Get Mystery Box with random crypto!

የፈደላት ባህሪ : ክፍል 04 ተቃራኒ የሌላቸው ባህሪያት (አስ - ሶፊር )፦ማለት የ | ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

የፈደላት ባህሪ : ክፍል 04

ተቃራኒ የሌላቸው ባህሪያት

(አስ - ሶፊር )፦ማለት የፊደሉ መውጫ
በመጣበቡ ምክንያት ድምፁ በተጣበበው
መውጫ ሲወጣ ደመቅ ያለ ልክ ፉጨት
የሚመሥል ድምፅ ነው እሱም ሶፊር ይባላል ።

የሶፊር ባህሪ ያላቸው ፊደላቶች س ز ص
ናቸው
ቀለል ያለ ምሳሌ ያዙ ሰዎች ከጎናችሁ
በሚሰግዱ ወይም ዝም ብለው በሚቀሩ
ግዜ ص س زከሶስቱ አንዱን ፊደል ሲያነቡ
የሆነ የፉጨት ድምፅ የመሠለ ይወጣል

ያ ድምፅ ነው ሶፊር የሚባለው ።

(አል - ቀልቀላህ )ቀልቀላህ ማለት የቀልቀላህ
ፊደሎች ሱኩን በሚሆኑ ጊዜ ካላቸው
የማስቸገር ባህሪ ለመላቀቅ አጋጭተን
(አንጥረን ) የምናነበው ሂደት ነው ።

የቀልቀላህ ፊደላቶች ከላይ እንዳሳለፍነው
አምስት ናቸው ق ط ب ج د

እነዚህ አምስቱ ሱኩን ሁነው ሲመጡ አንጥረን
ማንበብ ነው

ምሳሌ ፦ َوَمَاكَسَب ብለን ስናነብ
ምልክት ያደረኩባት ب ሱኩን
አርገን በምናቆም ጊዜ ነጠር አርገን
እናቆማታለን
ምክንያቱም ከላይ የዘረዘርናቸው
የቀልቀላህ ፊደል ውስጥ ب አንዷ
የቀልቀላህ ባህሪ ያላት ፊደል ስለሆነች ።

( የቀልቀላህ ደረጃ ) ለሁለት ይከፍላል
ቀልቀለተ ኩብራ ) ፦ ማለት
በጠቀስናቸው አምስት ፊደላት በሱኩን በምናቆም ጊዜ የቀልቀላነት ደረጃቸው ከፍ ይላል ማለትም በደንብ ነጠር አርገን
እናቆማለን

(ቀልቀለተ ሱግራ )፦ ማለት ከላይ
የጠቀስናቸው አምስቱ ፊደል ሱኩን ሁነው
በቃል መካከል ሲመጡ ከመጀመሪያው
ቀነስ አድርገን እናነጥራለን

ይቀጥላል ...

┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል

የማመልከቻ ሊንክ : ↶ @FurqanOnlineQuran
ግሩፓችንን ይቀላቀሉ ↶
https://t.me/furqan_school