Get Mystery Box with random crypto!

ቁርኣንን መተው የተለያዩ አይነቶች አሉት!!! ኢብኑል ቀይም (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ: | ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

ቁርኣንን መተው የተለያዩ አይነቶች አሉት!!!

ኢብኑል ቀይም (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ:-

➊ ,ቁርኣንን መተው ማለት፣ ከመስማትና በርሱ ከማመን እንዲሁም ወደርሱ ከመጠጋት መራቁ ነው።

❷ , በቁርኣን ከመተግበር መራቅ፣ ቢያነበውም ቢያምንበትም ሀላልና ሀራም በሚያደርገው ነገር ላይ ተግባሪ ሆኖ አለመቆም ቁርኣንን ከመተው ነው።

➌ , በመሰረታዊም ሆነ በቅርንጫፋዊ የዲን ጉዳዮች በቁርኣን ከመዳኘት መራቅ ቁርኣንን ከመራቅ ነው።
እንዲሁም እርግጠኛነትን አያስይዝም፣ ማስረጃዎቹም ቃል ብቻ እንጂ እውቀትን አያስጨብጡም ብሎ ማመን ቁርኣንን ከመራቅ ነው።

➍ , ሲያነቡት አለመገንዘብና አለማስተንተን ተናጋሪው በሚናገረው ምን እንደፈለገበት ለማወቅ ጥረት አለማድረግ ቁርኣንን ከመራቅ (ከመተው) ነው።

➎ ,በቁርኣን መታከምን መተው፣ በርሱም ለጠቅላላ የልብ በሽታ መድኃኒትነትን መተውና ለህክምና ከርሱ ውጭ ባለ ነገር ላይ መድኃኒትነትን መፈለጉ በርሱ ከመታከም መራቁ ቁርኣንን ከመተው ነው።

ይህ ሁሉ የላቀው አላህ እንዲህ በማለቱ ውስጥ ይካተታል:-

﴿وَقالَ الرَّسولُ يا رَبِّ إِنَّ قَومِي اتَّخَذوا هذَا القُرآنَ مَهجورًا﴾ الفرقان ٣٠

«መልእክተኛውም “ጌታዬ ሆይ! ሕዝቦቼ ይህንን ቁርኣን የተተወ ነገር አድርገው ያዙት” አለ።»
[አል ፉርቃን 30]አል ፈዋዒድ 82

Share
↷⇣ ⇣↷
https://t.me/furqan_school
https://t.me/furqan_school