Get Mystery Box with random crypto!

የ ፍቅር ቃል ♡ⓛⓞⓥⓔ♡

የቴሌግራም ቻናል አርማ yefki — የ ፍቅር ቃል ♡ⓛⓞⓥⓔ♡
የቴሌግራም ቻናል አርማ yefki — የ ፍቅር ቃል ♡ⓛⓞⓥⓔ♡
የሰርጥ አድራሻ: @yefki
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.08K
የሰርጥ መግለጫ

.የሰውነት መመዘኛው ትልቁ ሚዛን ፍቅር ነው.
-------------------------
መቀላቀል ይፈቀዳል መውጣት ግን አፈይቀድም !
እንኳን ደህና መጡ
VIEW CHANNEL 👇
https://t.me/yefki
የዩቱዩብ ቻናል ከፍተናል ሰብስክራይብ ማድረግ ለሚፈልግ
ይህው ሊንክ https://youtube.com/channel/UC1NOc9kd41Ziez_s94bt37A

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-12-26 23:12:42 ​​ መ ል ካ ሙ ዶ ክ ተ ር

ክፍል አራት

አዘጋጅ ሰሊና( የብዕር ስም )

ለምንድነው ግን ህይወቴ እንደዚህ በመልካም ሰዎች ጥላ ስር የምትኖረው? እግዚአብሔር አንዱን ሲነጥቅ ሌላውን አዘጋጅቶ ነው ማለት ነው? የእዩኤል ህመም ከቀን ወደ ቀን እየባሰ እየመጣ ነው እናቱ ግን ከበፊቱ አሁን በትንሽም ቢሆን መንቀሳቀስ ጀምረዋሉ ዶክተሩም ክትትል ማድረጉን አላቆመም እንደውም በራሱ ብር ከሌላ ሃኪም ቤቶችም ጭምር መድሃኒት ገዝቶ እየመጣ ነው፣ ግን ምን አይነት መልካም ሰው ነው? ብዙም ጊዜ ሰዎች መልካም ነገሮችን የሚያደርጉት ለዘመድ አልያም ጥሩ ግኑኝነት ላላቸው ሰው ብቻ ነው እንጂ እንደ ዶክተሩ ምንም ለማያውቁት ሰው መልካምነትን የሚያደርጉት ከመቶ ምናልባትም ቢኖሩ ሁለት ወይንም ሦስት ሰዎች ብቻ ናቸው። እዩኤል አንድ ሰሞን ጤነኛ ይሆናል ግን ወዲያውኑ ተመልሶ የባሰ ለሞት ሁሉ የቀረበ በሽተኛ ይሆናል የምትወደው ሰው ችግር ውስጥ ነው ማለት ደግሞ ከሰውነትህ አንዱ አካል ላይ ትልቅ ቁስል እንደመኖር ማለት ነው ሰውነትህ ላይ ትልቅ ቁስል ሲኖር ለአንድ ቦታ ብቻ ህመም አይሰማህም ለሁሉም የሰውነትህ ክፍል እንጂ! የምትወደው ሰው ችግር ውስጥ ነው ማለትም ልክ እንዲሁ ነው ቁስሉ የአንድ ሰው ብቻ ሳይሆን ቁስሉ ሁለቱንም የመጉዳት አቅም አለው በህመም ምክንያት ይበልጥ እየተጎዳ ያለው እዩኤል ቢሆንም ህመሙ ግን ከእሱም አልፎ የኔንንም ደስታ መንጠቅ አልተወም፣ በቃ ደስተኛ መሆን አልቻልኩም ሁሌም ሀዘን ሁሌም እምባ ብቻ እዩኤል እንደዚህ ሆኖ ማየት በራሱ ራሱን የቻለ ትልቅ ህመም ነው አይዞሽ ሀረግ በእኔ ምክንያት አንቺም ተጨናነቅሽ አይደል አይዞሽ ፍቅር ለሁሉም ቀን አለ ቀን የማይለውጠው ነገር የለም እኛም አንድ ቀን ሙሉ ሰው እንሆናለን ግን ምንጊዜም ተስፋ አትቁረጪ ብሎ እኔን ለማጽናናት የማይናገረው ነገር የለም የኔ ጥያቄ ግን መቼ? የሚለው ነው ህይወቴን በሙሉ አንድ ቀን አንድ ቀን እያልኩ ለመኖር ለአንዲት ምስኪን ልጅ ተስፋ የሚባል ቀልድ ምን ያደርጋል? የተስፋ ትርጉም ያልገባቸው እንደ እኔ አይነቱ ስንት ሰዎች ይኖሩ ይሆን? ተስፋ ማለት ጭላንጭል አይተው የሚጠብቁት ነገር የሚመስላቸው ተስፋ ማለት ደመና አይተው ይዘንባል ብሎ መጠበቅ የሚመስላቸው ምስኪኖች ተስፋ ማለት ግን ምንም ጭላንጭል የሌለበትን ነገር በእምነት መጠበቅ ማለት ነው ምንም ጭላንጭል የሌላውን ነገር መጠበቅ ደግሞ በጣም ከባድ ነው ለዚህም ነው ሰዎች አንድን ነገር ተስፋ አድርገው እስከመጨረሻው በእምነት ጸንተው መጠበቅ የማይችሉት ለትንሽ ጊዜ ጠብቀው ጭላንጭል ሲያጡ ተስፋ ቆርጠው ወደኋላ ተመልሰው የሚወድቁት እኔ እንደሆንኩ መጀመርያውኑ ብሩህ ተስፋ የለኝም ገና ከአሁኑ ሽንፈት ሽንፈት እያለኝ ነው ቀድሞ የሽንፈት ጽዋ መቅመስ ደግሞ ሞት ነው! ዛሬ ከዶክተሩ ጋር ቀጠሮ አለን ዛሬ የእዩኤልን ሙሉ የምርመራ ውጤት ለመንገር ሃኪም ቤት ቀጥሮኛል ምን ይፈጠር ይሆን? . . . . .

