ አማኑኤል ዶርም ዘልቆ ከአማኑኤል ጋር የመጠፋፋታቸዉን ያህል ተቃቀፉና ቁጭ አሉ። መልአክ ከየት እንደሚጀምር ግራ ስለገባው ዝም አለ። አማኑኤል እናቱ የሞተችበት ይመስላል፤ አንገቱን ደፍቶ ቁዝም ብሏል።

መልአክ ዝምታዉን ለመስበር ያህል ያልተገባ ጥያቄ ቢመስለዉም 'እና አማን እንዴት ነህ?' አለው..አማኑኤል መልአክን ቀና ብሎ አየና እንባ ካይኑ ፈሰሰ..
'ደና አይደለሁም! ህይወቴ ምስቅልቅል ብሏል! ደስተኛ መሆን አልቻልኩም! ፈተና አያጣኝም! እግዜሩም ትቶኛል! ምንም ነገር አይሳካልኝም..!' ሊለው ፈለገና መልሶ አንገቱን ደፋ..
መልአክ ናፍቆት የሰጠችዉን ወረቀት ከኪሱ አዉጥቶ..'አማን እኔ አንተን ማፅናናትም ሆነ ጥሩ እንዲሰማህ ማድረግ አልችልም ያለህበት ሁኔታ ከባድ እንደሆነ ቢገባኝም ግን አንተ ጠንካራ ነህ ትወጣዋለህ! ናፍቆት እንዳለችኝ አንተ ሁሉንም ነገር እንድትነግረኝ ብፈልግም ህመምህን ልጭርብህ ስለማልፈልግ ይቅር አትንገረኝ ይልቅ ይህን ወረቀት እንካ ናፍቆት ናት ስጠው ያለችኝ!' ብሎ እጁን ዘረጋለት..አማኑኤል መቀማት ያህል ከእጁ ነጥቆ ወረቀቱን ገለጠው..
.
.
.
ናፍቆት ዩኒቨርሲቲ ስትማርበት ወደነበረው ሃገር መመለሷ በጣም አሳሟታል! ማርታን ስታስታዉስ በሃገሩ ያሉ ነዋሪዎች ሁሉ እንደ አዉሬ ታዩዋት ጥላቻ አደረባት! ከአማኑኤል መራቋ ሳያንስ የጓደኛዋ እልፈት ሃገር ላይ መቀመጧ ክፉኛ አሳመማት.. ኮነሬል ማንያዘዋል ወደ አለም'ባንተ ደዉሎ ወደ ቤት ጠራው..

አለም'ባነተ የታመቀው ስሜቱ መልሶ ገነፈለበትና በርሮ ወደ ተጠራበት አመራ። በቦታው ደሬሶ ኮነሬል ማንያዘዋልን እና ባለቤታቸዉን ወይዘሮ ሚሚን ሰላምታ ከሰጠ በኋላ ወደ ናፍቆት ፊቱን መለሰ።

ናፍቆት ሶፋ ላይ ኩርምት ብላ ተጋድማ አልፎ አልፎ እንባዋ ይፈሳል። አለም'ባንተ ሰላምታ ሊሰጣት ቢሞክርም ምንም መልስ ስላሰጠችው ኮነሬል ማን ያዘዋልን እና ወይዘሮ ሚሚን እንዲወጡ ምልክት በመስጠት ከርሷ ጋር ብቻዉን ቁጭ አለ።

አለም'ባንተ የባጥ የቆጡን እያወራ ናፍቆት እንድትስቅ ወይ እንድታወራው ለማድረግ ቢጥርም አልሳካለት አለ። ምን ማድረግ እንዳለበት ሲያስብ ቆየና አማራጭ ስላጣ..'እሽ አማኑኤል እንዴት ነው? ዳነ ወይስ አልተሻለዉም!?' ሲላት ቀና ብላ አየችዉና ከተጋደመችበት ተነስታ አቅፋው ተንሰቅስቃ ታለቅስ ጀመር.. "የህመሙ መድሃኒት እዛው ህመሙ ላይ ነው!"
.
.
.
"የኔ ጌታ ይህን በምታነብበት ሰዓት እኔ ከዚህ ብዙ እርቄ እንደተጓዝኩ እወቅ። ላለመሄድ ማድረግ እምችለው ምንም ነገር ስላልነበር ያለ ፈቃዴ ካንተ እርቂያለሁ። የኔ ፍቅር እኔ ያለሁበትን አፈላልገህ ልትመጣ እንዳትሞክር! ነገሩ ይባስ ይከራልና..ደግሞ አታስብ እሽ ደና ነኝ! ጠብቀኝ አልልህም ሰው ስለነገ እርግጠኛ ሁኖ መናገር አይችልምና ብቻ እወቅልኝ.. "በልቤም ሆነ በአዕምሮዬ አፈቅርሃለው። እንዲያው ምንአልባት ልብም መምታቱን ቢያቆም አዕምሮም ቢረሳ። በነብሴ አፈቅርሃለው። ነብስ በፍፁም አትቆምም ወይም አትረሳምና።"

