Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅር መሸነፍ ነው ፍቅር እጅመስጠት ነው ለስሜት ተገዢ መሆን ማለት ነው | የግጥም ቃላቶች ✍



ፍቅር መሸነፍ ነው
ፍቅር እጅመስጠት ነው

ለስሜት ተገዢ መሆን ማለት ነው ፍቅር ከምክንያት ውጭ ሆኖ መኖርን መቀበል ነው

ፍቅር ከራስ ቁጥጥር ውጭ መሆን ነው
ስለዚህ አዎ መሸነፍ ነው

ያስፈራል ፍቅር የማይታከሙት ህመም የማይጠገን ቁስል የማያባራ እንባና ሰቆቃ ሊሆን ይችላል

የሚያስፈራው ያፈቀርነው ሰው ሳይሆን ማፍቀር ራሱ ነው፡

ካፈቀርክ በኀላ እኔ የምትለው ሁሉ ይጠፋል

ለራሳችን ትርፍ እንሆናለን በፈቃደኝነት ከራሳችን የምናስቀድመው የምናስበልጠው ሌላ ሰው ይኖራል ማለት ነው

ፍቅር ያለ ውጊያ መማረክ ነው
እጅ መስጠት፣ ወዶ መግባት፣ ከራስ መነጠል፣ መጥፋትና በማያውቁት ሰው ዓለም ውስጥ ገብቶ መሰደድ ነው።


ከወደዱት አጋሩ

@yegetemkalat

ፍቅር ብቻ