Get Mystery Box with random crypto!

የአሪስቶትል ምናባዊ ሰው (Aristotle's Imaginary Man) ፨ ' በአለም ላይ ለመኖር የ | የሀሳብ መንገድ

የአሪስቶትል ምናባዊ ሰው (Aristotle's Imaginary Man)
፨ " በአለም ላይ ለመኖር የሚያስፈልጉት ነገሮች እጅግ በጣም ጥቂቶች
ናቸውና አላስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች ራሱን አያጋልጥም፤ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ
እራሱን ቢያገኝ እንኳን ሕይወቱን አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጀና ቆራጥ ነው።
በእንዲህ ያለ ኑሮ ውስጥ ሕይወት አላስፈላጊ መሆኗን አምኖ ተቀብሏል።
ለታይታ ሲል አይኖርም፤ የሚወደውንና የሚጠላውን ነገር መደበቅ አይችልም፤
ሲናገርም ሲያደርግም በግልጽ እንጂ በድብቅ አይደለም፤ በእርሱ አይኖች
የሚደነቁ ነገሮች የሉምና ስለምንም ነገር አይደንቅም፤ ብዙ አያወራም፤ ሰዎችን
ለማስደሰት ሲል የማይገባውን አያደርግም፤ በሌሎች ይመሰገን ወይም ይደነቅ
ዘንድ ግድ የለውም። ጠላቶቹን ጨምሮ ስለ ማንም ሰው ክፉ አያወራም፤
አቋሙ የፀናና አነጋገሩም የተላከ ነው። በዓለም ላይ ጉዳዬ የሚለው ነገር ጥቂት
ስለሆነ ለምንም ነገር አይቸኩልም፤ የሕይወትን ክፉ አጋጣሚዎች በፀጋ መቀበል
ይችላል። እሱ የራሱ ጓደኛ እንጂ ሌላ ጓደኛ የለውም፤ በብቸኝነቱም ተደሳች
ነው።"
አሪስቶትል "ሰው" የሚለው እንግዲህ እንዲህ ያለውን ነው።
ታዲያ በዚህ ሚዛን ስንቶቻችን ሰው ሆነን ይሆን?
ዋቢ መፅሐፍ ጥበብ ቅፅ ፩
ከጲላጦስ ( ኃይለጊዮርጊስ ማሞ)

@yehasab_menged
@yehasab_menged