Get Mystery Box with random crypto!

ጥብቅ መረጃ አሸባሪው ትህነግ ከሽናባ ተራራ ጀምሮ በአራት ዙር በተቆፈረ ምሽግ ራሱን አደራጅቶ እ | Habesha media

ጥብቅ መረጃ

አሸባሪው ትህነግ ከሽናባ ተራራ ጀምሮ በአራት ዙር በተቆፈረ ምሽግ ራሱን አደራጅቶ እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ከመከላከያ ሰራዊት የደረሰበትን ምት መቋቋም ሲያቅተው ሙትና ቁስለኞቹን ይዞ ወደ ፊናርዋ እንደገባ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የአሸባሪው ትህነግ የጦር መሪዎች ወጣቾችናን ሕጻናትን ለጦርነት ሲመለምሉ ጥይት አይመታችሁም እያሉ ለጦርነት ማግደዋል።

ትህነግ የሰራቸው ምሽጎችም መኖሪያ ቤት የሚመስል ጥልቀት ያለው  አንገትን ብቻ የሚያሳይ ሌላው አካላቸውን የሚደብቅ ጠንካራ ምሽግ እንደሆኑ ታውቋል።

በተጨማሪም ትህነግ ሸሽቶ በሄደባቸው አካባቢዎች የUSAID ለትግራይ ህዝብ ተብሎ የመጣ ፍርኖ ዱቄት ለታጣቂዉ እንደሚያዉለዉ የሚያረጋግጥ አርማ ያለበት ማዳበሪያ እንደተገኘ ተረጋግጧል።

የትህነግ የሽብር ብድን በነዚህ ጥቂት ቀናት ከፍተኛ ምሽጎችን የጦር ጀነራሎቹን እያጣና እየሸሸ እንዳለ ከሰሞኑ በወጡ መረጃዎች ለማረጋገጥ ተችሏል።
via EBN