꧁༺༒༻꧂
ይቀጥላል
​​​​​​​​╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝

ሀሳብ በግል ለመስጠት @dkeya
• ₊° ✧︡ ˗ ˏ ˋ ♡ ˎˊ ˗ »»— ★ ——

ለአስተያየት ለውይይት @coldcommnt
★━━━━━━━━━━━━★
:¨· .·¨ :
`· .የ ፍቅር ቃል★° *゚ ተቀላቀል ክፈት

╔═ .✵. ══════════╗
@YEFKI @YEFKI @YEFKI
╚══════════ .✵. ═╝
1.1K views·.·★ 𝕜𝕖𝕪𝕒 ★·.· , edited  20:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-26 23:10:03 ​​ መልካሙ ዶክተር

ክፍል ሶስት

ክትትል ይፈልጋል ክትትል የሚያደርግለት ዶክተር ያስፈልጋል አለኝ አይይይ ዶክተር ክትትል ነው ያልከኝ? አይደለም ክትትል ለሚያደርግ ዶክተር እንደዚህ እራሱን ስቶ ወድቆ ህክምና ለማግኘት ብር እንኩዋን አጥተን እንዴት እንደሆንኩ እያየህ እንደዚህ ትላለህ አልኩት ቆይ ለምን እንደዚህ አናደርግም አለኝ እንዴት አልኩት እእእእ....
ቆይ ለምን እንደዚህ አናደርግም አለኝ እንዴት አልኩት እእእእ በብር ምክንያት ማንም ሰው መሞት የለበትም ስለዚህ በቻልኩ መጠን ቤት እየመጣሁ እኔ ክትትል አደርጋለሁ ምናልባት አንድ ቀን ጤናማ ህይወት መኖር ሲጀምር ሰርቶ መክፈል ይችላል፣ ክሊኒኩ የራሴ ስለሆነ ልጁን ለመርዳት እፈልጋለሁ አለኝ ዋውውውው በጊዜው የተሰማኝን ደስታ ልነገራችሁ አልችልም ዶክተር ከልብ አመሰግናለሁ በጣም ጨንቆኝ ነበረ እግዚአብሔር አብዝቶ ይስጥህ በእውነት መልካም ሰው ነህ ብዬ አመስግኜ እዩኤልን ወደ ቤት ይዤው መጣሁ። እናቱ ቤት ውስጥ በጭንቅ ተውጠው ቁጭ ብለው ነበር... ይህች አለም እንደዚህ ናት ምንም ፍትሕ የሚባል ነገር አታውቅም! ዛሬ የአንተ ጭንቅ ምናልባት ብር ማጣት ሊሆን ይችላል ዛሬ የአንተ ጭንቅ ጣፋጭ ምግብ ማጣት ሊሆን ይችላል ዛሬ የአንተ ጭንቅ ምናልባት ጥሩ ልብስ አለመኖር ሊሆን ይችላል ዛሬ የአንተ ጭንቅ ምናልባት ጥሩ አልጋ ላይ አለመተኛት ሊሆን ይችላል ዛሬ የአንተ ጭንቅ ምናልባት ከጓደኞችህ የበታች ሆኖ መታየት ሊሆን ይችላል ግን አንድ ቀን ፈጣሪ ለአንተ የሰጠህን ነጻ ስጦታዎች ዞር ብለህ ለማየት አይንህን ብከፈት እርግጠኛ ነኝ በህይወትህ ደስተኛ መሆን ትጀምራለህ። እንግዲህ አስቡ በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሁለቱም ሰዎች የአልጋ ቁረኛ መሆን ምንያህል ከባድ ነገር እንደሆነ እግዚአብሔር ከእንደዚህ አይነት የህይወት ፈተና ይሰውራችሁ እንደዚህ አይነት አጋጣሚ በጣም ከባድ ፈተና ነው ዛሬ አንተ በሰላም እየኖርክ ትርፍ ስለሆነ ነገር ትጨናቀለህ እባክህ የኔ ወንድም/እህት ጓደኛቼ እኔ እንዲሁ እያለሁ መኪና ያዙ ከማለትህ በፊት ጓደኞቼ እኔ እንዲሁ እያለሁ ሀብታም ሆኑ ከማለትህ በፊት ጓደኞቼ እኔ እንዲሁ እያለሁ ትልቅ ቦታ ደረሱ ከማለትህ በፊት . . . እኔ በሰላም እየኖርኩ ጓደኞቼ ግን ሰላም የላቸውም ለእኔ ቤተሰብ አለኝ ለጓደኞቼ ግን ቤተሰብ የላቸውም እኔ በህይወት አለው ጓደኞቼ ግን በህይወት የሉም የሚለውን ነገር ማሰቡን አትርሳ በዚህ አለም ላይ የህይወት ደረጃ የሚባል ነገር አለ አንድን ሰው መብለጥ የምትችለው በጥቂት ጎኖች ብቻ ነው እሱ ደግሞ በሌላ መንገድ ይበልጥሃል ወደድክም ጠላህም አንድን ሰው በሁሉ መብለጥ አትችልም አንተ አዋቂ ሀብታም ብትሆን ምናልባት እሱ ቆንጆ ደስተኛ ሊሆን ይችላል አንተ ውብ ቆንጆ ተወዳጅ ብትሆን ምናልባት እሱ ከአንተ የተሻለ ትዳር መስርቶ የሚኖር ሊሆን ይችላል አንተ ዲግሪ ላይ ዲግሪ ቢኖርክ እሱ በተፈጥሮ ከአንተ ይልቅ አስተዋይ ህይወቱን በትክክል መምራት የሚችል ሊሆን ይችላል በቃ ህይወት እንደዚህ ናት ይሄን ሁሉ መንገድ የመጣውት ደስተኛ ለመሆን ከእናንተ የበላይ የሆኑትን ብቻ ሳይሆን የበታች የሆኑትንም ተመልተኩ ለማለት ያህል ነው። እኔ ከብዙ ሰዎች የተሻልኩ እንደሆንኩ ያወኩት እዩኤል እና እናቱ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ ሳይኖራቸው ሁለቱም በህመም ተገደው ቤት ውስጥ ሞትን እየጠበቁ በማየቴ ነው ፈጣሪ አብዝቶ ይስጠው መልካሙ ዶክተር ክትትል ብቻ ሳይሆን ምግብ ሳይቀር እርዳታ እያደረገ ነው ለምንድነው ግን ህይወቴ እንደዚህ በመልካም ሰዎች ጥላ ስር ገብታ የምትኖረው? ፈጣሪ አንዱን ሲነጥቅ ሌላውን አዘጋጅቶ ነው ማለት ነው? . . . . . .
980 views·.·★ 𝕜𝕖𝕪𝕒 ★·.· , 20:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-26 00:06:34
ክፍል ሶስት
928 views·.·★ 𝕜𝕖𝕪𝕒 ★·.· , 21:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-24 23:40:29 ​​ መልካሙ ዶክተር

