አፈቅርሻለሁ ለምን አትበይኝ ምክንያት የለኝም ፍቅር ስሜት እንጂ ስበብ አይመስለኝም ብቻ | ፍልስፍና philosophy
አፈቅርሻለሁ
ለምን አትበይኝ ምክንያት የለኝም
ፍቅር ስሜት እንጂ ስበብ አይመስለኝም
ብቻ አፈቅርሻለሁ ማፍቀሬ ጥልቅ ነው
ፍቅርሽ ለእኔነቴ የልብ ዙፋን ነው
ህያው የሚሆነው አንቺን በማፍቀር ነው
ጅልነት አይደለም ሁሌ አንቺን ማለቴ
ሞኝነት አይሆንም ለፍቅርሽ መክሳቴ
ውለታ ፈልጌ ውደጅኝ አላልኩም
ፍቅር ሰጠው እንጅ ምላሽ አልፈለኩም
በቃ አፈቅርሻለሁ ማለቴን አልተውኩትም
አዎ አፈቅርሻለሁ አዎ እወድሻለሁ
ፍቅርቅር አድርጌሽ ሁሌም እኖራለሁ
አንቺን በማፍቀሬ እፎይታ አገኛለሁ
አንቺን እያፈቀርኩ በደስታ እኖራለሁ
በፍቅርሽ ውቂያኖስ ስዋኝ እኖራለሁ
አንቺ ካለሽልኝ ሙሉ ሠው እሆናለሁ
https://t.me/yefkrterkoch