Get Mystery Box with random crypto!

ልጩህበት ክፍል~~~~አምስት(5) አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ የ ቴሌግራም ቻናል . . . | ❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

ልጩህበት

ክፍል~~~~አምስት(5)

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ የ ቴሌግራም ቻናል
.
.
.
ደስ ባይለኝም ያቀደችልኝን ቀድሜ መረዳት አልችልም ነበርና ቃል ገባሁ።

ፈተናው ሊያልቅ አንድ ቀን ሲቀረው ጨነቀኝ
ዛሬ ጥዋት ስድስት ሰአት አከባቢ እነሱ ፈተናው በማለቁ ደስ ሲላቸው እኔን ግን ፍርሀት ፍርሀት አለኝ •••

ወደ ዶርም ገባሁ። በፈተናው ምክንያት የተጠራቀመ እንቅልፍ አለብኝ።ጋደም አልኩ ። ይዞኝ ሄደ።
አንድ ሳአት ያክል እንኳን ሳልተኛ የሆነ ከሩቅ የመጣ የመሰለኝ ጫጫታ ቀሰቀሰኝ።

ብርግግ ብዬ እዛው በጀርባዬ በተኛሁበት አይኔን ገለጥ ሳደርግ ሶስቱም አልጋዬ ጠርዝ ላይ ተደርድረው ቁልቁል እያዩኝ ይንጫጫሉ።

"ኧረ መተኛት እስቲ በዛሬ ቀን ይተኛል!"

"እኛኮ ገና ከፈተና ያልወጣሽ መሰለን?"

"ዛሬ ወሳኝ ቀጠሮ ከኛ ጋር መያዝሽን ረስተሽው ባልሆነ በይ ተነሽ አሁን!

" ውሃ አምጪና ድፉባት በናትሽ!"
ህልም ላይ ነበርኩ አቋረጣችሁኝ አልኳቸው ቀና እያልኩ።

ከሁለቱ ጓደኛቼ አንደኛዋ ትግስት(ቲጂ) ስትባል ሌላኛዋ ደግሞ ረድኤት(ረዱ) ትባላለች
የሶስተኛ አመት ተማሪዋ ስንተዋወቅ መሲ እንዳለችኝ ትዝ ይለኛል ግን በሌላ ስም ሲጠሯት ሰምቻለሁ።

"ምን አንቺ ህልም ብታይ ካባትሽ አታልፊ አሁን ብናቋርጥሽም ነገ ወይ ከነገ ወድያ ማየትሽ ስለማይቀር ትቀጥይዋለሽ ግን አብዝተሽ ስለሳቸው ስለምትጨነቂ እኮ ነው አደል ኤዱ ? አለችኝ ቲጂ
ንግግሯ ስላልጣመኝ መልስ ሳልሰጣት ፊቴን ልታጠብ ወጣሁ።
ስወጣ ግን •መሲ ተብዬዋ•••

" አባቷ ምን ሆነዋል ?ለምንድን ነው ስላባቷ የምትጨነቀው? ብላ ስትጠይቃቸው ሰምቻታለሁ።
ታጥቤ ስመለስ ስላባቴ ስትጠይቅ የነበረችው ያቺው መሳይ•••

"አንቺ እኮ በዚህ ውበትሽ እሄ ድርቅናሽን ትተሽ ፈጠን ያልሽ ልጅ ብትሆኚ እንኳን አባትሽ ጋር ደርሶ ለመመለስ መሳፈሪያ ሊቸግርሽ ለሌላም በተረፍሽ ለማንኛውም የሆነ ብር ከገባልኝ እኔ እራሴ እሰጥሻለሁ እሺ ኤዱዬ ሄደሽ ታያቸዋለሽ!"
አለችኝ ።

አባቴ በጣም ስለናፈቀኝ መጨረሻ ላይ የተናገረቻት ነገር የልብ ትርታዬን ጨምራው ሰፍ እንድል ብታደርገኝም በመጀመሪያው ንግግሯ ላይ ጥያቄ ነበረኝ•••
ድርቅናሽን ትተሽ ፈጠን ያልሽ ልጅ ብትሆኚ ስትይ ምን ለማለት ፈልገሽ ነው? አልኳት
ቀበጣጠረች•••

"ማለቴ ጭምት ነሽ ፣ሰው አትቀርቢም
ከሰው ጋር መቀራረብ መተዋወቁ ጥሩ ነው: ብቸኝነት አታብዢ ለማለት ፈልጌ ነው
"ለሰው መድሀኒቱ ሰው ነው"ሲባል አልሰማሽም?"