ክፍል ሁለት

አቅራቢ ሰሊና
_

ምግቡን ጨርሼ እማማ አመሰግናለሁ ብዬ ልሄድ ስል.. ልጄ የበሉበትን እቃ ማጠብ የጨዋ ሰው ተግባር ነው እቃውን ብታጥቢ ደስ ይለኛል አሉ እማማ ኧረ ችግር የለም እርስዎ ምግብ ሰጥተውኝ እኔ እቃ ማጠብ እንዴት ያቅተኛል እንደውም ቤት ውስጥ ያሉትን በሙሉ አምጡ አልኳቸው ተባረኪ ልጄ ብለው ትንሽ እቃ አምጥተው ሰጡኝ እኔም እቃውን ማጠብ ጀመርኩኝ...
እቃውን ጨርሼ ልሄድ ስል ልጄ አሁን ፀሐዩ በጣም ከባድ ነው ፀሐይ ትንሽ በረድ እስኪል ቁጭ ብለሽ ቴሌቭዥን መመልከት ትችያለሽ አሉኝ የዚህች መልካም እናት ሁኔታ ትንሽ ቢገርመኝም ቁጭ ብዬ ቴሌቭዥን ማየት ጀመርኩኝ በዚህ መሃል ከተቀመጡበት ተነስተው ቡና ማፍላት ጀመሩ...
ይህ ሁሉ ክብር ለኔ? ምን የሚሉት ነገር ነው? ቡናው ተፈልቶ ደረሰ በዚህ ሁሉ ሰዓታት ተጫወቺ ከማለት ውጭ ምንም ጥያቄ እየጠየቁኝ አይደለም እኔ ደግሞ ጥያቄ የማይጠይቅ ሰው ስወድ! በቃ ቤተሰብ ቤት ምናምን ስለሌለኝ ስለ ኑሮ ስለ ቤተሰብ ታሪክ ምናምን የሚጠይቁኝ ሰዎች ያስጠሉኛል፣ ነገር ግን እሳቸውን ለመጠየቅ ምክንያት የሆነኝ ነገር ቡናው ነበረ... እማማ ለምን ቤተሰብ እስኪመጣ ትንሽ አንጠብቅም አልኳቸው ትንሽ ከሳቁ በኋላ ቤተሰብ ነው ያልሽው? ብለው ጠየቁኝ እኔም አዎ ቤተሰብ ባይኖረኝም ቡና ከቤተሰብ ጋር ሲሆን ደስ ይላል ብዬ ነው አልኳቸው አይይይይ ልጄ የሉም አሉኝ አይመጡም ለማለት መስሎኝ ዝም አልኩኝ አብረን ቡናውን ጠጥተን በድጋሚ ለመሄድ ተነሳሁ ትልቅ ቀጠሮ ያለኝ ሰው አልመስልም? ልጄ ገበያ ለመሄድ አስቤ ነበረ ግን አቅም አጣሁ ብለው ዝም አሉ ታዲያ የሚልኩት ሰው የለም? በዚህ ጊዜ ሰው ከየት ይመጣል ብለሽ ነው የምትሄጅበት ከሌለ ለምን አንቺ ሮጥ ብለሽ አትመጪም አሉኝ ማን? እኔ ገበያ? እኔ እቃውን እንዴት ገዝቼ እንደሚመጣ እንኩዋን አላውቅም አልኳቸው በልቤ ደግሞ ለኔ ብር ሰጥቶ መላክ ውሻ ላይ አጥንት እንደመላክ ነው እስከአሁን ዝም ያልኩት ራሱ ምስኪን ስለሆንሽ ነው እንጂ ሌላ ሰው ቤት ገብቼ ቢሆን ኖሮ መቼ ምን ይዤ እንደወጣሁ ማወቅ አትችይም እያልኩ ሴትዮዋን በአግርሞት ማየቱን ቀጠልኩኝ... ቀላል እኮ ነው ልጄ ሮጥ ብለሽ ደርሰሽ ነይ ብለው 300ብር ሰጡኝ እኔም ብሩን ይዤ ከቤት ወጣሁኝ.... ልክ ከቤት እንደወጣሁ አእምሮዬ ላይ ብዙ ሃሳቦች መምጣት ጀምሩ፣ አንዴ ብሩን ይዤ ዛሬ ዘና ማለት አለብኝ የሚል ሃሳብ ነው ሌላኛው ልቤ ደግሞ ከዚህች ምስኪን እናት ብር ይዞ መጥፋት ከክህደት ሁሉ ትልቁ ክህደት ነው እያለ መውቀስ ጀመረ ቆይ እሺ በዚህ 300ብር እቃ ገዝቼ ስሄድ ትንሽ ብር ብቻ ብሰጠኝስ ብዬም ሐሳብ ውስጥ ገባሁ ልቤ ግን አሁንም ምንም ባይሰጡሽ እንኩዋን እቃውን ገዝተሽ መሄድ አለብሽ ብሎ ትእዛዝ ሰጠኝ እኔም የልቤን ትእዛዝ ተቀብዬ እቃውን ገዝቼ ወደ ቤታቸው ተመለስኩኝ ተመልሼ በመምጣቴ ደስታ ብቻ ሳይሆን ግራ የተጋቡ የሚመስሉት እናት እንዴት መጣሽ? እእእእ ማለቴ ቶሎ መጣሽ ቤት ገብተሽ ቁጭ በይ አሉኝ አይይይ አሁን እሄዳለሁ አልኳቸው ለምን? የት? ብለው ተጣድፈው ከተናገሩ በኋላ ግን አንድ ሁለት ቀን እዚህ ብትቀመጪ ደስ ይለኛል ብለው በትህትና ተናገሩ ኧረ ማዙካ አግኝቼ ነው ሲጀመር እኔ ምን መሄጃ አለኝ በደስታ ነው ቁጭ የምለው ብዬ ቁጭ አልኩኝ ለምሳ ብዬ የገባሁት ቤት የአራት ወር መኖርያ ቤት ሆኖ አገኘሁት። ከአራት ወር በኃላ ሱቅ ተልኬ ስሄድ በአጋጣሚ የሆነ ልጅ መጥቶ ሀይ ሀረግ ብሎ ሰላም አለኝ ሀረግ? እዚህ ሰፈር የኔን ስም ማንም አያውቅም እሱ እንዴት አወቀ እያልኩ ትንሽ በዝምታ ተዋጥኩኝ ምነው ሀረግ አላስታወሽኝም እንዴ? እዩኤል እኮ ነኝ ከጥቂት ወራት በፊት ከመንገድ ላይ አንስተሽ ሃኪም ቤት የወሰድሺኝ ልጅ ብሎ በድጋሚ ሰላም አለኝ ይቅርታ ወንድም ልቤ ሌላ ቦታ ስለነበረ ነው ታዲያ አሁን እንዴት ነህ አልኩት እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ደህና ነኝ፣ ሻይ ቡና ማለት እንችላለን ብሎ ጠየቀኝ አሁን አልችልም ተልኬ ነው የመጣውት አልኩት እና እዚህ ሰፈር ነሽ ማለት ነዋ አለኝ አዎ እዚህ ሰፈር ነኝ አልኩት እኔም እኮ እዚሁ ሰፈር ነኝ አለኝ በቃ ቻው ብዬ ወደ ቤት መጣሁኝ ገበያ ተልኬ ታማኝ በመሆኔ አራት ወር በሙሉ ቁርስ ምሳ እራት ጠግቤ መብላት ጀመርኩኝ ጥሩ አልጋ ላይ ተኝቼ ማደር ጀመርኩኝ ጥሩ ልብስ መልበስ ጀመርኩኝ እነዚህ አሁን ያልኩት ነገሮች ታማኝ በመሆኔ ካገኘውት ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው። ከቀኑ ስድስት ሰአት አካባቢ የግቢው በር ተንኳኳ... እኔ እዚህ ቤት ከገባሁበት ቀን እስከዛሬ እዚህ ቤት ሰው መጥቶ አያውቅም ምስኪኗ እናት ደግሞ ቤት ውስጥ ናት ማነው ብዬ በር ለመክፈት ሄድኩኝ በሩን ስከፍት.