እራስህን ጠብቅ! እና ምን አልባት ሰው ወደ ህይወትህ ቢገቃ ተቀበል እሽ እንዳትገፋ..ደና ሁን..!"

አማኑኤል የናፍቆትን ደብዳቤ አንብቦ እንደጨረሰ ወረቀቱን አቅፎ አለቀሰ..በዉስጡ ግን ተስፋን ሞላ..
.
.
.
መልአክ ለአማኑኤል ማድረግ እሚችለው ነገር ቢኖር በእናቱ በኩል ስለ ናፍቆት በማጣራት ሁኔታዋን ማሳወቅ ነው። ይሁን እንጂ ናፍቆት በመልአክ እናት ስልክ ለአማኑኤል ከደህንነቷ በቀር ምንም ነገር እንዳይነግረው ቃል አስገብታዋለች። መልአክ የአማኑኤል ስቃይ እያየሁ ዝም ከምለው ባላገኘዉና ብርቀው ይሻላል በማለት ደብዛዉን አጠፋ..
.
.
.
ናፍቆት ከቤተሰቦቿ ጋር ከጎንደር ከወጡ ሳምንታት አለፉ..ወራት ተቆጠሩ..አማኑኤል ያሳደገችዉን እናቱን ዘንግቶ ጎንደር ላይ ያገኘዉን ስራ እየሰራ የናፍቆትን መመለስ ይጠብቅ ይዟል..

ናፍቆት ከቤት ወታ ባታዉቅም አለም'ባንተ እየተመላለሰ ያወራታል ያጫዉታታል..ትንሽ ዘና ማለት ይታይባት እንጂ አማኑኤል በሃሳቧ ሳያልፈ የተቆጠረ ሰከንድ እንኳ የለም!!

ከአማኑኤል ጋር ሳታወራ ሳታየው ሰባት ወራት ተቆጠሩ..ናፍቆት ድንገት ስሜቷ ግንፍል ሲል ቤት ዉስጥ ባገኘችው አጋጣሚ ለአማኑኤል ብትደዉልም ስልኩ አንስቶ 'ሄሎ' ከማለቱ ትዘጋበታለች..!
ናፍቆት ትሆን ብሎ መልሶ ሲደዉልም Blacklist ስለምታደርገው አይሰራለትም!
.
.
.
ናፍቆትና አለም'ባንተ የእግር ጉዞ ለማድረግ ፍቃድ ስላገኙ በከተማዋ ዞር ዞር እያሉ ማዉራት ጀመሩና..
'እሚረሳኝና ህይወቱን እሚቀጥል ይመስልሃል?'
'እኔ እንጃ እስካሁን ዝም ብሎ እሚቀመጥ አይመስለኝም!'
'እራስ ወዳድነት ሊሆን ይችላል እኔ ግን እንዲረሳኝ አልፈልግም ሌላ ሴትም እንዲለምድ አልሻም!' አይኖ እንባ አዘለ..
'እንግዲህ ሰው ይቀየራል በሰው ስሜት እርግጠኛ መሆን አይቻልም!'
'አንተ በሱ ቦታ ብትሆን ትረሳኛለህ!!??'
'አይ እኔ እንኳ አረሳሽም!'
'ለምን?'
'እንዴት መሰለሽ በቃ "በኔ አይኖች እራስሽን እንድታይው ማድረግ ብችል እና ባሳይሽ ይገባሻል አንች ለኔ ምን ያህል ልዩ እንደሆንሽ ታይም ነበር!"
.
.
.

..ይቀጥላል..