አባባሉ እውነት ነው ግን የዚህ አባባል ተቃራኒውም እውነት እንደሆነ አትርሺ! ስላት

" ማለት?" አለችኝ

የሰው ትልቁ ጠላቱም ሰው መሆኑን ነዋ ።

ለማንኛውም ቃልሽን እምታከብሪ ሰው ከሆንሽ ብትመጪ ደስ ይለኛል ብላ እየተመናቀረች ወጥታ ሄደች።

ሁለቱ ጓደኜቼ ስላናደድኳት ሲከፋቸው አየሁ። ከዛ ቡሀላ ዝም አልኩ።

ፀጉር ቤት እንሂድ ሲሉ ሄድኩ።
ልብስ ከገዟቸው አዳዲሶቹ ልብሶች መሀል በነሱ ምርጫ ልበሽ ሲሉኝ ለበስኩ ።

አስር ሰአት አከባቢ ከግቢ እንውጣ ሲሉኝወጣሁ ።
ትንሽ እንደሄድን ግን ወዴት እየሄድን እንደሆነ ጠየኩ••

"መሲ ቤት ትንሽ እናመሽና ከዛ እንወጣለን"
አሉ። መሲ የግቢ ተማሪ ሆና የምን ቤት?

"እንዴ እሷኮ ካፌም አትጠቀምም ግቢም አትኖርም ውጪ ተከራይታ ነው እምትኖረው " አሉኝ እየተጋገዙ ።

ከግቢ በር እስከ ሰይዶ ሄድንና ከሰይዶ እስከ አሸዋ የሚሄድ ሌላ ፎርስ ይዘን ከዚራ ጋ እንደደረስን ወራጅ ወራጅ አሉ ተራ በተራ።
አንድ ሰርቢስ ያለው ድሮ እንደተሰራ አሰራሩ የሚመሰክር ትልቅ ግቢ ውስጥ ገባን።

መሲ ከሰርቢሶቹ አንዷን ይዛለች።
ከዛ ቡሀላማ ጦጣ ታውቃለህ ጦጣ ሆንኩልህ በቃ ምን አለፋህ
የመሲ ቤት ውስጡ በጭራሽ የተማሪ ቤት አይመስልም የተሟላ ነው በዛ ላይ እስከ ማታ ድረስ ከጫት ጀምሮ እስከ ሺሻ ታዛቢ ልትሆኚ ነው እንዴ የመጣሽው እንቺ ሞክሪ እያሉ እርስ በርስ እየተቀባበሉ ሲፈጩና ሲምጉት ዋሉ እሷን አላውቃትም በትንሹም ቢሆን የማውቃቸው ጋደኛቼ ግን እንዲህ ለመለወጥ የፈጀባቸው ግዜ ምን ያህል አጭር እንደሆነ ሳስበው ምን እንዳስነካቻቸው ግራ ገባኝ ።

ወሬያቸው ሁሉ እንቆቅልሽ ሆነብኝ።
በኔ በግዜ እንውጣ ውትወታ ከምሽቱ ሶስት ሰአት ላይ አንተ ያገኘከኝ ቦታ ላይ ወዳለው ሆቴል ነበር የገባነው።

ጓደኛቼ ሁኔታቸው ምንም አልጥምሽ አለኝ በኮድ ይነጋገራሉ ፣ በዛ ላይ ሰላም የማይሉት የማይጠመጠሙበት የለም ደሞ በየደቂቃው ልዩነት ስልክ ይደወልላቸዋል የሚያናግሩት ካጠገቤ ዘወር እያሉ ነው ። ጨነቀኝ ።

ላለመጨቃጨቅ ስል አንድ ቢራ ያዝኩ።
ትንሽ እንደቆየን በቃ ቤት እንቀይር ሲሉ ቆሌዬ ተገፈፈ ገና ከዚህ ቡሀላ ሌላ ቤት ካጠገባቸው እሩጭ እሩጭ አለኝ።