ማነው ብዬ ሄጄ በሩን ስከፍት.. እዩኤል? እንዴት መጣህ አልኩት እእእእእእ ታምራት የለም አለኝ ታምራት ታምራት? ማነው ደግሞ ታምራት አልኩት ኦኦኦኦኦ ለካ ቤት ተሳስቼ ነው የመጣሁት ብሎ በተረፈ እንዴት ነሽ አለኝ ደህና ነኝ አልኩት እንዲህ እንዲህ እያለን ከእዩኤል ጋር ጥሩ ጓደኛሞች ሆንን.. ቤት ተሳስቼ ነው የመጣውት ያለኝ ቀን ለካ ውሸቱን ነው ሱቅ የተገናኘን ቀን ተከትሎኝ መጥቶ ነው ቤቱን አይቶ ተመልሶ የሄደው እዩኤል በጣም የዋሀ መልካም ልጅ ነው በጓደኝነት ብዙ መቆየት አልቻልንም ጓደኝታችን ቶሎ ወደ ፍቅር ተቀየረ... የእዩኤል እናት በህመም መሰቃየት ከጀመሩ ብዙ አመታትን አስቆጥረዋሉ የእናቱን ሙሉ ኃላፊነት ከልጅነቱ ጀምሮ በእጁ ላይ ይዞ ያደገ ምስኪን ልጅ ነው ህይወቱ ከእኔ ህይወት ጋር ብዙ ተመሳሳይ ነገሮች ያሉት እዩኤል ከራሱ እድገት አንጻር ለኔ ያለው ክብር እጅግ በጣም ደስ ይለኛል አንድአንድ ጊዜ የልቤን ሃሳብ ሁሉ የሚያውቅ ይመስለኛል እኔም ህይወቴን ከመንገድ ላይ አንስተው ዛሬ እንደዚህ በደስታ እንድኖር ካደረጉኝ እናቴ ጋር አብሬ በደስታ እየኖርኩኝ ነው ለዚህች ምስኪን እናት ልጅ ይሁን ዘመድ የሚባል ነገር የላቸውም አሁን ግን እሳቸውም ልጅ እኔም እናት አግኝተን በደስታ እየኖርን ነው። እዩኤል አልፎ አልፎ ልክ እንደ እናቱ ሁሉ በህመም እየተሰቃየ ነው ጥሩ ሃኪም ቤት ሄደው ጥሩ ህክምና የማግኘት እድል ግን አልነበረውም፣ አንድ ቀን ቤት ውስጥ ቁጭ ብዬ ቴሌቭዥን በማየት ላይ እያለሁ ስልክ ተደወለልኝ የእዩኤል ስልክ ነው እኔም በደስታ ሀይ ፍቅር አልኩት እዩኤል አይደለም እናቱ ነኝ ቶሎ ብለሽ ድረሽ ታውቂያለሽ እኔ እንደሆንኩ አቅም የለኝም አሉኝ እማማ እዩኤል ምን ሆነ ስላቸው አሁን ጥያቄው ምንም አያደርግም ቶሎ ብለሽ ቤት ነይ አሉኝ እኔም በፍጥነት ቤታቸው ሄድኩኝ፣ እዩኤል እራሱን ስቶ ወድቆ ነበረ.... ቶሎ ብዬ ታክሲ ጠርቼ ወደ ሃኪም ቤት ወሰድኩት ከብዙ የፀጥታ ሰአታት በኋላ እዩኤል በድጋሚ ማውራት ጀመረ... እዚህ አለም ላይ አለኝ የምለው እዩኤል እንደዚህ ሆኖ ከማየት በላይ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር ምን አለ? ሀረግ አሁን እኮ ደህና ነኝ ይላል የሆዱን በሆዱ ይዞት ሁሉም ሰው የፍቅረኛውን ደስታ ይፈልጋል አይደል እሱም ለኔ ደስታ ብሎ ህመሙን ቀላል ለማድረግ እየሞከረ ነው ህመሙ በጣም ከባድ እንደሆነ ግን ሃኪሙ ነግሮኛል ዛሬ መልካሙን ዶክተር የተገናኘውበት ቀን ናት ለህክምናው የጠየቀኝ ብር በጣም ብዙ ብር ነው በኪሴ ውስጥ የነበረኝ ብር ደግሞ በጣም ጥቂት ብር ነው ይቅርታ አድርግልኝ ለጊዜው ሙሉ ብር የለኝም ልጁ እዚሁ ይቀመጥ እኔ ብሩን ይዤ እመጣለሁ አልኩት አይይይይ ችግር የለም ባይሆን ልጁ ክትትል ይፈልጋል ክትትል
ይቀጥላል ...
973 views·.·★ 𝕜𝕖𝕪𝕒 ★·.· , edited  20:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-24 23:39:25
ክፍል ሁለት
859 views·.·★ 𝕜𝕖𝕪𝕒 ★·.· , 20:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-22 23:48:28 ​​ መልካሙ ዶክተር

