Get Mystery Box with random crypto!

#ሀርሜ_ኮ : ክፍል-አራት : ...እቤት ውስጥ ማንም የለም …..እኔ ሳሎን ሶፋው ላይ ተመቻ | ❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

#ሀርሜ_ኮ
:
ክፍል-አራት

:


...እቤት ውስጥ ማንም የለም …..እኔ ሳሎን ሶፋው ላይ ተመቻችቼ ተሰትሬ ተኝቼያለው…አንገቴ ከፍ የሚያደርግ ልዩ አይነት ትራስ ከስር ተደርጎልኝ ቀና ብያለው…ፊት ለሰፊቴ ግድግዳ ላይ ለእኔ እይታ እንዲመች ተስተካክሎ የተለጠፈ 32” ሶኔ ፍላት ቴሌቬዝን ላይ አፍጥጬ…. ‹‹ብሬኪንግ ባድ›› የሚል ርዕስ ያለው ተከታታይ ፊልም እያየው ነው…፡፡ያው ከመጽሀፍ ቀጥሎ ፊልም ማየት በጣም የምወደው እና የሚያዝናናኝ የእየ እለት ድርጊቴ ነው..
ስለአለም ያለኝን ግንዛቤ በጣም ያሰፋልኝ የማያቸው የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ፊልሞች ናቸው..፡፡በቀን ቢያንስ 5 ፊልም አያለው..ቢያንስ ነው..እሰከ አስር እና ከዛም በላይ የማይበት ቀን አለ…፡፡ከሁሉም በላይ ግን በእናቴ እና አልፎ አልፎ በወንድሜ የሚነበብልኝ መጽሀፍት ለእኔ ሱሴ ናቸው..
በዚህ ውስብስብ የህይወት ቆይታዬ የተረዳውት አንድ ዋና ፌሬ ነገር ቢኖር መጻሀፍን የሚተካ ምንም ነገር አለመኖሩን ነው…ፊልም፤ኢንተርኔት ምንም ቢሆን ምንም፡፡ መጽሀፍ አዕምሮን እንደሚያዳብር አምናለው….ማንበብ የማሰብ ብቃትን የሚያጠነክር የአእምሮ ስፖርት ነው፡፡መፅሀፍ ስናነብ ቃሉን ወደ አዕምሮችን ልከን ምስሉንና እያንዳንዱን ድርጊት በራሳችን የአዕምሮ ግንዛቤ እና ፍላጎት መጠን አስልተን በራሳችን ዳሬክተርነት አክረተሮችን በምናባችን ፈጥረን ፊልሙን በመስራት የታሪኩን ሙሉ ጭብጥ ለመረዳ እንጥራለን፡፡ይሄ ሁሉ ውጣ ውረድ ታዲያ የማሰብ ብቃታችንን በጊዜ ሂደት ውስጥ ሚያፈረጥምልን የአዕምሮ ቅልጥፍና ማበልፀጊያ ጅምናስቲክ ማለት ነው…..፡፡
ለማንኛውም ሰው ካረዳኝ በራሴ መጽሀፍ ማንበቡ ስለሚከብደኝ አሁን ፊልሙን እያየው ነው እንዲህ አሁን ባለውበት ሁኔታ ሁሉን ነገር አስተካክላልኝ የሄደችው እናቴ ነች…ቤቱ ባዶ ከሆነ ሁለት ሰዓት በላይ ሆኖታል.የቤታችን ተንከባካቢ ትርሲትም እንኳን አስቤዛ ልትሸምት ወደ መርካቶ ከሄደች ቆየች…