Aman YTZ
@amanYTZ23

join and share
@YelbeDrset
@YelbeDrset

inbox me @amanYTZ23
296 viewsAman YTZ, 09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 11:00:56 ////////////////////////

እንደምን አላቹህ ቤተሰቦች?!
.
.
.
እየተከታተላቹህት ያለው #ተከታታይ_ልብ_ወለድ_ታሪክ ትንሽ ስላመመኝ እስኪሻለኝና መፃፍ እስክችል ድረስ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ማለትም እስከ ዕለተ እሁድ ቀን ድረስ Season Break አድርጓል። ድርሰቱ ተፅፎ የተቀመጠ ቢሆን እያነሱ መለጠፍ አይከብድም ነበር ግን እዉነት ለመናገር እያንዳንዱን ክፍል በየቀኑ እየፃፍኩ ስለማጋራው ዛሬ ፅፌ ለመለጠፍ እራሴን ስላመመኝ ሃሳቤን መሰብሰብ ስላልቻልኩ በመጪው እሁድ ካቆመበት ክፍል ቀጥየ ለመፃፍ እሞክራለሁ። በአራቱ ቀናት ያንባቢያንን ሃሳብና አስተያየት እየተቀበልኩ መልስ እሰጣለሁ። በትግስት ለምትከታተሉ እና ጊዚያቹህን ሰታቹህ ለምታነቡልኝ ሁሉ አመሰግናቹሃለው።
እዚህ ላይ አንዳንድ ነገረኛ አንባቢ "ከታመምክ ይሄን ምክኒያት እንዴት ፃፍክ!" ይል ይሆናል! እና እኔ እንዳልፃፍኩት ወንድሜን አፅፌው እንደሆን ይታወቅልኝ!
.
.
ልጠይቁኝ እምትሹ ሰዎች አንድ ኪሎ የኢንተርኔት ጥቅል፣ ሁለት ኪሎ የድምፅ ጥቅል..በመላክ እግዜር በተሎ ያሽልህ! ማለት ትችላላቹህ!!
አድራሻየ፦ @amanYTZ23 ነው።

መልካም ቀን!


@YelbeDrset
@YelbeDrset
@amanYTZ23
392 viewsAman YTZ, 08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 13:16:13 #ተከታታይ_ልብ_ወለድ_ታሪክ
.
.
.
.
#የኔ_ታሪክ!

ክፍል - ፴፪
.
.
.
"..ተያት ይች አለም ለሐቅ የላትም ዳኛ፣
ልክ ባንሆንም ልክ ነን እኛ!"
.
.
..ናፍቆት እንባዋ ቀስ እያለ በጉንጯ ወደ ትራሱ እየወረደ አልጋዋ ላይ ጋደም ብላለች። የናፍቆት እናት የልጃቸዉን መጎሳቆል አይተው ቢከፉም የተወሰነው ዉሳኔ ለወደፊት ህይወቷ ጥሩ እንደሚሆን በማሰብ ዝም ብለው ቁጭ ብለዋል።
.
.
.
ኮነሬል ማንያዘዋል እና አማኑኤል የነዳጅ ማደያው አካባቢ ከባጃጅ ወርደው ትንሽ ከተራመዱ በኋላ አዲስ ምሪት የተመሩ ሰዎች ወደሚሰሯቸው ቪላ ቢቶች ተጠግተው ቁጭ አሉ።

ኮነሬል ማንያዘዋል ሊሰድቡትና ሊጮሁበት አስበው የነበረዉን ናፍቆት ከተናገረቻቸው መካከል.."አፍቅረህ አታዉቅም!?" ያለቻቸው በሃሳባቸው ዉልብ አለና መንፈሳቸው ሰከን አለ።
ጉሮሯቸዉን ጠረግ ጠረግ አደረጉና 'ይሄዉልህ አንተ ገና ታዳጊ ልጅ ነህ! ካንተ እኔ ብዙ ነገርን አይቻለሁ አሳልፊያለሁ! እና ልጄ ስላተ እምትለው እዉነት ቢሆን አንተም እዉነተኛ ፍቅር ቢኖርህም የኔን ብቸኛ ልጅ ላንተ አሳልፌ መስጠት አልችልም! የወጣትነት ፍቅር ሁላችንም አልፈንበታል! ከፍ ስትልና ልጅ ስትወልድ ትረዳኛለህ../'