ክፍል አንድ ➊

አዘጋጅ ሰሊና

ስሜ ሀረግ ነው፣ ሀረግ የሚለውን ስም ማን እንዳወጣልኝ እንኳን አላውቅም ሀረግ የሚለው ስም ለኔ ብዙ ትርጉም ይሰጠኛል አንድ አንድ ጊዜ የሆነ ሰው ጥሎኝ ልሄድ ተክሎኝ የሄደ ዛፍ እንደሆንኩ ይሰማኛል ፍሬ የሌላ ዛፍ! የብቸኝነት ህይወት እንደዚህ ከባድ ነው ብሎ ለሌላ ሰው ለማስረዳት እንደዚህ ነው ብሎ ምሳሌ የሚሰጡት ነገር እንኳን ሊኖር አይችልም። ሁሉ ሰው ወደዚህች አለም ሲመጣ ተመሳሳይ ነገር ነው ይዞ የሚመጣው ከዚህ አለም ሲሄድም ተመሳሳይ ነገር ነው ይዞ የሚሄደው ነገር ግን በዚህች አለም ላይ ሁሉም ሰው የተለየያ ህይወት ይኖራል አንዱ የአንዱን ህይወት መኖር በፍጹም አይችልም ምክንያቱም የዚህች አለም ኑሮ መሪዋ እድል በምንለው ነገር የተያዘች ናትና፣ እሱ ወደፈለገበት እንጂ እኛ መሄድ የምንፈልግበትን ቦታ መሄድ አንችልም። ማንም ሰው ከእናቱ/ከአባቱ ተለይቶ መኖር አይፈልግም ግን ብቸኛ ሆኖ ይኖራል፣ ማንም ሰው አካለ ስንኩል ሆኖ መኖር አይፈልግም ግን በግድ ሆኖ ይኖራል፣ ማንም ሰው ድሃ ሆኖ መኖር አይፈልግም ግን ድሃ ሆኖ ይኖራል፣ ማንም ሰው በህመም እየተሰቃየ መኖርን አይፈልግም ግን ብዙ ሰዎች በህመም እየተሰቃዩ ይኖራሉ ፣ ለዚህም ነው ህይወት የምርጫ ጉዳይ ሳትሆን እድል ላይ የተሰራች ቤት ነው ያልኩት በዚህ አለም ላይ አብዛኛው ነገር ለሰዎች በተናጥል ተሰጥቷል ለሁሉም ሰው እኩል የተሰጠ ነገር ቢኖር " ፍቅር " ብቻ ነው! በዚህ ምድር ላይ ለሁሉም እኩል የተሰጠ ስጦታ ፍቅር ብቻ ነው ህጻን ይሁን ሽማግሌ፥ ሴት ይሁን ወንድ፥ ቆንጆ ይሁን አስጠሊታ ፥ሁሉም ሰው የፍቅር ስጦታውን ተቀብሏል፣ ምንም እንኳን ስጦታውን በአግበቡ የሚጠቀሙ ሰዎች በጣም ጥቂቶች ቢሆኑም ቅድም እንዳልኩት ሁሉም ሰው የፍቅር ስጦታን ከፈጣሪ ዘንድ ተቀብሏል።
የኔ የፍቅር ታሪክ የሚጀምረው በአንድ መጥፎ አጋጣሚ ቢሆንም አጋጣሚው ግን በድንገት ህይወቴን ቀይሮ አየሁት
ፈጣሪ ህይወትህን ለመቀየር ሲፈልግ ሰው ይልካል እንጂ እሱ አይመጣም ሰይጣንም ቢሆን ህይወትህን ለማበላሸት ሲፈልግ ሰው ይልካል እንጂ እሱ በተግባር አይመጣም ልዩነቱ ፈጣሪ መልካም ሰው ይልካል ሰይጣን ደግሞ ክፉ ሰው ይልካል እንደ አጋጣሚ ሆኖ ለኔ የተላከው ሰው መልካም ሰው ነበረ እዩኤል እኔ እንደዚህ ነው ብዬ ከምነግራችው በላይ መልካም ልጅ ነው ከምንም በላይ ለኔ ለብቸኛዋ ምስኪን ልጅ ወንድም እናት አባትም ጭምር ነው እዩኤልን የተዋወኩት ድሮ ድሮ የጎዳና ልጅ እያለሁ ነበረ አንድ ቀን መንገድ ላይ መሬት ላይ ወድቆ ሰው ሁሉ ዝም ብሎት እያለፈ አይቼ ኪሴ ውስጥ ለምሳ ሰርቄ በያዝኩት ብር ሃኪም ቤት ወሰድኩት ሃኪም ቤት ውስጥ የካርድ ብር አጥቼ ወዲህ ወዲያ ስል............

