Get Mystery Box with random crypto!

የ ቃል ደብዳቤዎች💌

የቴሌግራም ቻናል አርማ yekaldebdabewoch — የ ቃል ደብዳቤዎች💌
የቴሌግራም ቻናል አርማ yekaldebdabewoch — የ ቃል ደብዳቤዎች💌
የሰርጥ አድራሻ: @yekaldebdabewoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 530
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ላይ 👇
ደብዳቤዎችን💌
ወጎችን📃
ግጥሞችን📝
የተለያዩ መፅሐቶችን📚 ያገኛሉ፡፡
ሀሳብ, አስተያየት እንዲሁውም እንዲለቀቅላችሁ የምትፈልጉት ደብዳቤ ካለ
@Hebestina ይላኩልን፡፡ ቻናሉ ላይ እንለቃለን...

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

3

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-08 21:15:47 ጎረቤታችን ናቸው። አለም ለእነሱ መዋደድ ግድ የሚሰጠው ይመስላቸዋል ወይ ሰው ባለበት ለፍቅራቸው ምስክርነት መናገር ፍቅር ያጠናክራል የሚል እውቀት ጭንቅላታቸው ውስጥ ሰርጿል ።
እንዴት እንደሚከባበሩ ፣ እንደሚዋደዱ አንዳቸው ለአንዳቸው ስጦታ እንደሆኑ በሆነ ምክንያት ሰብሰብ ስንል መዘብዘብ ይጀምራሉ። የልጃቸውን ልደት አዘጋጅተው ማታ ከቤርሳቤት ጋ ሄድኩ ፤ ጥሩ ሰዎች ስለሆኑ እና ቤርሳቤት ማህበራዊ ህይወት ስለምትወድ ሄድን ። የተገናኙበትን እለት ለዘጠነኝ ጊዜ ሳያዛነፍ ሳይጨመር እየተቀባበሉ ተረኩልን ። ለዘጠነኛ ጊዜ ሰምተነዋል ሳንል ሁሌም ሲነግሩን የምንጠይቀውን ጥያቄ የምናጨበጭበውን ጭብጨባ አጨበጨብን ።
ድንገት እናንተ የት ነው የተገናኛችሁት አለችን ኤልሳ ። ከቤርሳቤት ጋ ተያየን። ፈጠን ብዬ ፦ አዳማ የ leadership ስልጠና ስሰጥ ቢሮዋ ወክሏት ሰልጣኝ ነበረች ። ተከይፌባት በሰበባ-ሰበብ ስልኳን ተቀበልኩ ። ደጅ ጠንቼ እትት ብዬ ይሄው አንድ ልጅ ወለድን
አልኩኝ፤ አለቀ። ውሸት ብዙ አይጎተትም ብዙ ካልተጠና በቀር ቤርሳቤት ዝም አለች።
የአወራሁት ውሸት ነበር ። ለካ ሁሉ እውነት አይወራም ። ለካ የሚከደን ገጠመኝ አለ። ለካ ለራሳችን ደግመን የማንነግረው የሚጎመዝዝ እውነት አለን። እውነታው ፦ ከቤርሳቤት ጋ የተገናኘነው ጭፈራ ቤት ነው የተገናኘን ቀን ነው የተናፋነው ፤ ወሲባችን ፍቅር አልነበረውም ፤ ከአንድ ዙር መፋተግ በኋላ፤ አንድ ዙር ፍቅር አልባ ወሲብ እንዳለቀ ፊቴን አዞርኩ ሲጋራዬን ለኮስኩ ፤ ፊቷን አዙራ ስልኳን መነካካት ጀመረች ። ሁለታችንም ጀብረር ብለን ነበር። ምንም ያላወራው ይመስለኛል ፤ እርግጠኛ ነኝ ከዚህ በኋላ አንገናኝም ፤ በአንድ ቀን የምትጋደም ፣ ከሴተኛ አዳሪ ገንዘብ ባለመቀበል ብቻ የምትበልጥ ወይም የምታንስ ልጅ ማን ቁምነገር ይሰጣታል። አስክሮ ፣ እትትት ብሎ የሚቾምስ አለሌ ሸሌ ወንድ ለቁምነገር እንደማይሆን እርግጥ ነው። ተኛን !