ወሬአቸዉን አቋርጠው አማኑኤል አዩት አንገቱን ደፍቶ እያዳመጣቸው መሆኑን አስተዋሉና ቀጠሉ..'ገና ተማሪ ነህ! ቤት የለህም! ስራ የለህም! ከገጠር እንደመጣህም ሰምቻለሁ! እና በዚህ ሁኔታ ልጄን እንዴት አድርገህ ልታኖራት አስበህ ነው!? ይህንን ብቻ መልስልኝ!?!' አሉት..አማኑኤልም ቀና ብሎ አያቸዉና 'ለዚህ ጥያቄዎ መልስ እንደሌለኝ ያዉቃሉ! የቤተሰብ ሐብት ወይ ዉርስ የለኝም ገና ተማሪ ነኝ! ግን ልጅዋትን ከነብሴ አፈቅራታለሁ ከልቤ እወዳቲለሁ እና እሷን ደስተኛ ለማድረግና እርስዎ ይገጥማታል ብለው የሰጉትን ህይወት ሳታይ እንድትኖር ለማድረግ እኖራለሁ! ይሄን ብቻ ነው ልልዋ እምችል!!' አላቸው ፈርጠም ብሎ..

ኮነሬል ማንያዘዋል በትዝታ ወደ አለፈው ህይወቱ ቃኘት አድርጎ ተመለሰና የልጁን እና የአማኑኤልን ሁኔታ አሰበ..'ይሄዉልህ ገና ወጣት ስለሆንክ ልጄን እረስተህ ሌላ ሴት ለማፍቀር ጊዜ አለህ ስለዚህ ልጄን እርሳት! ከነገ ጀምሮ በዚህ መኖርን እናቆማለን ሐገር ልንለቅ ነው! በምንሄድበት ሐገርም ለርሷ እሚሆናትን እኔ ፈልጌ አጋባታለሁ! አንተም የራስህን ፈልግ! እንዲህ ተረጋግቸ የማወራህ እኔም አፍቅሮ ማጣትን ስለማዉቅ ነው! ከዚህ በኋላ ግን ከልጄ ራቅ ዝንቧን እንኳ እሽሽ እንዳትል! ብቸኛዋ ልጄ ካንተ ጋር ስታክ ማየትን አልሻም! የተደላቀቀ ህይወትን እሚሰጣት ጋር ነው መኖር ያለባት! አይ አልሰማም ካልክ ግን ዉርድ ከራስህ መላ ህይወትህን ነው እማበላሸው ነግሬሐለው!!' አሉት የተረጋጋው መንፈሳቸው እየታወከ..

አማኑኤል ወደ ኮነሬል ማንያዘዋል ላይ አፍጥጦ 'ምን አልባት እኔ የገንዘብ ደሃ ልሆን እችላለሁ እርሶ ግን የአስተሳሰብ ደሃ ነዎት! በጭራሽ ደግሞ ከኔ ይልቅ ብዙ ነገር አላሳለፉም አላዩምም! አሳልፈዉም ከሆነ ካሳለፉት ህይወት የተማሩት ይሄን ከሆነ የባከነ የህይወት ትምርህት ነው ያሳለፉት! እኔን እንዳሻዋ ማድረግ ይችላሉ ግን ቃል እገባልዎታለሁ ልጅዋትን የትም ብትሆን ፈልጌ የራሴ አደርጋታለሁ!!' አላቸው ደሙ ፈልቶ የመጣው ይምጣ በማለት.. ኮነሬል ማን ያዘዋል ከተቀመጡበት ተነሱና በለበሱት ከስክስ ጫማ አማኑኤል ፊት ላይ አሳርፈው አሽቀነጠሩትና..'ደሃ የደሃ ልጅ እንዴት ብትደፍር ነው እንዲህ እምትናገረኝ እንዲያዉም ከልጄ መድረስ ቀርቶ እርሷ ባለችበት ሃገር ካገኘዉህ እገድልሃለው!!' አሉትና የመጡበትን መንገድ ይዘው መሄድ ጀመሩ..

አማኑኤል ከወደቀበት ተነስቶ ድምፁን ከፍ አድርጎ..'የህዝብ ደህንነት እና ህይወት ጠባቂ ሁነው የኔን የወጣቱን ህይወት እንደነጠቁኝ መቼም እንዳይረሱ!!' አላቸው..ኮነሬል ማንያዘዋል ግን ወደ ኋላ ዞር ብለው ሳያዩ ሄዱ..

