Get Mystery Box with random crypto!

ኮከብ ቆጠራና ጥንቆላ—የወደፊቱን ጊዜ ለማወቅ ያስችላሉ? በፍቅር ወፈን የቀረበ ኮከብ ቆጠራ | የፍቅር ወላፈን

ኮከብ ቆጠራና ጥንቆላ—የወደፊቱን ጊዜ ለማወቅ ያስችላሉ?

በፍቅር ወፈን የቀረበ


ኮከብ ቆጠራ (zodiac sign) ክፍል አንድ

ኮከብ ቆጠራ የሚባለው ከዋክብት፣ ጨረቃና ፕላኔቶች በምድር ላይ ባሉ ሰዎች ሕይወት ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ያሳድራሉ በሚለው እምነት ላይ የተመሠረተ የጥንቆላ ዓይነት ነው። ኮከብ ቆጣሪዎች፣ እነዚህ የሰማይ አካላት አንድ ሰው በተወለደበት ወቅት ያላቸው አቀማመጥ የግለሰቡን ባሕርይና የወደፊት ዕጣ እንደሚወስን ይናገራሉ።

ኮከብ ቆጠራ የተጀመረው በጥንቷ ባቢሎን ቢሆንም አሁንም በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት አለው። በዩናይትድ ስቴትስ በ2012 የተደረገ አንድ ጥናት እንደሚጠቁመው በጥናቱ ከተካፈሉት ሰዎች መካከል አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ኮከብ ቆጠራ “ሳይንሳዊ ሳይሆን እንደማይቀር” ይሰማቸዋል፤ አሥር በመቶ የሚሆኑት ደግሞ “በሳይንስ የተደገፈ” እንደሆነ ተናግረዋል። ግን እውነታው ይህ ነው? በጭራሽ። እስቲ እንዲህ እንድንል የሚያደርጉንን ምክንያቶች እንመልከት።

ፕላኔቶችና ከዋክብት ኮከብ ቆጣሪዎች በሚገልጹት መንገድ በሰዎች ሕይወት ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር የሚያስችል ኃይል የላቸውም።

ኮከብ ቆጣሪዎች ብዙውን ጊዜ ትንቢት የሚናገሩት እንዲሁ በደፈናው ስለሆነ በማንም ሰው ላይ ሊፈጸሙ ይችላሉ።

ኮከብ ቆጣሪዎች በዛሬው ጊዜ የሚጠቀሙበት ስሌት የተመሠረተው ‘ፕላኔቶች የሚዞሩት በምድር ዙሪያ ነው’ በሚለው ጥንታዊ አመለካከት ላይ ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ፕላኔቶች የሚዞሩት በፀሐይ ዙሪያ ነው።

የተለያዩ ኮከብ ቆጣሪዎች ስለ አንድ ግለሰብ የሚናገሯቸው ትንበያዎች አይመሳሰሉም።

ኮከብ ቆጣሪዎች፣ ሰዎችን የተወለዱበትን ቀን መሠረት በማድረግ በ12 የዞዲያክ ምልክቶች ሥር ይመድባሉ። ሆኖም ባለፉት መቶ ዘመናት ምድር በጠፈር ውስጥ የምትገኝበት ቦታ በጊዜ ሂደት ስለተቀየረ በተለያዩ የዞዲያክ ምልክቶች የሚወከሉት ቀናት፣ ቀደም ሲል ስማቸው ከተሰየመበት ኅብረ ከዋክብት ጋር አይጣጣሙም።

የዞዲያክ ምልክቶች ስለ አንድ ሰው ባሕርይ ፍንጭ እንደሚሰጡ ይነገራል። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን በአንድ ቀን የተወለዱ ሰዎች ተመሳሳይ ባሕርይ የላቸውም፤ አንድ ሰው የተወለደበት ቀን ከባሕርይው ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። ኮከብ ቆጣሪዎች የአንድን ግለሰብ እውነተኛ ማንነት ከመመልከት ይልቅ አስቀድመው ያስቀመጧቸውን መላ ምቶች መሠረት በማድረግ የግለሰቡ ባሕርይ እንዲህ ነው ብለው ይናገራሉ። ታዲያ ይህ ፍርደ ገምድልነት አይደለም?

ቀጣይ ክፍል ይቀጥላል..