Get Mystery Box with random crypto!

ዋናዎቹ (wanawochu) ፍቅር fkr

የቴሌግራም ቻናል አርማ yefuri — ዋናዎቹ (wanawochu) ፍቅር fkr
የቴሌግራም ቻናል አርማ yefuri — ዋናዎቹ (wanawochu) ፍቅር fkr
የሰርጥ አድራሻ: @yefuri
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 451
የሰርጥ መግለጫ

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ
አሜን
Ezi channel layi
Ye fonka zefenoch
Gtmoch
Achachr ye fkr tarikoch
Yilekekubetal destachu destachn new zena feta yibelu.
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧llll
@seya1222
@abuk29

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-03 06:21:47
207 viewsAb, 03:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 06:21:46
197 viewsAb, 03:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 23:11:32 #ጊዜ

ጊዜ. ፦ ይጥላል

ጊዜ ፦ ያነሳል

ጊዜ ፦ ይፈርዳል

ጊዜ ፦ ሁሉም ጊዜውን ይጠብቃል እንጂ መሆኑ አይቀርም
195 viewsAb, 20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 23:11:32 #My_brother ነገ ያንተ መሆኗን ላላመንክባት ሴት በየሳምንቱ ስጦታ ከምትገዛ ምን አለ ብዙ ነገር ላየችብይ ህይወቷን ሙሉ ላንተ ለኖረችው ለእናትህ 1 ኪሎ ቡና ብትገዛ
188 viewsAb, 20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 23:11:32 ካስተማሩ አይቀር
.
ልጅ፡ አባዬ እስኪ ውሸት አሥተምረኝ...?
.
አባት፡ አየሃቸው በሠማይ ላይ ያሉ ሠዎች እህል ሲወቁ?
.
ልጅ፡ ውይ ውይ ውይ አባዬ ገለባው አይኔ ውስጥ ገባ
.
አባት፡ በል አርፈህ ተቀመጥ ከኔ ይበልጥ እየዋሽህ ምኑን አሥተማርኩህ
188 viewsAb, 20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 22:57:23 አህመድ እና መርየም የሚባሉ ባል እና ሚስት ነበሩ። በጣም ደስ የሚል ቤትና ሁለት የሚወደዱ ልጆችም አሏቸው፤ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት።

ከዕለታት አንድ ቀን አህመድ ለስራ ጉዳይ ወደ ሌላ ከተማ እንዲሄድ በአለቆቹ ይነገረዋል። ለበርካታ ቀናት ሊቆይ እንየሚችልም ይገለፅለታል።

ሚስቱ መርየም ይህንን ስትሰማ እሷም ከከተማ ወጣ ብሎ ትንሽ የመቆየት ፍላጎት ስላደረባት አብረው ለመሄድ ጥያቄ ታቀርብለታለች። እርሱም በደስታ እሺታውን ይገልፅላትና ለጉዜ ላይ ዝግጅት ይጀምራሉ። ከሁሉም በፊት ግን #ሁለቱ ልጆቻቸውን በቅርበት የምትጠብቅላቸው አንዲት ታማኝ ሴትን ይቀጥራሉ።

ባልና ሚስቱ ለጉዞ የሚያስፈልጋቸውን ዝግጅት አጠናቀው ወደ ተባለው ከተማ ይሄዳሉ.......

......አህመድና መርየም መመለስ ከሚገባቸው ቀን ዘግይተው ነበር ወደ ቤት የተመለሱት። መኖሪያ ከተማቸው ሲደርሱ ሁለቱም ደስ አላቸው። ነገር ግን ከሚኖሩበት ሰፈር አካባቢ አቅጣጫ ጭስ መሰል ነገር ሲመለከቱ ምን እንደሆነ ለማጣራት በቀጥታ ወደ ቦታው ያመራሉ። አንድ ቤት ተቃጥሎ በእሳት እየነደደ ነበር። #መርየምም "የሚገርም ነው! የእኛ ቤት አይደለም። ወደ ቤታችን ሄደን ልጆቻንን እንይ" ትላለች።

አህመድ ግን መኪናውን እየነዳ ወደ ተቃጠለው ቤት ቀርቦ ተመለከተ። በጣም በማዘንም "የማን ቤት እንደሆነ አወቅሽ? እዚያ ትልቁ ፋብሪካ ውስጥ የሚሰራው የጀማል ቤት እኮ ነው። እስካሁን ከስራ የተመለሰ አይመስለኝም። አንድ ልናደርገው የምንችለው ነገር ይኖራል ብዬ አስባለሁ" በማለት ተናገረ።