አማኑኤል ጉትትት እያለ ወደ ሎዛ ማርያም ቤተክርስቲያን ገብቶ ዋናው በር ላይ በጉልበቱ ተንበርክኮ ተደፋ አይኑ እንባ ሞላ..ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ..እራሱን ጠላ..ድሃ መሆኑ ያሳጣዉን ፍቅር ሲያስብ መፈጠሩ አስጠላው በራሱ አዘነ..!! ስለናፍቆት አሰበ ምን እንዴት ሁና ይሆን ብሎ ተጨነቀ..በርሱ ድህነት ምክኒያት እርሷም ባልፈለገችው መንገድ ልትኖር መሆኗን ሲያስብ በራሱ ተናደደ ግፍ የሰራባት ያህል ተሰማው..እዚያ ከቤተክርስቲያኗ ኩርምት ብሎ ቁጭ አለ..
.
.
.
መልአክ ከማርታ እልፈት በኋላ እራሱን መሆን አልቻለም። ከቤተሰቡ ጭምር ገለል ብሏል ቅዳሜና እሁድ ለይስሙላ ግቢ ይሄዳል ይመለሳል..ከሰኞ እስከ አርብ ፀበል ይጠመቃል..ቤተክርስቲያን ዉስጥ እሚሰጡ ትምርቶችን መከታተል ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ ከቀን ቀን እየተሻለው መቷል..የተለያዩ መጽሐፍትንም በማንበብ እራሱን መገንባት ጀምሯል..ህይወትን ባቆመባት መቀጠል እንዳለበት በማሰብ እንዳዲስ 'ሀ' ብሎ ጀምሯል..
.
.
.
ናፍቆት አማኑኤል ልታገኝ እምትችልበት ሁኔታ እንደሌለ ስላወቀች ወረቀትና እስክርቢቶዋን አገናኝታ አጭር ደብዳቤ ቢጤ ፅፋ በጡት ማሰሪያዋ ዉስጥ አስቀመጠች..
.
.
.
መልአክ በለሊት ቤተክርስቲያን ተሳልሞ ከእግዜር ሰላምታ በቀር መቅረቡን የነሳቸዉን ሰዎች በማሰብ ወደነ ናፍቆት ቤት አቀና..በቦታው ሲደር የናፍቆት እናት ጎረቤቶቿን እየተሰናበተች ናፍቆት አንገቷን ደፍታ ቁማ ኮነሬል ማንያዘዋል ወዳዘጋጀው መኪና እቃ እየጫነ ደረሰ..ግራ ገብቶት ወደ ናፍቆት ተጠጋና 'ትንሿ ምን ተፈጥሮ ነው የት ልትሄዱ ነው?!' አላት..ናፍቆትም በሃይል አቀፈችዉና አለቀሰችና ደብዳቤዉን ብጁ እያስጨበጠች ሁሉንም ነገር አማኑኤል ይነግርሃል ይችን ብጣሽ ወረቀትም ለርሱ ስጥልኝ አለችው.. መልአክ የመናገር እድሉን ሳያገኝ ናፍቆት ወደ መኪና ገባች..በመኪናው መስኮት እጇን እያንቀሳቀሰች "ቻው!" አለችው..መልአክ "ቻው!" እሚለዉን ቃል ሲሰማ ደነገጠ ነገሩ የከረረ መሆኑ ተረዳ..እጁን እያዉለበለበ "እንገናኛለን!" አላት..
.
.
.
አማኑኤል በርቀት ከፍ ያለ ቦታ ሁኖ ከካምፕ የወጣችዉን መኪና አየ..እየሮጠ ለመድረስ ሞከረ ግን አልቻለም..ሄደች..ከርሱ እራቀች..የመንገዱ ዳር ላይ ተዘርሮ አለቀሰ..ልቡን ቅዝቃዜ ተሰማው..ነብሱን ጨለማ ዋጣት..
.
.
.
"መለያየት ሞት ነው ለተዋደደ ሰው..!"
.
.
.

..ይቀጥላል..