ሃኪም ቤት የካርድ ብር አጥቼ ወዲህ ወዲያ ስል አንዲት
መልካም እናት ልጄ ሰው ጠፍቶብሽ ነው ወይ ብለው ጠየቁኝ እኔም የሆነውን ነገር ሁሉ በትህትና ነገርኳቸው፣ እርሳቸውም አይዞሽ ልጄ አንቺ መልካም ልጅ ነሽ የካርዱን ብር እኔ እሰጣችኋለሁ ግን የህክምና ብር አለሽ ወይ ብለው ጠየቁኝ
ማዘር እኔጋ ምንም ብር የለም ምናልባትም ልጁ ቀድሞ
እራሱን ቢያውቅ ስልክ ቁጥር ተቀብለን ለቤተሰቦቹ መደወል
እንችል ነበረ አልኳቸው
መልካም ብለው እርሳቸውም ከእኔ ጋር አብረው የልጁን ሁኔታ
ለማየት ቁጭ አሉ
ዶክተሩ የመጀመሪያ እርዳታ ከሰጠ በኋላ ለጊዜው ብዙ
አሳሳቢ ችግር እንደሌለበት ነገር ግን እራሱን ከጭንቀት ነጻ
ማድረግ እንዳለበት ነግሮት አንድአንድ መድሃኒቶችን ሰጥቶ
ትንሽ ብር ሲጠይቅ እኔ ቶሎ ብዬ ቤተሰብ ጋር ልደውል ስልክ
ቁጥር ስጠኝ አልኩት
ከዝምታ ሌላ ምንም መልስ መስጠት አልቻለም
በዚህን ጊዜ ከልጁ ዝምታ የሆነ ነገር መረዳት የቻሉት እናት
ከቦርሳ ውስጥ አውጥተው ሃኪሙ የጠየቀውን ብር ሰጡ
በጣም ደስ አለኝ ግን ምን አይነት መልካም እናት ናቸው?
ከዛም ልጄ እኔ አሁን ወደ ቤት ልሄድ ነው እናንተም ወደ
ቤታችሁ ተመለሱ ይሄ የታክሲ ብር ነው ብለው ብዙ ብር ሊሰጡ
ሲሉ እማማ እኔ ምን ቤት አለኝ ብለው ነው ለኔ የሄድኩበት ሁሉ
ቤቴ ነው የትም ሰፈር ብሄድ መኖር እችላለሁ ብሩን ለሱ
ስጡት አልኳቸው ልጄ ምን እያልሽ ነው ቤት የለኝም ማለት ምን ማለት ነው?
ቤተሰብ አለሽ አይደል ብሎ ጠየቁኝ እማማ ለካ እርስዎም ቀልደኛ ኖት ቤተሰብ ቢኖረኝ ይሄን
እመስላለሁ ብዬ ጥዬ ልሄድ ሲል ታዲያ ወዴት ነሽ ብለው ጠየቁኝ
ወዴት ነኝ? እኔን ከየት ነሽ ብሎ እንጂ ወዴት ነሽ ብሎ ሰው
ጠይቆ አያውቅም ምክንያቱም እኔ እግሬ ወደ መራኝ መሄድ
እንጂ እዛ እሄዳለሁ ብዬ መንገድ አልጀምርም አልኳቸው
ታዲያ ለምን ዛሬ ከእኔ ጋር አትሄጅም አሉኝ ቡሌ ይስጡኝ እንጂ የትም እሄዳለሁ አልኳቸው
ቡሌ ደግሞ ምንድነው ሲሉኝ
እማማ ምሳ አልበላሁም አልኳቸው
ልጁን አንተስ አትሄድም አሉት
እማማ እርሶ በጣም መልካም እናት ኖት ስለ ሁሉም ነገር
በጣም አመሰግናለሁ እግዚአብሔር ያክብሮት እኔ አሁን ቤት መሄድ እፈልጋለሁ እናቴ ትጠብቀኛለች ብሎ ልሄድ ሲል
ታዲያ ምስጋናው እኮ ከእኔ በላይ አጠገብህ ለቆመች ልጅቷ
ነው መሆን ያለበት እሷ እኮ ናት ከመንገድ ላይ አንስታ ሃኪም
ቤት የወሰደችህ አሉት
እሱም ወደ እኔ መጥቶ በመጀመሪያ ይቅርታ አድርግልኝ
ሃኪም ቤት የወሰድሽኝ አንቺ እንደሆንሽ አላወኩም ነበረ
በመቀጠል ደግሞ በጣም አመሰግናለሁ ስሜ እዩኤል ነው
ብሎ እጄን ጨበጠ
እኔም ሀረግ አልኩትና ለትንሽ ሴኬንዶች ሁለታችንም ፍዝዝ
ብለን ቀረን
በዚህ መሃል በይ አሁን እንሂድ እሱም ወደቤት ይሂድ ብሎ
እኔን ወደቤታቸው ይዘውኝ ሄዱ
ቤታቸው ደረስን፣ ቤት ውስጥ ለጊዜው ሌላ ሰው አልነበረም
ልክ ቤት እንደገባን የእጅ ውሃ ሰጥተውኝ ተሰርቶ ከተቀመጠው ምግብ አምጥተው ሰጡኝ
እኔም ተገኘ ብዬ ልጀምር ስል ቆይ ልጄ ምግብ ከመብላትሽ በፊት የሰጠሽን አምላክ ማመስገን አለብሽ ብለው አመስግነው
ሰጡኝ ምግቡን ግማሽ ካደረኩ በኋላ የእሳቸው ነገር ትዝ አለኝ
እማማ እርስዎ አይበሉም አልኳቸው እሺ መጣሁ አሉና ሌላ ምግብ አምጥተው ጨምረው ከእኔጋ አብሮ መብላት ጀመሩ
ይህች ቀን በህይወቴ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ ሰዎች ክብር
የሰጡኝ ቀን ነበራች
ምግቡን ጨርሼ እማማ አመሰግናለሁ ብዬ ልሄድ ስል...... ይቀጥላል!

​​​​​​​​╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝

ሀሳብ በግል ለመስጠት @dkeya
• ₊° ✧︡ ˗ ˏ ˋ ♡ ˎˊ ˗ »»— ★ ——

ለአስተያየት ለውይይት @coldcommnt
★━━━━━━━━━━━━★
:¨· .·¨ :
`· .የ ፍቅር ቃል★° *゚ ተቀላቀል ክፈት

╔═ .✵. ══════════╗
@YEFKI @YEFKI @YEFKI
╚══════════ .✵. ═╝
992 views·.·★ 𝕜𝕖𝕪𝕒 ★·.· , edited  20:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-22 23:45:54
መልካሙ ዶክተር


ክፍል አንድ
850 views·.·★ 𝕜𝕖𝕪𝕒 ★·.· , 20:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-04 00:32:12 ​​​​ ❖የመጨረሻ ክፍል❖