ሳንተቃቀፍ ተኛን።
እኩለ ለሊት እንዳለፈ ይመስለኛል አመመኝ ከተኛሁበት አልጋ ተስፈንጥሬ ከአልጋዬ ብዙ
ሳልርቅ ወለሉ ላይ አስመለስኩ ።
ከመቅፅበት ተነስታ ከጎኔ መጥታ ልቤን ያዘችልኝ ፤ ከሆዴ ጀምሮ አማጥኩኝ ፣ አማጥኩኝ አቅም አነሰኝ እና ጥምልምል አልኩ ፤ መታገል ፣ ማጓራት ብቻ የሚወጣ ግን የለም ውሃ ጠጣ ብላ ሰጠቺኝ ፤ ትንሽ ጠጣሁ አፍታ ሳይቆይ የጠጣሁትም ውሃ ወጣ ። ቀና በል ፥ ይሸትኻል አለቺኝ ፤ ትውከቱ እንዳይሸተኝ ቀና እያደረገችኝ ፤ እሷን ተደግፌ ቀና አልኩ ጨርቅ አምጥታ (ከውስጥ የለብስኩትን ቦዲ) ውሃ ነክራ አንገቴን ፣ ግንባሬን አራሰችልኝ ፤ ቅዝቅዝ አለኝ ። ቀስ ብዬ ጠቅልል ብዬ ተኛሁ ፤ ስትንጎዳጎድ እንቅስቃሴዋ ይሰማኛል ፤ አቅሜ ተዳክሞ ስለነበር ለጥ አልኩ ። ጠዋት ስነቃ እና ማታ የሆነውን ሳጤነው ሁኔታዋ እና እንክብካቤዋ አንጀቴን በላው።
ትውከቴ ከቦታው የለም ፤ እንዴት አልተፀየፈችውም ፤ ማን ስለሆንኩ አንደዚህ
ተንከባከበቺኝ ?! አብረን ቁርስ በላን ። ስለማታው ሁኔታ ምንም አላወራንም ፤ አፈርኳት ፤ ውለታዋ ቆጠበኝ። ከዛ ቀን በኋላ አብረን ነው የምንውለው። ተልካሻ ስፍራ ፤ በማይረባ ሁኔታ እንዴት እንደዚህ ግጣሜን ላገኝ ቻልኩ ።
በሁለት ወር ከአስራምስት ቀን ዳግም ለሁለተኛ ቀን ተዋሰብን ፤ ያኔ ሰውነቴ ተቀብሏት
ነበር ፤ ሰውነቷ ተቀብሎኝ ነበር እናም ተዋሃድን ፤ የሚዋደዱ ሰዎች ሲዋሰቡ ወሲቡ
ውህደት ነው ፣ የነፍስ ቁርኝት ፤ ተቆራኘን።
ውድ ቦታ እና ቅዱስ ቦታ ብቻ ነው ትክክለኛ ሰው የሚገኘው ያለው ማነው? ህይወታችን የሚመዘነው በምናገኘው ደስታ ነው ።
ዛሬ አምናታለሁ ! የምትንዘላዘልበትን ምክንያት ደፍኜዋለሁ ፤ ፍቅሬ እንድትታመነኝ ሰርቷታል
። እንደትላንት እንዳልሸረሙጥ ከእሷ ጋ ያለኝ ነገር ይጋርደኛል ። ሰው መቼ በተገናኘበት ስፍራ ብቻ ይመዘናል ፤ ያለንበት ስፍራ ሁሌ መቼ ልካችን ሆኖ ያውቃል። አጀማመራችን ሳይሆን አካሄዳችን ነው የማንነታችን ማሳያ ። ይሄ በልባችን የተፃፈ የምንኖረው እውነት ነው ። ይሄን እውነት መግለፅ ረብ ለሌለው ትዝብት መጋለጥ ነው። ሁሉ እውነት አይነገርም። አንዳንዴ አንዳንድ ውሸት ከእውነት ይበልጣል ።