Aman YTZ
@amanYTZ23

join and share
@YelbeDrset
@YelbeDrset

inbox me @amanYTZ23
341 viewsAman YTZ, 10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 13:08:23 join and share
@YelbeDrset
@YelbeDrset

inbox me @amanYTZ23
285 viewsAman YTZ, 10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 13:07:51 #ተከታታይ_ልብ_ወለድ_ታሪክ
.
.
.
.
#የኔ_ታሪክ!

ክፍል - ፴፩
.
.
.
..አማኑኤል የሚከራይ ቤት ባለማግኘቱ ሶስት ቀን አልጋ ለማያዝ ተገደደ.. እንደፈለገው ተንቀሳቅሶ ክራይ መፈለጉ ከባድ ስለሆነ ለደላላዩች ማስፈለጉን ቀጠለ.. ወይዘሮ መብራቴ ከወጭ አንፃር እና አሁን ስለተሻለው እራሱን እንደሚንከባከብ ነግሯት ወደ ቀየዋ እንድትሄድ አሳመናትና ሳትፈልግ ሄደች።

ወይዘሮ መብራቴ ከጎንደር በወጣች በሰልስት ቀኗ አማኑኤል ቀበሌ ፲፬ ዉስጥ ቆርቆሮ በቆርቆሮ የሆነች ለጭስ ቤት ታስባ የተሰራች ዶርም አጊንቶ ተከራየ..የዩኒቨርስቲ ትምርቱንም ባፃፈው የህክምና ማስረጃ በማቅረብ ዊዝድሮ ሞላ..ጎንደር ላይ ያቆመዉን ህይወት ቀጠለ..

ናፍቆት ከእጅ የወጣች አፈንጋጭ ሁናለች..ከቤት ስትወጣ ማንንም አታስፈቅድም ዝም ብላ ጥወጣለች ዝም ብላ ትገባለች..ከአማኑኤል ጋር እንዳድስ ተዋዉቀው ጓደኞች ሁነዋል በቀን አንዴ ሳታየው አትዉልም። እረሳሁሽ ቢላትም እንዲያስታዉሳት ሳትጎተጉት እንዳዲስ ፍቅር ልታሳድርበት እየጣረች ነው። አማኑኤል በበኩሉ ሁሌ እንዳዲስ ነው በፍቅሯ እሚዎድቅ..

ቀኖች ነጉደው ሳምንታት አልፈው ክረምቱ አለቀ አዲስ አመት ብቅ አለ። ወይዘሮ መብራቴ አዲስ አመትን ከልጃቸው ጋር ለማሳለፍ ጎንደር ተከሰቱ..አዲስ አበባ እያሉ ጀምረው በቀያቸው እሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ቦታዉን ሸንሽነው ሸንሽነው ለጎረቤታቸው ሽጠው ጨረሱት..ቤቱ ካረፈበት ቦታ ዉጭ መላ ግቢው በአቶ አለማየሁ ስም ሆነ..

አዲስ አመት በተርካሳዋ የቆርቆሮ ቤት በጥሩ አለፈ..ወይዘሮ መብራቴ ናፍቆት ከልጃቸው ለማራቅ ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ስለተገነዘቡ ችላ አሏት። ናፍቆት ከአዘዞ አንስታ ወደ ቀበሌ ፲፬ ያለዉን መንገድ ቢያን አንዴ ትመላለስበታለች። አማኑኤልም ይሄን ሁሉ በማየት እዉነቱን ሊነግራት ቀን ቀጥሮ ምቹ ሁኔታን ይጠብቅ ጀመር።

ወይዘሮ መብራቴ ለአዲስ አመት ብለው ጎንደር ቢመጡም በዛው የስቅለትን በዓል አክብረው ወደ መጡበት ተመልሰው ሄዱ..

ጥቅምት ወር መግቢያ ቀኖች ላይ አማኑኤል ለናፍቆት ደዉሎ ወደ ዶርም እንድትመጣና እሚነግራት ትልቅ ነገር እንዳለ አሳወቃት። ናፍቆትም በደስታ ተሞልታ ተስማማች። ቀጠሯቸው ለከሰዓት ስለነበር ናፍቆት ረፋዱ ላይ ምሳዋን በልታና ልብስ ለባብሳ ትጠባበቅ ጀመር። አማኑኤልም በበኩሉ አንድ ወይን ገዝቶ የወይን መጠጫ ከአከራዮቹ ለምኖ ያችን ተርካሳ ዶርም አፀዳድቶ እየጠበቃትነው..