ሚስቱ መርየም ግን ተቃወመችው "እኛን የሚያገባን ምንም ነገር የለም። ይህ የለበስከው በጣም የሚያምርና ውድ ልብስህ ከጥቅም ውጭ ነው የሚሆነው" በማለት ወደ ባት እንዲሄዱ ገፋፋችው።

አህመድ ለመርየም ንግግር ምላሽ ሳይሰጥ መኪናውን እያሽከረከረ ወደ ሚቀጣጠለው ቤት ደረጃ አጠገብ አቆማት። ቤቱ ሙሉ በሙሉ በእሳት ተያይዟል። አንዲት ሴት ከቤቱ ውስጥ የስቃይ ድምፅ ታሰማለች። "ልጆቹ! ልጆቹ!!" በማለትም ታለቅሳለች። ባልና ሚስቱ ከሚገባው በላይ ደነገጡ።

አህመድ በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ የወደቀችውን ሴት ትከሻ ክንድ በመያዝ ካነሳት በኋላ ልጆቹ የት እንደሆኑ ጠየቃት። ሴትየዋም ልጆቹ ምድር ቤት ውስጥ መሆናቸውን እያቃሰተች ተናገረች።

አህመድ እየተጣደፈ አጠገቡ ያገኘውን ባልዲ ሙሉ ውሃ በለበሰው ልብስ ላይ በማፍሰስና በውሃ የተነከረ ፎጣ አናቱ ላይ በማሰር ወደ ምድር ቤቱ ይገባል። ምድር ቤቱ በጭስ ታፍኗል። ሙቀቱ ሰው አያስቀርብም። እንደምንም ብሎ ልጆቹን በትከሻው ተሸክሞ ሲወጣ ሌላ የህፃናት የጭንቀት ድምፅ ይሰማዋል። በትከሻው የተሸከማቸውን በፍርሃት የሚንቀጠቀጡ ልጆች ይዞ ከወጣ በኋላ ቤቱ ውስጥ ሌሎች ህፃናትም እንዳሉ ይነገረዋል። ምን ያህል እንደሆኑ ሲጠይቅ ሁለት መሆናቸው ይገለፅለታል።

በድጋሚ ተመልሶ ሊገባ ሲንቀሳቀስ ሚስቱ እጁን ይዛ ልትከለክለው ትሞክራለች። "መሞት ትፈልጋለህ እንዴ!? ተመልሰህ እንዳትገባ!" በማለት ስትናገር አህመድ የያዘችውን እጇን መንጭቆ እሳቱ ወደሚነድበት ቤት ሮጦ ይገባል። በጭስ ታፍነው ለመሞት የተቃረቡ የሚመስሉ ሁለት ህፃናትን ያገኛል። ወዲያውኑ በጎንና ጎኑ አንገቱን በደንብ እንዲይዙ አድርጓቸው ከቤቱ በመውጣት ላይ እያለ አንዳች የሚያውቀው የሚመስለው ነገር ሰውነቱን ይወረዋል። ጎንና ጎኑን አንገቱን በሁለት እጆቻቸው ጨምድደው የያዙት ልጆች የሚያውቃቸው መሰለው። እየሮጠ ከሚቃጠለው ቤት እንደወጣ የተመለከተው ነገር የማይታመን ሆነበት። ሳያስበው ጉንጩ በእንባ ተሞላ። ሁለቱ ህፃናት የራሱ ልጆች ነበሩ። እንድትጠብቃቸው የተቀጠረችው ሴት ገበያ ስትሄድ በአደራ ጎረቤት አስቀምጣቸው ነበር።

@yefuri
193 viewsAb, edited  19:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 10:43:13 .... እደሩ

ሴት ፦ ልጅ ውሀ ናት ሰሜትህን ጥማትህን ታረካለች

ሴት ፦ ፀሐይ ናት ሲበርድህ ታሞቅሃለች

ሴት ፦ ብርሀን ናት ጎጆህን ታደምቃለች

ሴት ፦ ዓይንህ ናት ትመራሃለች ያላየኸውን ታሳይሃለች

ሴት ፦ መሰታወት ናት ዓይንህን በዓይንህ ታሳይሃለች!

ምንም ባለ ፀጋ ብትሆን በሀብት ብትትረፈረፍ ያለእሷ ጎዶሎ ነህ ።

ይህንን ውሉ ካወክ ለሴት ልጅ ክብር ይኑርህ!


SHARE @yefuri
SHARE @yefuri
254 viewsAb, edited  07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 09:16:19
213 viewsAb, 06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