አሁን ግን በሩ ሲከፈት ሰማው…ማን እንደሆነ አንገቴን ጠምዝዤ በአይኖቼ ማየት አልችልም…፡፡
ግን በበር አከፋፈቱ እና በእርምጃው ማንነቱን ወዴያው ነው ያወቅኩት…ወንድሜ መሀሪ ነው፡፡አዎ መጥቶ ፊት ለፊቴ ተገተረ..ያው እንደወትሮው ጭብርር እንዳለ ነው….በጥቁር ፔስታል የታጨቀ ዕቃ ተሸክሞ በመምጣት አጠገቤ ካለው ጠረጵዛ ላይ ጎንበስ ብሎ አስቀመጠውና እሱም አጠገቤ ቁጭ በማለት
‹‹ሀይ ወንድሜ?›› አለኝ እንደሁልጊዜው አይኖቼን በማርገብገብ ለሰላምታው ምላሽ ሰጠውት
‹‹ማንም የለም እንዴ?››የግራ እጄን የማሀል ጣት በማወዛወዝ ቤቱ ባዶ እንደሆነ ነገርኩት ፡፡እጁን ወደ ፔስታሉ ሰደደና በፕላስቲክ የታሸገ የመንጎ ጭማቂ አወጣ…ከፈተውና እስትሮ አደረገበት..ከዛ ወደ እኔ አፍ አስጠጋና ጭማቂውን በግራ እጁ ይዞ በቀኝ እጁ እስትሮውን አፌላይ ሰካው ‹‹…በል እንግዲህ እድሜ ለወንድሜ እያልክ ምጠጥ ››አለና ከእስትሮው በተነሳ እጁ ሪሞቱን በማንሳት እያየውት የነበረውን ፊልም ዘጋው‹‹ይቅርታ…አሁን ፊልም ማየት አትችልም …ወይ መጽሀፍ እናነባለን ..ወይም እናወራለን›› አለኝ
ፈገግ አልኩና በሀሳቡ እንደተስማማው ገለጽኩልት..ግማሽ ሊትር የሆነችውን ጅውስ ለመጠጣት ግማሽ ሰዓት ያህል ፈጀበኝ…ያን ሁሉ ጊዜ ወንድሜ ያለምንም መቻኮልና መሰልቸት በቀልድ እያዋዛ ነበር ጅውሱን የመገበኝ፡፡
‹‹በል እንግዲህ አሁን ደግሞ ያራሴን ጅውስ ልጠጣ›› አለና እኔ የጠጣውበትን ባዶ የጅውስ ፕላስቲክ ወርውሮ እጅን ወደ ፔስታሉ ከተተና በለጬ ጫቱን መዞ በማውጣት ጠረጵዛው ላይ አስቀመጠው…አሁንም እጁን በድጋሜ ሰደደና የፕላስቲክ እሽግ ኮካና በወረቀት የታሸገ ለውዝ አውጥቶ እዛው ጠረጵዛ ላይ በመደዳ ደረደራቸው፤ የጫቱን ፔስታል ከፍቶ የጫቱን እስር ፈቶ አንድ ሁለት ቅጠል አወጣና በቄንጥና በፍቅር እየቀነጣጠሰ ወደ አፉ በመውሰድ ይጠቀጥቀው ጀመር…ከዛ ኮካውን ከፈተና ተጎነጨለትና መልሶ አስቀመጠው…ሌላ ጫት መዘዘ ቀነጠሰና ጎረሰው…ለውዙን ፈለፈለእና ወደ አፉ ጨመረ…….ከዛ ከለበሰው ግብዴ ጃኬት ሰፊ ኪስ ውስጥ መፃፍና አወጣና ገለጦ ማንበብ ጀመረ..ሁሌ እስኪግል እንዲህ ነው የሚያደርገው…ለሀያ ደቂቃ ያህል በፅሞና ካነበበ ብኃላ አጣጥፎ አስቀመጠውና ወደ እኔ ዞረ.
