Get Mystery Box with random crypto!

የ(لفظ زلجلالة) ህግጋት #ክፍል_ሁለት ለዛሬ የምንመለከተው ስለ( لفظ الجلالۃ ) | ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

የ(لفظ زلجلالة) ህግጋት

#ክፍል_ሁለት

ለዛሬ የምንመለከተው ስለ( لفظ الجلالۃ ) ይሆናል

#ለፍዘል_ጀላላህ ማለት በአላህ ስሞች ላይ የምትመጣዋ #ላም ናት የዝችን ላም አህካም #በሶስት መልኩ እንመለከታለን


لام الجلالۃ أتت قبلها الفتحۃ

لام الجلالۃ أتت قبلها الضَمَّا

لام الجلالۃ أتت قبلها الكسرا

እነዝህ የላሙል ጀላላህ ክፍሎች ናቸው ለፍዘል ጀላላህ በነዝህ ሁኔታ ነው የምትከሰተው እስኪ አንድ በአንድ እንይ ኢንሻ አላህ

لام الجلالۃ أتت قبلها الفتحۃ  
حكمها التفخيم   والشاهد    وفخم الام من إسم الله عن فتحٍ أو ضمٍّ كعبد ﷲ

ይህ ላም ከፊትለፊቱ ፈትሀ የመጣበት ላሙል ጀላላህ ነው ይህ ደግሞ ሑክሙ ( ፍርዱ ) #ተፍኺም ( ወፍራም ) ነው የምትሆነው እሷን ማቅጠን አይቻልም

ለምሳሌ ፦  {{ إنَّ ﷲ }}   {{ وَﷲ }}

እነዝህ ላሞች ሁለቱም ከፊትለፊታቸው የመጣው ፊደል ፈትሀ ነው ያለው ለዛ ሲባል ይወፍራል ማቅጠን አይቻልም።

لام الجلالۃ أتت قبلها الضما   
حكمها التفخيم    والشاهد    وفخم الام من إسم الله عن فتحٍ أوْ ضمٍّ كعبد الله

ይህ ደግሞ ላሙል ጀላላህ ከፊት ለፊቷ ዶማ ሲመጣባትም ሑክሙ ወይም ፍርዱ ትወፍራለች #ተፍኺም ናት ማቅጠን አይቻልም

ለምሳሌ ፦  {{ نَحْن أنصارُ ﷲ }}

እዝህ ምሳሌ ላይ ራ ዶማ ስለሆነች ላሟም ትወፍራለች ።


لام الجلالۃ أتت قبلها الكسرا  
حكمها الترقيق
    
#ላሙል_ጀላላህ ከበፊቷ ከስራህ ከመጣባት እሷም ያላት ሑክም ትቀጥናለች #ተርቂቅ ነው የምትሆነው እሷን ማስወፈር አይቻልም።

ለምሳሌ ፦ {{ لِلَّٰهِ ملك السموات }}

በዝህ ምሳሌ መሰረት የበፊተኛዋ ላም ከስራህ ስለሆነች #ላሙል_ጀላላህም ትቀጥናለች ማለት ነው ማስወፈር አይቻልም #ወሏሁ_አዕለም

ይቀጥላል ኢንሻ አላህ ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን

... አብዱረህማን አቡ ዐሰይሚን

ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል
◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
ጆይን :   ሼር  ፣ ሼር ፣ ሼር
                  بـــارك الـلــه  فـــــيــــــكـــم
https://t.me/furqan_school
https://t.me/furqan_school