«خَيْرُكُمْ مَنْ تَعَلَّمَ الْقُرْآنَ وَعَلَّمَهُ»: * ክፍል አንድ ኑን አሳኪና ወተንዊን* التعريف النون الساكنة : _ ኑን አሳኪና ማለት ፦ እሷ ኑን ፊደል ሁና በምንም አይነት ሀረካ ያልተሀረከች *( نْ )* ማለት ነው ። _ ከተገነባችበት ንግግር አስሊ ናት _ በምንቀጥልበት ጊዜ ፣ በምናቆምበት ጊዜ ፣ በምንናገርበት ጊዜ እና በምንፅፍበት ጊዜም እሷ ትገኛለች ( ثابتة ) ናት _ በስም ፣ በፊደል እና በድርጊት ውስጥ ትመጣለች _ በመጨረሻም በመሀልም ሁና ትመጣለች ። *ምሳሌ፦ ( من عمل ) ( منكم ) ( عنه)* تعريف التنوين : _ ተንዊን ማለት ፦ ኑን ስኩን ጭማሪ ነው _ በስም መጨረሻም ይመጣል _ በምናነብበት ጊዜ እና በምንቀጥል ጊዜ ስትገኝ በምንፅፍበት ጊዜ እና በምናቆምበት ጊዜ ግን አትገኝም ። *ምሳሌ (عليماً ) ( ً خيرا ) ( لعبٌ)* ምልክቷ ሁለት ሁለት ሁና ትመጣለች *( ٌ ٍ ً ) በምናቆምበት ጊዜ ያለው ፍርድ ፡ በአሊፍ ስኩን ሀረከተይን ስበን እናቆማለን *ምሳሌ ( ً خيرا ) ኸይረን የሚለውን ወደ ( خيرا ) ኸይራ ብለን እናቆማለን* _ *ታ መርቡጣ* ሲሆን ደግሞ በሃ ስኩን እናቆማለን *ለማሳሌ፦ (رحمةٍ) ረህመቲን የሚለው ስናቆም ( رحمة ) ረህመህ ብለን እናቆማለን* _ ተንዊን ሸርጡን ሳያሟሉ ግን እንደተንዊን የሚቀሩ አሉ እነሱም ፦ ( لنسفعاً بالناصية ) وليكونا) من الصاغرين) ኡ/ አህመድ አደም አሏህ ይጠብቀው ። بسم الله الحمد الله وحده وصلاة وسلام على من لانبي بعده . السلام عليكم ورحمة الله وبركاته. አንኑን አሳኪና ወተንዊን አራት ህጎች አሏቸው ። 1/ *ኢዝሃር* 2/ *ኢኽፋእ* 3/ *ኢድጋም* 4 *ኢቅላብ* * ኢዝሃር* — ኢዝሃር ማለት ቋንቋዊ ትርጉሙ ግልፅ ማድረግ ነው ። ኢስጢላሃን ( በተጅዊድ ኡለሞች አነጋገር) ከአንኑን አሳኪና ወይም ተነረዊን ቀጥሎ የኢዝሃር ፊደል ሲመጣ ያለምንም ጉና ጭማሪ ግልፅ አድርጎ ማንበብ ማለት ነው። የኢዝሃር ፊደሎች ስድስት ነቸው። *እነርሱም፦ [ ه . ء ح .ع . خ غ*] እነዚህ ስድስቶቹ የኢዝሃር ፊደሎች *ሁሩፈል አልሀልቂ* በመባል ይጠራሉ። ሁሉም ከጉሮሮ የሚወጡ በመሆናቸው። እነዚህ በአንድ ንግግር ተሰብስበው እናገኛቸዋለን። የመጀመሪያ የመጀመሪያ ፊደሎች ጋ እናገኛቸዋለን ። *أخي هاك علما حازه غير خسر* ኢዝሃር ሊሆን የቻለበት ምክንየቱ የፊደሎቹ መውጫ መራራቃቸው ነው። ከአልጀዘሪያ *فعند حرف الحلق أظهر وادغم* *في الام والراء لابغنة لازم* በሁለት ቃል ወይም በአንድ ቃል አናገኘዋለን። *ምሳሌ በሁለት ንግግር ፡* *( رسول أمين )* *በአንድ ንግግር ፡ ( منهم )* هذا والله اعلم . ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል ┄┄┉┉✽» ✿ »✽┉┉┄┄ በኦንላይን ቁርኣን ለመቅራት የመመዝገቢያ ቦት : ↶ https://t.me/FurqanCenterHelpBot ግሩፓችንን ይቀላቀሉ ↶ https://t.me/furqan_school አዲሱን ቻናላችንን ይቀላቀሉ ↶ https://t.me/Furqan_Online_Quran 2.2K viewsFurqan Online Quran, edited 09:03