Get Mystery Box with random crypto!

ለሰው ምን ያህል መሬት ይበቃዋል? (በሌቭ ቶልስቶይ) ከረዥም ዘመን በፊት በአንድ ትንሽ የደቡብ | የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

ለሰው ምን ያህል መሬት ይበቃዋል?
(በሌቭ ቶልስቶይ)


ከረዥም ዘመን በፊት በአንድ ትንሽ የደቡብ ኤዥያ አገር የሚኖሩ ብልህ ንጉሥ ነበሩ። ግዛታቸውን ለመገንጠል የተነሳ አንድ የውስጥ ወንበዴ ቡድን አስቸግሯቸው ስለነበር በጦርነት ሊያጠፏቸው ወሰኑ፤
ለጦር አዛዡም ይህን ጦርነት በድል ፈፅሞ ከተመለሰ ከፍተኛ የሆነ ሀብትና መሬት እንደሚሰጡት ቃል ገቡለት። በዚህም የተነሳ የንጉሡ ጦር በከፍተኛ ቆራጥነት ተዋግቶ የወንበዴው ጦር ተደመሰሰ። የሞተው ሞቶ የቀረው ቆስሎም ተማረከ፤
ንጉሡ ቃል እንደገቡት ለጦር አዛዡ ብዙ ሀብት ከመደቡለት በኋላ "በእግሩ ቀኑን ሙሉ ፀሀይ እስክትጠልቅ የሄደበትን የግዛቴን መሬት ለክታችሁ ስጡት።" ብለው ሸለሙት።

የጦር አዛዡም ተደሰተ፤ ብዙ ለም የሆነ መሬት መያዝ ይፈልግ ስለነበር በተዘጋጀበት ቀን በጣም በማለዳ ተነስቶ ስንቅ አዘጋጅቶ መጓዝ ጀመረ። በመጀመሪያ ጉልበቱ የቻለውን ያህል በለሙ መሬት ላይ ሮጠ። መሬት ለኪዎችም በፈረስ ይከተሉት ነበር፤
ከዚያም በፍጥነት ቀኑ ሳይመሽ ይራመድ ጀመር። ብዙ ከሄደ በኋላ ወደ ከሰአት ምሳውን ሳይቀር እየሄደ በላ።

ሆኖም ከበላ በኋላ ጥቂት መሬት ሄዶ ስለደከመው እየተራመደ ውሃ ጠጣ። ዘጠኝ ሰአት ያለእረፍት ተጉዞ በመጨረሻ እገሩ በጣም ዛለ፤
ቢሆንም አንድም እርምጃ ቢሆን ለም መሬት ነውና መራመዱን ቀጠለ። ሲል ሲል እግሩ መራመድ አቅቶት ዝሎ ወደቀ።
አሁን ለኪዎቹ ምልክት ሊያደርጉ ሲሉ "ቆዩ ... ቆዩ" ብሎ መዳኽ ጀመረ። ከዚያም ጥቂት ሄዶ በልቡም መሳብ ጀመረ፤
በመጨረሻ ፀሃይ ገና ሳትጠልቅ የቻለውን ተንጠራርቶ ሲሳብ ልቡ ቀጥ አለችና ትንፋሹ ቆሞ ሞተ። የንጉሡ ቦታ ለኪዎችም ደነገጡ።

የጦር አዛዡን ከሞተበት ሳያነሱ በፈረስ መልእክተኛ ወደ ንጉሡ ቤተ መንግሥት ላኩ፤
መልክተኞቹም የአዛዡን ሲጓዝ ውሎ ልቡ ደክሞ መሞቱን ነግረው "ምን ያህል መሬት እንስጠው?" ብለው ጠየቁ። ንጉሡም እጅግ አዝነው "ለሰው ምን ያህል መሬት ይበቃዋል?" ብለው ተከዙ፤
"እንግዲህ ይህ ሰው የወደቀበትን ቦታ ብቻ ከእግሩ ጫፍ እስከ ራሱ ጫፍ ብቻ ለክታችሁ ስጡት። ሬሳውንም እዚያው ቦታ ቆፍራችሁ በክብር ቅበሩትና የጀግና ሃውልት አቁሙለት።" አሏቸው፤
በተባለው መሰረት የጦር አዛዡ በመጨረሻ በሞተባት ቦታ በክብር ተቀበረ። በመቃብሩም ሀውልት ላይ

"ለሰው የሚበቃው መሬት ይህ ነው።" ተብሎ ተፃፈ።

ከንባብ ዳርቻ ለህይወት ጠኣም
#share and join for more
@KenibabDaricha1
@KenibabDaricha1