#Adhanom Mitiku

@yekaldebdabewoch
289 viewsKal--kidan, 18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 09:30:31 አሞኛል ብዬም አላሰብኩም
ብቻ እንደው ደና አይደለሁም
ልቤ አንድ ነገር ይሰማኛል
አንተን ሳስብህ ይጨንቀኛል


@yekaldebdabewoch
306 viewsHáŷmî, 06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 17:24:14 ሶፊያ ትባላለች የቀድሞ ፍቅረኛዬ ነበረች። ከተለያየን በጣም ብዙ ጊዜ ሆኖናል። እጅግ ከብዙ ጊዜ በኋላ ተደዋውለን ሻይ እየጠጣን ነው። በጨዋታችን መሃል ድንገት ለምን ግን ያኔ ተውሺኝ አልኳት ። ሳቀች ፤ ስትስቅ አይኗ ይጨፈናል ። ሰላማዊ በሆነ አስተያየት ካለምንም ወቀሳ መልሷን እየጠበኩ እንደነበር የተረዳች መሰለኝ ከሳቋ መልስ "እውነቱን ለመናገር ያኔ መተው ነበረብኝ ፤ ያን ውሳኔ የወሰነችው የድሮዋ ሶፊያ ናት"። አብራሪልኝ አልኳት ከስስ ፈገግታ ጋር ፊቴን አኮስኩሼ "ጭንቅላትህ ምክንያታዊ ሃሳብ አያፈልቅም ነበር ። የማይጥምህን ሃሳብ ፤ ያልወደድከውን አቋም ነፍስህ ተረጋግታ አትሰማም ። አንተ ያልፈለከው ካልሆነ ፤ ነፍስህ ትቅበዘበዛለች ሁሌ ከአንተ የፈለቀ ሃሳብ ትክክለኛ እና አዳኝ ይመስልሃል። Soft dictator ነህ ። አምባገነንነትህ በፍቅር ስለምትሸፋፍነው እና
ያፈጠጠ ስላልሆነ በቀላሉ አይገለጥም ።
ፍቅርህ እጅ መንሻህ ነበር መከራከርያ፤መደራደርያህ፤ማፅናኛህ ፤መፅናኛህ ፍቅር ነበር ። ፍቅር ከእውነት የሚበልጥ ይመስልሃል። አንዳንዴ ፍቅር ፤ አንዳንዴ እውነት እንደየሁኔታው እንደሚበላለጡ አልገባህም ።
በበነነው በተነነው ትቀናለህ ፤ እንዳላየህ የምታልፈው ነገር የለም። ሰው ደሞ ብስለቱ
የሚለካው እንዳላየህ በሚያልፈው እና እያወቀ በሚተወው ልክ ጭምር ነው። ስሜትህን ሆነ አስተውሎትህን አሁንም አሁንም ታንፀባርቃለህ። ከፍተኛ የሆነ Emotional intelligence ይጎልህ ነበር ። በዚህ ሁሉ መሃል አንደ አሁን ብስለት መገለጫ ባይሆን ራሱ በአሁን ማስተዋሌ በጭራሽ አልተውክም ነበር። አየህ ያኔ ሙሉ ሰው ፍለጋ ላይ ነበርኩ። ሙሉ የሚባል ሰው አለመኖሩን ለመረዳት ከብዙ ነፍስ ጋር ተዋሃድኩ ፤ ጉድለት ፤ እንከን ፤ ድክመት መልክ እና ይዘቱን እየቀያየረ ሁሉም ጋር እንዳለ ብዙ ቆይቶ ነው የገባኝ ። ጉድለት ይዞ ምሉዕ ፍለጋ መባተል ያለመብሰል ምልክት ነበር። አለመብሰል ነበር ያዳከረኝ ። ትላንት የገፋሁትን አይነት ማግኘት ቀላል አይደለም ። ሶፊያ እንዲህ አልነበረችም ፤ ጭንቅላቷ ሰልቷል ። እድሜ ይሆን ፤ንባብ ይሆን ፤ ከነፍስ ነፍስ መባተሏ ይሆን ብቻ ሃሳቦቿን የምትገልፅበት መንገድ ጭምር ተቀይሯል ።
ዋነኛ የመለያየት ምክንያት ፍፁም ነፍስ ፍለጋ መባተል ነው። ለድክመቶቻችን ሁሉ ጣት
ቅሰራ እና ማላከክ ፈይዳ የለውም ! አለመብሰል ስንቱን በረከታችንን አሳጣን ።

ቸር ሰንብቱልኝ

#Adhanom Mitiku


@yekaldebdabewoch
494 views Hebest , 14:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 17:22:52 እስኪ ወንጀል እንስራ ውዴ
ልቤን ስረቀው ልብህን ልስረቀዉ
288 views Hebest , 14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 06:51:19

እስከምትቸለው ድረስ ፍቅርን ስጥ እያወክ አትበድል በቻልከው መጠን ለማስደስት ጣር እንተ ስትቅርብው እሱ እጥፍ ሚርቅህ ከሆን ተወውና ኣምራጭ ፈለግ ምክንያቱም አንዳንድ. ስዎች ስትከተላቸው መሄጃ ያጣህ ይመስላቸዎልና !!


‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌@yekaldebdabewoch
453 viewsHáŷmî, 03:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 06:50:13 እንዳልጠይቅ ይቅርታ ማረኝ እንዳልልህ
እኔስ ሳውቀው ምንም የለም አንተን ያስቀየምኩህ
ግራ ገባኝ ምን ልሁን ደግሞ ናፈከኝ
ተበድየም ባንተ ላይ መቁረጥ አቃተኝ
@yekaldebdabewoch
404 viewsHáŷmî, 03:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 22:08:02 ውሽት
በእዕምሮዬ ልቆ በምግባር
ብደክምም
ላንቺ ያለኝን ፍቅር
ፍጹም አልዋሽውም
ምን እንድል ፈለግሽ
አንቺ በበኩልሽ
እኔ በበኩሌ እወድሻላው
ብዬ ስልሽ
ውሸት አይምሰልሽ
ስቶጪ ስስትገቢ የጫማሽን
ክር ፍትቼ ባላስተኛሽ
ጥዋት ተነስቼ ቁርስ ባላበላሽ
የወንድ መገለጫው ክብሩ
እሱን ሰጠውሽ
ከወርቅ የከበረውን ልቤን
እሱን ከስጠውሽ
በርግጥ ለፍቅሬ መግለጫ
ማድረግ ያለብኝን ሳላደርግ አልቀርሁም
አመታትን ልቤ ላይ አኑሬሽም
ባልፍም
አይቆጨኝም
ብቻ ለኔ አንቺ
ሰማይ የተሳልሽ
ከልቤ ማትፋቂ
ቀስተደመናዬ ነሽ።
@ ከዳዊት (ለ)
399 viewsዳዊት, edited  19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 08:20:23 በውስጤ ላሉት የ"ለምን" ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት፣ ጦርነት የከፈተብኝን ውስጤን ዝም ለማሰኘት ስል መናገር ጀመርኩ። አብደሀል ለሚሉኝ አለማበዴን ለማስረዳት አላበድኩም ብዬ መጮህ ጀመርኩ። ቀስ በቀስ ሰዎች ሸሹኝ፤ የውስጤን በመናገሬ እብድ ተባልኩ።
እኔ ግን... አሁንም እላለው፤ ላለመሸነፍ የምታገል፣ እብድ አለመሆኔን ለማሳመን የምለፈልፍ ሰው እንጂ በእርግጥ እብድ አይደለሁም።

✥-- @ABEN_E --✥

@yekaldebdabewoch
583 viewsKal--kidan, 05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 08:14:31 የሆነ ምሉዕነት መንፈሱን አጥግቦታል... የቤቱ እያንዳንዱ ጥግ ብርሃን ይፈንጥቃል... ለሱ ብቻ የሚሰማውን ዝማሬ ያዜማል... እርሱ ብቻ በሚያስተውለው መንገድ ዝማሬውን ተከትለው የቤቱ እቃዎች ያሸበሽባሉ ... ሁሉ ነገር ያጫውተዋል... ከመታጠቢያ ቤት የሱን ሸሚዝ ብቻ ለብሳ ስትመጣ ጎትቶ ወደ አልጋው አስቀመጣት... ልመና እና ጉጉት ኩራት በተቀላቀለው ደምፅ "ዛሬ አትሂጅ ..." አላት ካንገቷ ስር የሚፈልቀውን መአዛ እየማገ...
"ሂድ ሞዛዛ... " ብላው ካልገው ላይ ተስፈንጥራ ተነሳች...
"ምን አለበት?"
ስልኳን እየጎረጎረች "አይሆንማ "
"እባክሽ አለሜ"
"ተፌ ደሞ እያወክ"
ጉጉቱ ለሷ ፈተና እንደሚሆንባት ሲገባው ዝም አለ ...ገፁ ላይ ነፍስ ስታጣ አይኗ ሃዘን ለበሰ... ካልጋው ላይ ወጥታ እቅፉ ውስጥ ተወሸቀች... "ተፌ..."
"ወዬ አለሜ..."
"በነፃነት ውስጥ ላፈቅርህ እፈልጋለው..."


የሚለው አልነበረውም አጥብቆ አቀፋት አናቷን ሳማት ...ሲተቃቀፉ ከአካሏ ላይ ስሮች ሲበቅሉ ይታወቃታል... ቆዳቸው ሲገናኝ እርስ በርስ ሲዋዋጡ ታስተውላለች ካንደበቱ ቃል ባይወጣውም የልቡ ምት ስልቱን ሲቀይር ይሰማታል...ምንም አትለውም...እቅፉ ውስጥ እንዳለች ዝምታዋን ያዳምጣል... ዝምታዋ ላይ ትዝታ ይቀዳበታል... እና በትውስታዎቹ ልክ ደጋግሞ ይስማታል...


/ዘካሪያስ/


@yekaldebdabewoch
518 viewsKal--kidan, 05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