Get Mystery Box with random crypto!

#ፀሀይ በቃሉዋ መንገድ ለይ ፍጹም አትባክንም፡ ከምስራቅ ምእራብ መንገዷን አትስትም። #እኔስ ከ | ሸገርን በግጥም

#ፀሀይ

በቃሉዋ መንገድ ለይ ፍጹም አትባክንም፡
ከምስራቅ ምእራብ መንገዷን አትስትም።

#እኔስ
ከቃልሽ እውነታ መች እርቄ አውቃለው፡
ልኬ ነው ባልሺኝ ልክ በመንገድሽ አለው።
አይኔን እዪው ዛሬ፡
ከትናንት መንገድሽ ሄዶ መች ይነቃል።
ልቤስ የፍቅርሽን ወይን መች አጉድሎ ያውቃል??

አንቺዬ.......ልጠይቅሽ እስኪ፡
ትናንት ያዘለ፡
ትዝታን ያዘለ ተጓዥ መንገደኛ፡
የትስ መሄጃ አለው የቃል እስረኛ??
ብቻ እጠብቅሻለው......።

[በረከት]
[@berii34]

@yegtm
@yegtm