‹‹አንድ ነገር ላውራህ እስኪ›› ሲል ጀመረ..ለመስማት ተዘገጀው…ያው ተዘጋጀው ስል ስሜቴን አነቀቃው ማለቴ ነው…ታናሽ ወንድሜ ቀጠለ ‹‹ምን አልባት የምትወደውን ወሬ ላይሆን ይችላል ላወራልህ የተዘጋጀውት..ግን ይሄንን ወሬ ካንተ ጋር ካልሆነ ከሌላ ከማንም ሰው ጋር ላወራው አልችልም..ከእህቶቼም ጋር.. ከእናቴም ጋር..፡፡ለምን? ብትለኝ እኔ እንጃ ነው መልሴ….፡፡ ከእነሱ ጋር ማውራት ከአንተ ጋር እንደማውራ አይቀለኝም..፡፡ምን አልባት አንተ ጥሩ አድማጭ ስለሆንክ ሊሆን ይችላል..ምን አልባት ሁለታችንም ወንድም አማቾች ብቻ ሳንሆን የቤቱም ብቸኛ ወንዶች ስለሆን ሊሆን ይችላል….››አለና ንግግሩን አቆርጦ ፔስታሉን ወደ ራሱ ጎተት አደረገና ጫቱን ከውስጡ መዝዞ ቀነጣጥሶ በመጉረስ በላዩ ላይ ኮካ ተጎነጨለትና ጠርሙሱን አስቀምጦ ንግግሩን ካቆመበት ቀጠለ…‹‹ላወራህ የፈለግኩት ስለአባቴ ነው….ማለት ስለአባታችን…ያው ስለእሱ መስማት እንደማትፈልግ እና እንደማትወደው አውቃለው…እኔም ስለእሱ ሳስብ ግራ የሚያጋባ ስሜት ነው የሚሰማኝ….እርግጥ አልዋሽህም አንዳንዴ ምን አለ አጠገቤ ቢኖር ብዬ እመኛለው....እርግጥ ለእዚህ ቤተሰብ መክፈል የሚገባውን መስዋዕትነት አልከፈለም…..ያ ትልቅ ድክመቱ ነው…ግን ያው ምንም ቢሆን አባቴ ነው….ዝም ብዬ እንዳልተፈጠረ ሰው ልቆጥረውና ልረሳው አልችልም …
አሁን ስለእሱ ላወራህ የቻልኩት አንድ ጽሁፉን ፌስ ብክ ገጹ ላይ አንብቤ ነው..ያው እንግሊዝ ከገባ ቡኃላ ሀይለኛ ፖለቲከኛ ሆኗል….፡፡ ስለዲያስፖር ፖለቲካ ደጋግሜ አውርቼሀለው…አባታችን ከነዛ ተዋናዬች ውስጥ ዋናው ሆኗል..ይግርምሀል ስለአባቴ ብዙ ነገሮቸ ለማወቅ ሞክሬያለው..ማለት ያው ጥሎን ሲሄድ ህጻን ስለነበርኩ እንደ ህልም ነው ሚታወሰኝ..ግን እዚህ ሳለ እንዴት አይነት ሰው ነበር…?ምን አይነት አባት…እንዴት አይነት አስተማሪ…?እንደነበር ከተለያ ሰዎች ለማጣራት ሞክሬያለው…፡፡
እዚህ አገር ሳለ የነበረውን የፖለቲካ ተሳትፎም ለማወቅ ጥሬያለው…..እርግጥ እዚህ እያለ የሆነ ፓለቲካ ድርጅት ውስጥ አባል ነበር..ግን ማንም የማየውቀውና እዚህ ግባ የማይባል ተሳትፎ የነበረው ተራ አባል ነበር…. አሁን በገጹ ላይ የሚጽፋቸው ጽሁፎችን ሳነብ ልክ ከዚህ ሀገር የወጣው የፖለቲከኛ ስደተኛ ሆኖ ከኢህአዲግ የእስር መንጋጋ ሾልኮ በሱዳን በኩል ኮብልሎ በስቃይ አሁን ያለበት ሀገር እንደደረሰ ነው፡፡
እኔም አንተም እንደምናውቀው ሀቁ ግን አባታችን የፖለቲካ ስደተኛ ሳይሆን የኑሮ ስደተኛ እንደሆነ ነው…፡፡ያው ታውቀወለህ ለምን ጥሎን እንደሄደ..እሱ ግን በዲያስፖራው አለም ያለውን ተቀባይነት ለማግዘፍ ‹‹…ስራዬን ለቅቄ ቤተሰቤን በትኜ በስደት አለም ከ15 አመት በላይ የእየባከንኩ ያለውት በዘረኛው መንግስት ምክንያት ነው…››ብሎ የጻፈውን አንብቤ ምን አይነት ውሸታም አባት ነው ያለን ?ብዬ ልታዘበው ችያለው…ግን እንደዛም ሆኖ በሆነ ተአምር ወደ ሀገር ተመልሶ ለአንዴም ሰከንድ ቢሆን ፊት ለፊት በአካል ባየው ደስ ይለኛል..ይገርምሀል እኔ ብቻ አልምሰልህ እናቴም በጣም ትናፍቀዋለች..መአት ቀን ፎቶውን በተመስጦ እየተመለከተች እንባዋን ስታንጠባጥብ ደርሼባታለው …ግን እውነቱን ለመናገር የእናቴ እንባ ለእሱ