Get Mystery Box with random crypto!

ልጩህበት! ክፍል- 13 አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ . . . ተነስተህ በቦክስ ወደ ጀርባው | ❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

ልጩህበት!

ክፍል- 13

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
.
ተነስተህ በቦክስ ወደ ጀርባው ዘርረውና ልጅቷን ይዘኃት ውጣ ውጣ አለኝ።
መሲ ተነስታ ወደ ሽንት ቤት ስትሄድ ከጀርባ ተከተልኳት ! እሷ ከፊት እኔ ከውኋላ ወደ ሽንት ቤት እምትወስደው ቀጭና መንገድ መሀል ላይ እንደደረስን ከጀርብዬ ኮቴ ሳያሰማ ማጅራቴ አከባቢ •••
ኮሌታዬን ቀብ ሲያደርገኝ በድንጋጤ መንጭቄው በፍጥነት ዞርኩ!
"ክክክ አንተ ምነው ? ሊያጠቃኝ ይችላል ብለህ የምታስበው ጠላት አለህ እንዴ?
ተፈናጠርክ እኮ ካካካ•••!"
ኮንትራት የያዘኝ ሰውዬ ነበር። የሚገርመው እራሴ አምጥቼው ሳበቃ እዛ ጭፈራ ቤት የውስጠኛው ክፍል ውስጥ መኖሩን ጭራሽ ረስቼዋለሁ!
ወደ ወንዶች ሽንት ቤት ጎን ለጎን እየሄድን •••
"ደሞ ደክሞኛል ገብቼ ተኛለሁ ባጃጅ ከፈለክ ብለህ ሌላ ስልክ ሰጥተከኝ አልነበር እንዴ የሄድከው ነው ወይስ ሞባይሉን ሰጠኸኝ ስትወጣ አንዷ ጠልፋህ ነው? መሆን አለበት ! እዚ ቤት ያሉ ሴቶች እኮ ልዩ ናቸው እንኳን
እዚህ ድረስ እራሱ የመጣውን ሰው በአየር ላይ ፖይለቱን አማሎ አውሮፕላን ለመጥለፍ ወደኋላ የማይል ውበት ነው ያላቸው ቆይ የጭፈራ ቤቱ ባለቤት የቁንጅና ውድድር አዘጋጅቶ ከአንድ እስከ አምስት የሚወጡትን ነው እንዴ የሚቀጥረው! ካካካ!"
ኧረ መቆለል አልኩና በሆዴ !
ኧረ አይደለም ባጋጣሚ ነው አልኩት ሸንተን ስንመለስ•••
"ምኑ ነው አጋጣሚ ቆንጆዎች መሆናቸው?"
አይ የኔ እዚህ መከሰት!
"እና ብቻህን ነህ ብቻህን ከሆንክ ለምን ውስጥ እኔጋ አለመጣህም " እያለ አቁሞ ሲነዘንዘኝ መሲ ከሽንት ቤት ወጥታ እየተውረገረገች ባጠገባችን አለፈች። አፈጠጥኩባት ።
እሱም በሚስቁት አይኖቹ እኔ ላይ አፈጠጠብኝ ።
"ተመለስክ?!"
ኬት ?
"ከልጅቷ ላይ ነዎ!"
አዎ አልኩት ፈገግ ብዬ !
በል ና እሄንን እማ እየጠጣን ነው መስማት የምፈልገው ናናናና !" እያለ እጄን እንደያዘ ወደ ውስጥ ገባን።
እዛ የተገኘሁበትን እውነት ልንገረው? አልንገው ? ብነግረውስ ምን ብዬ ልንገረው? ምናልባት ጥሬ እውነቱን እንደወረደ ስነግረው ምናልባት እኔን የተሰምልኝ ስሜት ካልተሰማው•••
"ቆይ ከልጅቷ ጋር ዘመድ ናችሁ?"
ኧረ አይደለንም ።
"ትውውቅ አላችሁ ማለት ታውቃታለህ ?"
አይ!
"እሺ ቆይ ልጅቷን ወደሀታል?'
ኧረ በጭራሽ!
"ታድያ ምን አግብቶህ ነው እዚህ ሁሉ ፈተና ውስጥ እራስህን የምትከተው?!" ቢለኝስ!
እኔ የሴቶች እህቶቼ ጉዳትና ጥቃት እንደሚያገባኝ አምናለሁ ይሄ የሚያገባቸው የማይመስላቸው እሄን ምን አገባኝ እያሉ ነገር ግን በማያገባቸው ብዙ ነገሮች ውስጥ እጃቸውን የሚያስገቡ ሰዎች በዙርያችን ብዙ ናቸው።
የሴት ጥቃት አይመለከተኝም እያሉ የአርሰናል መጠቃት የሚያደባድባቸው በሞሉባት ሀገራችን
አላውቃትም!
ዝምድናም የለንም!
አልወደድኳትም!