ሰዓቱ ልክ ሰባት ተኩል ሲል ናፍቆት ከተቀመጠችበት ተነስታ ልትወጣ በሩ ላይ ስትደርስ የት እንዴት እንደመጣ ያላየችው አባቷ ኮነሬል ማንያዘዋል ከፊቷ ድንቅር አለ።
.
.
.
አማኑኤል የእጁን ሰዓት እና የስልኩን ሰዓት እያፈራረቀ ያያል..ዘገየች..በጣም ዘገየች..የስልኩን ቁልፍ ነካክቶ ደወለ ስልኳ አይነሳም..ደጋግሞ መደወሉን ቀጠለ..አይነሳም..ጭንቀት ዉስጥ ገባ እሚያደርገው ቅጡ ጠፋው..
.
.
.
ናፍቆት እንደሞት ጣረሞት ከፊቷ የተደነቀረው አባቷ አስደንግጧት ወደ ኋላ ሸሽታ ዘፍ ብላ ቁጭ አለች..ኮነሬል ማንያዘዋል አይኑን አፍጥጦ 'ወደየትም መሄድ አትችም! ማንንም ማግኘት ሆነ ስልክ ማዉራት አትችይም አርፈሽ ቁጭ በይ!' አለና የእጅ ስልኳን ቀማት..

ናፍቆት አይጥ እንደዋጠች ድመት ዝም አለች። አባቷ ሌላ ሰው ሁኖ ታያት እጅግ ፈራችው። ኮነሬል ማን ያዘዋል ወንበር ስቦ ከናፍቆት ፊት ለፊት ቁጭ አለና ምሬት የቀላቀለ ቁጣ አወረደባት..
'እንዴት ብትበላሽ ነው ከቤተሰቦችሽ ፍቃድ እንዲህ የተንዘላዘልሽ ለዱርየ ብለሽ ስንት መከራየን አይቸ አሳድጌሽ ያዋረድሽኝ! ለነገሩ አንች ጋር ንግግር ምንም ጥቅም የለዉም! እማደርገዉን እኔ ነኝ እማውቅ! አሁን የልጁን አድራሻ ብቻ ንገሪኝ!?!' አላት..

ናፍቆትም በመንተባተብ..'አ..ባየ ይሄዉልህ እ..መጀመሪያ ተረጋጋ..ልጁ ምንም አላደረገም እኔ ነኝ ወደርሱ እየሄድኩ ካልወደድከኝ እያልኩ እማስቸግረው! እባክህ አባየ እርሱን ምንም ነገር ለማድረግ እንዳትሞክር እኔ ያልከኝን ሁሉ አደርጋለሁ!' አለችው እንባዋ ካይኗ አልፎ መሬት ላይ እየተንጠባጠበ..'ኧረ እንደዛ ነው! ጭራሽ ትከላከይለታለሽ!? ጥሩ እሽ! እስካሁን ካደረግሽው አንፃር እንዲህ እንደሚፈጠር አስቤው ነበር! ሁሉም ነገር እዚህ ላይ ያበቃል! በከረምኩበት ሃገር ቤት ገዝቻለሁ ከነገ በኋላ ወደዛ እንሄዳለን ካሁን በኋላ እዚህ ምንም አናደርግም! እናትሽም በሃሳቤ ተስማምታለች! ለኔም ከጎኔ መሆናቹህ ጥሩ ነው! አንችም ትምርትሽን ትቀጥያለሽ! አንዷ ልጄ ስትበላሽማ ዝም ብየ አላይም! በይ ማልቀስሽን አቁሚና ልብስሽን ሸካክፊ!!'
'ምን..የምርህን ነው አባ..ኧረ ተው እንዲህማ አታድርግ! በቃ እኔ ወደ እርሱ አልሄድም! ከዚህ ግን አታርቀኝ! ክባክህን አባየ ይቅርታ አድርግልኝ! ፍቅር ይዞኝ ነው! ከአቅሜ በላይ ነው! ከአማን ይሄን ያህል እርቄ መኖር አልችልም! እባክህ ተረዳኝ! በጣም ጨካኝ ነህ! አፍቅረህ አታዉቅም!!!' የልቦን ሁሉ አዉጥታ ጮኸችበት..