ሌላ ጭፈራ ቤት ሄደን ብዙም ሳንቆይ ረዱ ቅድም የነበርንበት ሆቴል ስልኬን ጥየው መጣሁ ብላ ጮኸች ።

ከቲጂ ጋር ተያይዘው ሮጡ ። እኔ ከሷ ጋር እንደተፋጠጥኩ እነሱ በሄዱ በሰከንዶች ውስጥ አንድ ሰውዬ ካያት ረጅም ግዜ የሆነው ይመስል መሲ ላይ እየጬኸ ተጠመጠመባት።

ሰላም ብሏት የሚሄድ መስሎኝ ነበር። ግን እዛው እኛው ጋር ቁጭ ብሎ ውስኪ በማለት መጠጥ አዘዘ።

ፈራሁ ። ሽንቴ መጣ። ሸንቼ እንደተመለስኩ።
"ተጫወቺ እንጂ አንቺ ቆንጆ ምንድን ነው ዝምታ አበዛሽኮ? አለኝ ሰውየው።
ቀጠል አርጋ•••

"ተዋወቂው አሌክስ ይባላል " አለችኝ

ፈጠን ብሎ "አሌክስ" አለና እጁን ዘረጋ

ኤደን አልኩና እጄን ሰጠሁት ። ጨበጠኝ ። ትንሽ አቆይቶ ሲለቀኝ አሁንም ሽንቴ መጣ ።
ተነስቼ ወደ ሽንት ቤት ሄድኩ።
ከጀርባዬ የሆነ ሰው በፍጥነት ሲከተለኝ ይታወቀኛል።

ልጅ የክፍላችን ተማሪ ነው። ግን አንግባባም ሰላምም አንባባልም። ባጋጣሚ እዛ እየተዝናና ነበረ ለካ።
ድንገት ሳላየው እሱ አይቶኝ ነው መሰለኝ ተከተለኝና ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ቀጥታ •••

"እቺ አስተኳሽ አንቺንም አገኘችሽ!" አለኝ ።

አልገባኝም ማነች እሷ? አልኩት
"ብዙ ግዜ እምናያት ከሁለቱ ጓደኛሽ ጋር ነበር እነሱን አስበልታ ከስንቱ ተቀባብላለች አሁን ደሞ አንቺን ልታስበላሽ ነው?"

በፈጠረህ ምን እያልክ እንደሆነ በሚገባኝ አማርኛ ንገረኝ አልኩት።
ይበልጥ ወደኔ ጠጋ አለና •••

"እሄውልሽ እኔም አንቺም ወደዚህ ግቢ እኩል ነው የመጣነው ስለሷ የነገረኝ ድሮ ከታላቅ ወንድሜጋ ጋደኛ የነበረ እዚሁ ግቢ የሚማር የሶስተኛ አመት ተማሪነው።

አብራሽ ያለችው ልጅ የግቢ ተማሪዎችን በተለይ ፍሬሾቹን ለዚህ ሀገር ወንዶች በማቀባበል ቢዝነስ የምትሰራ አደገኛ ሴት ነች።
በርግጠኝነት አንቺንም ልታቀባብልሽ ነው ያጠመደችሽ ሞባይሏን ብትቀበያት እና ብታይው ለገበያ ልታቀርብሽ አንቺ ሳታያት ያነሳችሽ ብዙ ፎቶ አለ
ያንን ፎቶሽን ያየ ሰው እቺን ልጅ ካስበላሽኝ እሄን ያክል እሰጥሻለሁ ይላታል አለቀ ተሟሙታ ታጠምድሻለች !

አንዴ ከግቢ በሆነ መንገድ አብረሻት ወጥተሽ እምትፈልገው ቦታ ከደረሽላት ቡሀላ አለቀ ከተስማማሽ በፀባይ ካልተስማማሽ ደሞ በግድም ቢሆን ለእርድ ታቀርብሻለች !
ቢዝነሱ ስለጣማት ሆን ብላ ሶስተኛ አመት ላይ አንዳንድ ኮርስ እያፈላች እዚሁ ግቢ ውስጥ አምስት አመት ሆናታል !

ከየክፍለ ሀገሩ እዚህ ደርሷቸው የሚመጡ ስንት አበባዎችን እንዳስቀጠፈች ብትሰሚ እንኳን እንደዚህ አጠገባ ልትቀመጪ ከሩቁ ስታያት ትሸሻት ነበር!

  ይ ላ ሉን

@yefikrclinic

  ይ ላ ሉን
@yefikrclinic
@yefikrclinic