እያልክ ለሷ መቆም እንቆቅልሽ የሚሆንበትና ምን አገባህ የሚልህ ቢያጋጥምህ ምን ይገርማል?!
ምንም!።
ስለዚህ ምን ልበለው? በቀላሉ የሚፋታኝ አይመስለኝም ።
"ምናገባህ!" እንዳይለኝ ትንሽ ቀየር አድርጌ ልነግረው ወሰንኩና•••
ይሄውልህ ቅድም ሞባይሉን ሰጥቼህ ስወጣ የአንደኛ አመት የዩንቨርስቲ ተማሪ የሆነችውን የአክስቴን ልጅ ከማይሆን ሰው ጋር አየኋት!
ከኔ ጋር ከተጣላን አመት ሆኖናል። ተኮራርፈናል። አንነጋገርም ግን ብንጣላም ስለሰውየው በደንብ ስለማውቅ ጥያት በጭራሽ አልገባም ልጅቷ እንደዚህ አይነት አመል የላትም እርግጠኛ ነኝ ቅድም የገላመጥኳት ልጅ በሆነ መንገድ ሸውዳ አምጥታለት ነው •••
አልኩና ስለመሲና ስለሰውየው በዝርዝር ነገርኩት።
እሄን ግዜ ሰውየው ከኔ በላይ የተቆጣ ነብር ሆኖ ቁጭ አለ። ፊቱ ተለዋወጠ።
"በቃ ይሄን ጉዳይ ለኔ ተወው አንተ ዝምበልና ቁጭ ብለህ ጠጣ!"
ማለት ምን ልታደርግ ነው?!
"ዝም ብለህ ጠጣ! ብዬሀለሁ ዝም ብለህ ጠጣ!" አለኝ ክርድድ ባለ ድምፅ።
ድሮም ነገረ ስራው ግራ ነበር የሚገባኝ አሁን ደግሞ ባንዴ ሲለዋወጥብኝ እኔ እራሴ ፈራሁት ።
ካጠገቤ ሄዶ እነመሲን ከሩቁ አይቷቸው ተመለሰ።
ከደቂቃዎች በኋላ ከነመሲ ጋር ያለው ሰውዬ ቦርጩን እያሻሸ ወደ ሽንት ቤት ሲያልፍ እኩል እየነው! ተያየን••
"እሄ አሁን ያለፈው ነው አደለ?
"አዎ ግን ምን ልታደርግ ነው?
"አቢቲ አማርኛዬ አልገባ ካለህ የፈለከውን የሚገባህን ቋንቋ ንገረኝና በሱ ላስረዳህ ከዚህ በኋላ ለኔ ተወው የትም እንዳትንቀሳቀስ እዚሁ ቁጭ ብለህ እየጠጣህ ጠብቀኝ !"
ብሎኝ ሰውየውን ተከትሎ ወደ ሽንት ቤት ሄደ።
ብዙም ሳይቆይ ተመልሶ መጣና ምንም ሳይለኝ መጠጣት ጀመረ
ወደሽንት ቤት የሄደውን ሰውዬ ካሁን ካሁን ይመለሳል ብዬ ብጠብቅም አልተመለሰም ጨነቀኝ እንዴ ምን አርጎት መጣ? ግራ ገባኝ
ምን አልከው ሰውየው እኮ ብር ያጠገበው ባለጌ ነው ምን አለህ? ስለው•••
መልስ ሳይሰጠኝ እሄን ውስኪ እንደውሃ እየጠጣ •••
"ጠጣ ጠጣ ያቺን አየሀት ዝም ብላ እያየችህ ነው አብረካት መደነስ ትፈልጋለህ ልጥራት እንዴ?"
አለኝ ጥግ ኮርነር ላይ ካሉት ሴቶች መሀል ወደኛ እያየች ወደምትናጠው ሴት እያመለከተኝ
ወይ መደነስ እኔ ሰውየው እምጥ ይግባ ስምጥ ሄዶ ካናገረው በኋላ ከሽንት ቤት ባለመመለሱ ምን አርጎት ነው የመጣው እያልኩ ግራ ተጋብቻለሁ ጭራሽ ደንስ ይለኛል ምን አይነት ባህሪ ያለው ሰው ነው እሄ ደግሞ ቢያንስ እንኳን የኔ ጭንቀት ለምን አይገባውም እንዴ በራሴ ጉዳይ ዝም በል ጠጣ ደንስ ስላለኝ ዝም የምል ይመስለዋል?!
ወደ ሽንት ቤት ሌላ ሰው በሄደ እና በወጣ ቁጥር እያየሁ በጭንቀት ከመፈንዳቴ በፊት እራሴ ሄጄ ለማረጋገጥ ስለፈለኩ•••
••• እሺ መጣሁ አንዴ ስመለስ አብሪያት እደንሳለሁ አልኩትና ሄድኩ መጀመሪያ ወደነመሲ ገልመጥ ሳደርግ ሁለቱ ብቻ ናቸው እነሱም እንደኔ ሰውየው የት ሄደ ብለው ግራ ተጋብተዋል መሰለኝ ግራና ቀኝ ይገላመጣሉ ።
ወደ ወንዶች ሽንት ቤት በፍጥነት ሄድኩና ከአምስቱ ሽንት ቤቶች መሀከል ክፍት የሆኑትን ሁለቱን አየት አድርጌ በማለፍ ሶስተኛውን ስበረግደው•••

ይቀጥላል.....
Share
@yefikrclinic
@yefikrclinic
@yefikrclinic