ኮነሬል ማንያዘዋል ለመጀመሪያ ጊዜ እጁን አንስቶ ናፍቆትን ፌንት በሚያሰራ እጁ በጥፊ መታትና..
'ኧረ ጥሩ ምላሰኛ ወቶሻል ጭራሽ ትመልሽልኛለሻ..ጥሩ በዉሳኔየ ጭራሽ እንደማልቆጭ ነው ያረጋገጥሽልኝ! ደግሞ በዚህ እድሜሽ ስለ ፍቅር ታወሪያለሽ!! ወይኔ ማንያዘዋል ከሰርኩ ተዋረድኩ!!' ብሎ ቀጥጣ የልብስ ሻንጣዋን አንስቶ ልብሶቿን ማስገባት ጀመረ..ናፍቆትም ጉንጯን ይዛ እያለቀሰች ትለምነው ጀመር..

የናፍቆት እናት ከጎረቤት ቆይታ ስትገባ አባትና ልጅ እየተጨቃጨቁ አገኘቻቸዉና..በመደናገጥ ዘለው ባለቤታቸዉን እጅ ይዘው ናፍቆት እንዳይመታት ተከላከሉት..'ምንድን ነው ምን እያደረክ ነው! ልጄ ላይ እንዴት እጅህን ታነሳለህ!' አሉት.. ኮነሬል ማንያዘዋልም..'አንች ነሽ ለዚህ ሁሉ ምክኒያት በስርዓት ያሳደኳትን ልጄን እንዲህ ያበላሸሻት!! አሁን ቀጥታ እቃቼን ሸካክፈን ነገ በጥዋት ከዚህ ለቀን እንወጣለን!!' አላትና ቀድሞ ሁሉንም አብረው ስላቀዱ ዝም አለችው እና ናፍቆትን ወደ ማረጋጋት ገባች..
.
.
.
አማኑኤል በጣም ተጨነቀ እና ተርካሳዉን ዶርም ቆልፎ ወጣ..የምስራች አካባቢ ታክሲ ጠበቀና ወደ አዘዞ ተፈተለከ..

ኮነሬል ማን ያዘዋል የናፍቆት ስልክ ላይ ደጋግሞ ሲደወል የነበረዉን ስልክ ወደራሱ ስልክ ገልብጦ ደወለ..ስልኩ ከዛኛው ጫፍ ተነሳ..
'ሄሎ?'
'ሄሎ የአማኑኤል ስልክ ነው?'
'አዎ ነው! ማን ልበል?'
'የናፍቆት አባት ነኝ! ናፍቆት ትንሽ ስላመማት እና ልታይህ ስለፈለገች ወደ አዘዞ መምጣት ከቻልክ ብየ ነበር!' አለው እንደምንም ቁጣና ንዴቱን ተቆጣጥሮ በማስመስል..አማኑኤል በጣም ግራ ቢገባዉም እና የሰማዉን ለማመን ቢከብደዉም..'እሽ እየመጣሁ ነው መንገድ ላይ ነኝ!' ብሎ ስልኩን ዘጋው..

ኮነሬል ማንያዘዋል አማኑኤልን ሲያገኘው ምን እንደሚያደርገው ሲያወጣ ሲያወርድ ቆየና አማኑኤል አዘዞ መድረሱን ደዉሎ ሲያሳዉቀው ከካምፕ ወጣና በሩ ላይ እንዲመጣ ነገረው..አማኑኤል ፈራ ተባ እያለ ኮነሬል ማንያዘዋልን አገኛቸዉ..

ኮነሬል ማንያዘዋል አይናቸው ደም መስሎ የዉሸት ፈገግታ ፊታቸው ላይ ለጥፈው አማኑኤልን ሰላምታ ሰጡትና ትከሻው ላይ እጃቸዉን ጣል አድርገው 'ናፍቆትን ከማግኘትህ በፊት እስኪ እኔ እና አንተ እናዉራ!' አሉትና ባጃጅ ይዘው ወደ 'አጣጥ' መስመር የሚወስደዉን መንገድ ይዘው ሄዱ..አማኑኤል ልቡ በፍጥነት እየመታ ፍራት እየተሰማው ነገሩ ቢጨንቀዉም ምንም ማድረግ አልቻለም..
.
.
.

..ይቀጥላል..

Aman YTZ
@amanYTZ23
285 viewsAman YTZ, 10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