ሚስጥራዊ ሚስት



የሴቶች ሽንት ቤት? ብላ በፍጥነት ሄደች፣እኔም ተከተልኩኝ መቅዲም በሁኔታችን ግራ ተገብታ ተከተለችን..ልጅቷ ሽንት ቤት ከደረሰች በኋላ በሩን ማንኳኳት ጀመረች..ከዝምታ ሌላ መልስ ግን አልነበረም ደስታ ደስታ እያለች በሩን መደብደብ ቀጠለች
አሁንም ከዝምታ ሌላ መልስ አልነበረም ጩኸት የሰሙ ሰዎች ሁሉ መሰብሰብ ጀመሩ
ቤቱ በውስጥ ተቆልፎ ስለነበረ በሩ አይከፍትም፣ባለቤቱ መጥቶ ምንድነው ምንድነው ሲል እኔ ፈጥኜ የሆነች ልጅ ራሷን ልታጣፋ ገብታ ነው በፍጥነት በሩን ክፈቱ አልኩኝ
ሰው ሁሉ ነብስ ለማዳን ብሎ በሩን በግድ ሰብረው ቤት ገቡ
ምኑን አዳኑት ገደሉት እንጂ!
ግማሹ ይስቃል ግማሹ ይሳደባል እኔ በደስታ ብዛት ስክር ብዬ ልወቅድ ሁሉ እየሆንኩ ነው፣
ደስታ ሁሌም እዚህ ክፍል አምጥቶ የሚያቀበጥራት ቺክ ቢላዋ ቢኖር መውጋት ሁሉ የምትተው አይመስለኝም
እኔን የገረመኝ ግን የሷ ነገር ሳይሆን የመቅዲ ዝምታ ነው
ጭራሽ ጆን ና ወደቤት እንሂድ አለችኝ እሺ ብዬ መኪና ውስጥ ገብተን ጉዞ ቀጠለን....
አይዞሽ መቅዲ ይኼ ባለጌ! እኔ እኮ በቀደምም ብዬሽ ነበረ አንቺ ነሽ እምቢ ያልሺኝ ብዬ ሳልጨርስ ስለ ደስታ ከአንተ በላይ አውቃለሁ አለችኝ እንዴት ብዬ ስጠይቃት የደስታ ፍቅረኛ የትምህርት ቤት ጓደኛዬ ናት ሁሉንም ነገር ትነግረኝ ነበረ አለችኝ፣እና ይኼን ሁሉ ጉድ እያውቅሽ ነው የምትወጅው አልኳት? ባክህ እኔ እሱን አልወደውም እኔ እኮ ከአምስት አመት በላይ ሚስቱ ሆኜ የምኖርለት ባል አለኝ ብል ሳቀች
ምን
እኮ ማነው? የት ነው የሚኖረው አልኳት አየህ ችግርክ ማስተዋል አትችልም ይኼን ሁሉ አመታት የራስህን ስጦታ ለሰው ለመስጠት ግጥም ጽፈህ እየሰጠህ ሆቴል ይዘህ እየሄድክ ኖረካል እኔም ላንተ ደስታ ጅል ሆኜ ሁን ያልከውን ሁሉ እየሆንኩልህ ነበረ ከእንግዲህ ወዲህ ግን እንደዚህ ነገር ብትሞክር ራሴን ነው የማጠፋው አለችኝ ምን? እኮ አንቺ የኔ ምስጢራዊ ሚስት?
ኖ አይሆንም!ከአፌ እንዴት እንደወጣ ሳላውቅ ራስሽን አታጥፊ እኔ እኮ በጣም እወድሻለሁ ላንቺ ደስታ ስል አይደል እኔስ ይኼን ሁሉ የሆንኩት አልኳት እኮ ባሌ ነህ አይደል አለችኝ ኖ ኖ ወንድምሽ ነኝ በእህትነት ነው የምወድሽ አልኳት
ከመኪናው ውረድ አለችኝ
ለምን አልኳት ውረድ አልኩህ እኮ ስትለኝ... መቅዲ ምን መሰለሽ ብዬ ሳልጨርስ ሽጉጥ ከየት እንደሆነ አውጥታ አናቷ ላይ ደቅና አሁን አትወርድም አለችኝ?
እሺ እወርዳለሁ ግን ይኼን ነገር መሬት ላይ አስቀምጪ አልኳት
በራሴ ህይወት ላይ ምን አገባህ? የሚያገባህ የምታዝን ቢሆን በአምስት አመት ውስጥ ትክክለኛውን ስሜት ማወቅ በቻልክ ነበረ እውነታው ግን እኔ ላንተ ምንም አላደርግ የኔ መኖር ላንተ ምንም ጥቅም የለውም!!
እኔ ደግሞ ካንተ ተለይቼ መኖር አልፈልግም አለችኝ ሰውነቴን ምን አይነት መንፈስ እንደተቆጣጠረ አላውቅም እኔም እኮ እውድሻለሁ እኔም እኮ ካንቺ ተላይቼ መኖር አልፈልግም ብዬ ከንፈሯን በድንገት ሳምኩኝ
ጅል ነህ እሺ እንደዚህ አትልም ብላኝ እሷም ምላሽ ሰጥታችኝ
የራስ የሆነ ነገር ያው የራስም ነውና አምስት አመታትን ፍቅሬን ለሰው ለመስጠት ቀና ደፋ ብዬ መጨረሻው ላይ እኔው ራሱ ተጠምጄ ቀረሁኝ
አንድ አንድ ጊዜ ሰዎች ልክ እንደ መቅዲ ሁን ያልከውን ነገር ሁሉ የሚሆኑት አድርግ ያልከውን ነገር ሁሉ የሚያደርጉት ስላማያውቁ ሳይሆን አንተን ስለሚወዱ ላንተ ደስታ ብለው ነው!!
በህይወት ጉዞ ላይ እና በሩጫ ውድድር ላይ ማንም ሰው ከየት እደሚነሳ እንጂ እንዴት እንደሚጨርስ እርግጠኛ መሆን አይችልም! ስለዚህ መጨረሻ ላይ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ስለማታውቅ መጨረሻህን ዛሬ ላይ ሆነህ አትገምት፤ በህይወት ውስጥ እንደ እኔ ቸልተኛ አትሁን፣ ሁሌም አስተውል እኔ ባለማስተዋል በአንድ አመት ውስጥ የማገኛትን መቅዲን ለማግኘት አምስት አመት ጠብቄለሁ፤በዙሪያ ያሉትን ነገሮች ምንም ጥቅም እንደሌለ አድርገህ ሩቅ ሩቅ ብቻ አትመልከት፣ መልካም ነገሮችን ለመፈለግ ሩቅ ሩቅ ቦታ ብቻ አትሂድ መጀመሪያ አጠገብህ ያሉትን ነገሮች በማስተዋል ተመልከት!
የትላንቱ ወዛደር የዛሬው ሀብታም እና የአንድ ልጅ አባት ጆን!!
➠❖ተፈፀመ➠❖

ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ @dkeya
ˢᵘᵖᵖᵒʳᵗ ᵘˢ መልካም መሆን ዋጋ አይጠይቅም!

