Get Mystery Box with random crypto!

#ቁርኣን_የሕይወት_ብርኃን / የአንባቢ እረፍት ሱራዋን ለአጎቴ ልጅ ሰጠሁት 'አንድ የገጠር ሰ | ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

#ቁርኣን_የሕይወት_ብርኃን /
የአንባቢ እረፍት

ሱራዋን ለአጎቴ ልጅ ሰጠሁት
"አንድ የገጠር ሰው ፋቲሓን ብቻ እየቀራ ሲሰግድ ያዩት አንድ ሸይኽ ሱረቱ አድ-ዱሐን አስተምረውት ከፋቲሃ ቡሀላ እሷን እየቀራ ሲሰግድ ቆየና የሆነ ጊዜ ላይ ...... ልክ እንደሱ ፋቲሐን ብቻ እየቀራ ለሚሰግድ ለአጎቱ ልጅ ሱራዋን አስተማረውና.... እርሱ ግን ልክ እንደበፊቱ ፋቲሐን ብቻ እየቀራ መስገድ ጀመረ።
ሱረቱ አድ-ዱሐን ያስተማሩት ሸይኽ በሌላ ጊዜ ፋቲሐን ብቻ እየቀራ ሲሰግድ አዩትና ያኔ ያስተማርኩህ ሱራስ...? ብለው ሲጠይቁት ሱራዋን ለአጎቴ ልጅ ሰጠሁት/አስተማርኩት፣ የሰጡትን ስጦታ መልሶ መውሰድ አይቻልም ስለተባለ እኔ እሷን መቅራት አቆምኩ አላቸው ይባላል!።

#ቁርኣን_የህይወት_ብርሃን
እየኮመኮማችሁ

https://t.me/furqan_school