Get Mystery Box with random crypto!

#ቁርአንን_አስተካክሎ_መቅራት — የአሏህ ቃል ከሰባት ሰማይ በላይ የወረደውን የፈጣሪያችንን ንግ | ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

#ቁርአንን_አስተካክሎ_መቅራት

— የአሏህ ቃል ከሰባት ሰማይ በላይ የወረደውን የፈጣሪያችንን ንግግር በትክክል በወረደበት መልኩ መቅራት ነው የሚፈለገው።

★ይህንን ታላቅ የአላህን ቃል በትክክል ለመቅራት ደግሞ በመጀመሪያ ላይ የተለያዩ ቃዒዳዎችን ትማራለክ ከተጅዊድ ጭምር።

ይህንን ቃዒዳህ የምትማረው ወደ ላይ ስትቀራ የፊደላትን #መኻሪጅ እና #ሲፋት ለማወቅ እና ለማስተካከል ትልቅ ድርሻ ስለለው ነው።

አብዘሀኛው ህዝባችን ቁርአንን በትክክል መቅራት አይችልም ለተጅዊድ ያላቸው ቦታ በጣም ዝቅተኛ ነውና።

አብዘሀኛው ህዝብ የሚፈልገው እንደምንም ብሎ ማኽተም ብቻ እንጅ በትክክል መቀራቱን አይደለም ይህ ደግሞ ትክክል አይደለም።

ቁርአን ማኽተሙ ብቻ ያለ ተጅዊድ ያለ ማስተካከል ጥቅም የለውም ወንድም እህቶች ስለዝህ በተጅዊድ ላይ ትኩረት እንስጥ።

ከፊሎች ደግሞ የተጅዊድን ት/ት የሚንቁም አሉ ግን ይዓጅብካል ስለ አንድ አሕካም ወይንም መኻሪጅ ብትጠይቀው ምንም የማይመልስልክ የተጅዊድን ት/ት ሲያጣጥልብክ ትመለከታለክ ።

ምን ማጣጣል ብቻ ይሄ ዝም ብሎ ጊዜን መጨረስ ነው ይልካልም አሏሁሙስተዓን ተጅዊድን መማርኮ #ፈርዱል_ኪፋያ ነው ፣ በሁሉም ቃሪእ ላይ ደግሞ #ፈርዱል_ዓይን ነው ይህንን አያውቁምን

እናም ወንድም እህቶች ይህንን የአሏህን ቃል በትክክል  ልንቀራ ዘንድ ሰበብ የሚሆነን እነዚህ ቃዒዳዎች የተጅዊድ ት/ቶች ስለሆኑ በጣም ትኩረት ማድረግ ይኖርብናል ።

አሏህ የሱን ቃል በትክክል ከሚያነቡትና ከሚተገብሩት ያድርገን...

◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
ጆይን :   ሼር  ፣ ሼር ፣ ሼር
         بـــارك الـلــه  فـــــيــــــكـــم ...
https://t.me/furqan_school
https://t.me/furqan_school