ለአስተያየት ለውይይት @coldcommnt
★━━━━━━━━━━━━★
:¨· .·¨ :
`· .የ ፍቅር ቃል★° *゚ join open

╔═ .✵. ══════════╗
@YEFKI @YEFKI
╚══════════ .✵. ═╝

በቅርብ በሌላ አጓጊ ታሪክ ይጠብቁን።
1.1K views·.·★ 𝕜𝕖𝕪𝕒 ★·.· , edited  21:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-04 00:30:31 ​​ ሚስጥራዊ ሚስት
┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉
ክፍል
┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉
አቅራቢ ሰሊና( የብዕር ስም )
┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉
....ምን ችግር አለው ቅዳሜ ማታ ሦስታችንም አብረን እንቀውጣለን ዛሬ ግን እኔ እና አንተ ለብቻችን እንቀውጣለን አለኝ ዋውውው በጣም ደስ አለኝ ዛሬ የጉድ ምሽት ይሆናል.. አመሻሽ አከባቢ እኔ እና ደስታ እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ ተለመደው መጠጥ ቤት ሄደን...
እድለኛ ከሆንኩ ዛሬ ጉዱ ይወጣለታል ጥያቄው ፍቅረኛው ትመጣ ይሁን የሚለው ነው?
እስኪ እሱን አብረን እናያለን ደግሞ ትመጣለች የሚል እምነት አለኝ ምክንያቱም ደስታ እኔን በምንም መልኩ እንደይጣራጥር ሙሉ በሙሉ ሃሳቡን የሚቀይር ነገር እኮ ነው የነገርኩት አንድ ጥግ ይዘን ሁለታችንም ቁጭ ብለን መጠጣት ቀጠለን.... ጨዋታው ስለ ሴቶች ነው እኔ ነኝ ከዚህ በፊት እዚህ ቤት ስላወጣዋቸው ሴቶች ቀድሜ መንገር የጀመርኩት፣ ከዛ በኋላ እሱም ልብ ውስጥ ያለውን ሁሉ አብረው አንሶላ ስለተጋፈፉ ሴቶች አንድ በአንድ መናገር ቀጠለ
ይኼ ቀደደ! እኔ እኮ ሴት የሚባል ነገር አላውቅም ለመጀመሪያ በጓደኝነት ቀርቤ የማውቃት ሴት መቅዲ ብቻ ናት የሰውን ከውጪ የሚታየውን ሁኔታ አይተው እሱ እንደዚህ እሷ እንደዚህ ናት አይደለም እሱ እኮ እንደሱ አይደለም ማለት ከስህተት ሁሉ ስህተት መሆኑን ደስታ አስተማረኝ
ከምር ደስታ ማለት እኮ ከውጪ ለሚመለከት ሰው በቃ የቤት ልጅ ምንም ነገር የማያውቅ የሴት አይን እንኩዋን ደፍሮ ማየት የማይችል ልጅ ይመስላል፣ እኔ ደግሞ በታቃራኒው ሁሉንም ነገር የምችለው በነገሮች ሁሉ ብቁ ሴቶችን ቀርቤ ማሰመን የምችል ወንድ እመስላለሁ እውነታው ግን ሌላ ነው፡ አንድ ሁለት እያለን ለካ ብዙ ጠጥታናል፣ አይኔ ውጭ ውጭውን በማየት ላይ ነው፣ እስከአሁንም ፍቅረኛው አልመጣችም በእግዚአብሔር ቶሎ ብለሽ ነይ እያልኩኝ ነው፣ እሷ ግን መምጣት አልቻለችም ቀስ ብዬ የደስታን ስልክ ከጠራጴዛ ላይ አንስቼ ለፍቅረኛው የኔ ፍቅር የት ነሽ እኔ እዛው የተለመደው ቦታ ነኝ በጣም ናፍቅሸኛል ከናፍኩሽ በፍጥነት ድረሽ ብዬ ሚሴጅ ላኩኝ
ደስታ ግን የሷን አለመምጣት እንደ ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅሞ ውብ እና ቀውጢ የሆናች አንዲት ሴትን ይዞ ቤቱን አብረው ቅውጥ እያደረጉ ነው፣ቆይ ግን ሴቶች ለምንድነው ደስታን እንደዚህ የሚወዱት?
እሱ አጠገብ ሲደርሱ ሁሉም በአንዴ እንደ ቅቤ ቅልጥ ይላሉ፣
በልቤ ዛሬ ይቺን ውብ ልጅ ማውጣት ከቻለ የእውነትም ይችላል ብዬ ሳልጨርስ እዛው ከንፈሩን መሳም ጀመረች
የዛሬዋ ደግሞ ምኗ ጉዳኛ ናት እባካችሁ ከዛም ትሼርቱን ይዛ ወደ ተለመደው ክፍል ወሰደችው
የሚገቡበትን ክፍል ካየው በኋላ ለመቅዲ ደውዬ መቅዲ በጣም አሞኛል እባክሽን የበላፈው መጠጥ ቤት በፍጥነት ድረሽልኝ ብዬ ስልኩን ዘገውት፤ ስልክ ስትደውል አውቄ ዝም አልኩኝ
አምላኬ ሁለቱም በአንዴ እንዲመጡ አድርግ እያልኩ እኔንም የፍርሃት ይሁን የደስታ ብቻ አላውቅም ሽንቴ ወጥሮኛል
የደስታ ፍቅረኛ መጣች...
አይኗ ውሃ የጠማው ውሻ ይመስላል አይኗን ዞር ዞር እያደረገች ቤት ውስጥ ደስታን መፈለግ ቀጠለች፣እሱ ግን ቤት ውስጥ የለም: በዚህ መሃል መቅዲ መጣች
ዬስስስስስስስስስ ጆን ምን ሆንክ እያለች መላ ሰውነቴን መበርበር ጀመረች... ነይ የሆንኩትን ለሳይሽ ብዬ እጇን ይዤ ልወስደት ስል ባክህ ልቀቀኝ ትቀልዳለህ እንዴ? አንተ በሰው ህይወት መቀለድ ድሮም ትወዳለህ፣እኔ እኮ የእውነት አመመኝ ያልከኝ መስሎኝ መኪናውን በምን አይነት ፍጥነት ይዤ እንደመጣው የማውቀው እኔ ነኝ አንተ ግን ትቀልዳለህ አይደል ብላ ጥላኝ ሊትሄድ ስትል እሺ ደስታ የት እንዳለ ታውቃለሽ? አልኳት ደስታ የሚለውን ቃል ሲሰሙ ሁለቱም ሴቶች ደነገጡ
ሁለቱም የኔው ደስታ አሉኝ
አዎ የሁላችውም ደስታ አልኳቸው
መቅዲ ማነሽ የኔ እህት ባክሽ ወደ ቤት ሂጅ ልጁ እብድ ነው አለቻት
ልጅቷ ግን አይደለም እዚህ ነኝ ብሎ ሚሴጅ ልኮልኝ ነበረ እኮ ማነህ አንተ ደስታ የት ነው አለችኝ
የባለፈው ሽንት ቤት አልኳት
የሴቶች ሽንት ቤት? ብላ በፍጥነት ሄደች እኔም ተከትዬ ሄድኩኝ መቅዲም በእኛ ሁኔታ ግራ ተጋብታ ተከተለች

LIKE እና SHARE ማድረግ እንዳይረሱ አስተያየት ካላችሁ @dkeya ላይ ይፃፉልን !!!
931 views·.·★ 𝕜𝕖𝕪𝕒 ★·.· , edited  21:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-04 00:27:38
ክፍል አስራ ስድስት እና የመጨረሻው ክፍል
794 views·.·★ 𝕜𝕖𝕪𝕒 ★·.· , edited  21:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