Get Mystery Box with random crypto!

ለሰው ልጅ ግን በምድር ላይ ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም። *** ከዚያም ከኮረብታው ወረደ፤ እኛም | የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

ለሰው ልጅ ግን በምድር ላይ ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም።
***
ከዚያም ከኮረብታው ወረደ፤ እኛም ተከተልነው። ይሁዳም ከሩቅ ተከተለ። ቆላማው ቦታ ላይ ስንደርስ ሌሊት ሆኖ ነበር።
ቶማስም እንዲህ አለው፡- "መምህር ሆይ አሁን ጨለማ ነው፤ መንገዱንም ወደ ፊት ማየት አንችልም። ፈቃድህ ከሆነ ምግብና መጠለያ ወደምናገኝበት ወደዚያኛው መንደር ምራን"
ኢየሱስም ለቶማስ መለሰ፤ እንዲህም አለ፡- "በተራባችሁ ጊዜ ወደ ከፍታው ይዣችሁ ወጣሁ፡፡ እጅግ በተራባችሁ ጊዜ ወደ ሜዳው ይዣችሁ ወረድኩ።

ነገር ግን ዛሬ ማታ ከእናንተ ጋር መቆየት አልችልም። ብቻዬን ልሆን ይገባኛል”
ስምዖን ጴጥሮስም ወደ ፊት በመውጣት ‹‹መምህር ሆይ በጨለማ መሀል ትተኸን አትሂድ። በእዚህም ቦታ ቢሆን ከአንተ ጋር እንድንቆይ ፍቀድልን። ሌሊቱ እና የሌሊቱ ጥላ አይዘገይም፣ ከእኛ ጋር ከቆየህ ንጋት በቅርቡ ያገኘናል"
ኢየሱስም መልሶ፡- ‹‹በዚች ሌሊት ለቀበሮዎች ጕድጓድ፣ ለሰማይ ወፎችም ጎጆ ይኖራቸዋል፥ ለሰው ልጅ ግን በምድር ላይ ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም።

እናም በእርግጥ አሁን ብቻዬን እሆናለሁ፤ ከፈለጋችሁኝ እናንተን ቀድሞ ካገኘሁበት ሐይቅ አጠገብ ታገኙኛላችሁ›› አለ፡፡
በከባድ ሀዘን ውስጥ ሆነን ከእርሱ ራቅን። ደጋግመን እየቆምን ፊታችንን ወደ እርሱ አዙረን ተመለከትነው፤ እናም በብቸኝነት ግርማ ወደ ምዕራብ ሲንቀሳቀስ አየነው።
ከመካከላችን እርሱን ለማየት ፊቱን ያላዞረው ሰው የአስቆሮቱ ይሁዳ ብቻ ነበር።
ይሁዳም ከዚያ ቀን ጀምሮ ደነገጠ፥ ራቀም። እኔም በፊቱ አደጋ እንዳለ አሰብኩ
- Khalil Gibran

THANK YOU FOR READING.
ELODIA READING
ኤሎድያ ንባብ

@Elodia_G ንባብ @Elodia_G
READING
@Elodia_G ንባብ @Elodia_G
READING
@Elodia_G ንባብ @Elodia_G
READING