Get Mystery Box with random crypto!

የተውጋ ልብ #ክፍል 2 'እህቴ መጨረሻው እኮ ነው ውረጂ እንጂ' አለኝ …ሽምጥ ጋልቦ ይዞ | 👑የፍቅር_ደብዳቤዎች 💏

የተውጋ ልብ


#ክፍል 2

"እህቴ መጨረሻው እኮ ነው ውረጂ እንጂ" አለኝ …ሽምጥ
ጋልቦ ይዞኝ ከሄደው ኃሳብ ደንብሬ ባነንኩ… ዞር ብል ሚኪ
አጠገቤ የለም።መኪናውን ባማትር ብቻዬን ቀርቻለሁ።
እየተርበተበትኩ ወረድኩና ረዳቱን

"ይቅርታ አጠገቤ የነበረው
ልጅስ?" አልኩት። ስትፈዢበት ጊዜ ምን ያድርግ? አይን አይንሽን
አይቶ ወረደ… ድንዝዝ!! ብሎኝ ተፈተለከ።

መሃል አራት ኪሎ ላይ የጨው አምድ ሆኜ ቀረሁ። ከሰው ሁሉ
ወንዱን ከወንድ ሁሉ ሚኪን ፈለኩት። ግን ላገኛሁ አልቻልኩም፤
አጣሁት። ድንገት ድንጋጤዬ ሲበርድልኝ ወደ አራት ኪሎ ዩኒቨርስቲ
ከነፍኩ።እዛም ፈለግኩት …ጊቢው ውስጥ ለመግባትም ተከልክዬ
ከጥበቃዎቹ ጋር እሰጣገባ ገጠምኩ። ቢቸግረኝ ከግቢው
የሚወጡትና የሚገቡትን በሙሉ ሚኪን ያውቁት እንደሆነ መጠየቅ
ጀመርኩ።ማንም አውቀዋለሁ ያለኝ ግን አልነበረም።
*@**
ምናው አምላኬ አሳይተከኝ ነሳኸኝ እያልኩ ማጉረምረም ቀኑን ውዬ አመሻሽ ላይ ወደ ቀዘቀዘው ቤቴ ስመለስ ሰፈሬ ደምቃለች በርግጥ ሁሌም ውደማታ ላይ ውጣቱ ጥንድ ጥንድ ሆነው ውክ የልጆች ጩህት ሳቅ ስፈራችን ባንድ እግሮ ነው የምትቆመው።

ጋሽ አንዳርጌ ያቺን የምትሞቀውን ጋቢያቸውን ተከናንበው
"የልጆቹን ሳቅ ጭቅጭቅ ይመለከታሉ....ቢያረጁም አራዳ ናቸው... ሙድ የገባቸው ...

" እንደምን ዋሉ ማለቴ እንደምን አመሹ...
"ወይ አንቺ መች ይሆን ሁለት ሆነሽ የምትገቢው .....
"አይ ፋዙካ ከላይ ነው....ትዛዙ ግን አይቀርም በቅርቡ
"አይ አንቺስ ቆመሽ እንዳቀሪ እኛም ድግስ ለመብላት ወልደሽ እንደነዚ ስጮህ ማየቱ አይከፋም"
"አረ አሁንማ አይቀርም ምን ይታውቃል ነገ ሁለት ሆኔ እመጣለው"
"ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ አሉ
እውነት ነው ምንም ሳናውራ ስለፍቅር በተስፋ ያውም ነገ በለው መቀደድ

እያልኩ ውደ ቤቴ ዘው ....ያረኩትን ጫማ በብረሀን ፍጥነት ጥዬ ውደ አልጋዬ በጀርባዬ ተዘርዬ የቀኑን አስብ ጀመር።... ወይኔ ደና እጄ የገባውን በራሴ ድክመት አጣሁት እያልኩ ከራሴ ጋር መሞገት ...
"ድንገት ግንባሬን እየሳመ ፀጉሮቼን እንደማሻሸት. ሀዊዬ የዛሬዋ ቀን በጣም ደስ የምትል ናት አንቺን ያገኛሁበት ደስ የሚል ጊዜ እያሳለፍን ያለንባት ....ብሎ ከናፍሮቹን ልስም ስጠጋ .........

"አይኖቼን ገለጥ እንደማደርግ ስል ያቀፍኩት ትራስ ሆኖ ቁጭ ....ወይኔ ልጅት እንዲ ሆኜ ልቅር ልቤ በሚኪ ተውግቶ ..... አሁን ምን የሚሉት መቃዠት ነው። ምን አለ አሁን ያየሁት እውን ቢሆን እረ አምላኬ ተለመነኝ ባልጠፋ ለኔ የአጥንቴን ፍላጭ አጣሁ።
ወይ የባህር ዳር ሸበላ ልቤን በፍቅር ውግቶት ቁጭ ufffff

መንጋት አይቀር ነጋ የተዋት ፀሎቴ ከሌሎች ቀን የተለየች ነው እጆቼን ወደ አምላኬ ዘርጋሁና ሚኪዬን የኔ አድርግልኝ ማታ የቃዠሁትን ዛሬ ላይ እውን አድርግልኝ አሜን ።....
"እረ ተመልከተኝ .ከቤቴ ውጥቼ ውደ አራት ኪሎ ጊቢ የሚውስድ ታክሲ ግብት እዛ ሚኪዬን ያገነኛኝ ቦታ ተቀምጬ ማሰብ ጀመርኩ
"ከታክሲው ወርጄ አራት ኪሎ ጊቢው ጋር ፊቴን ቀና ሳደርግ......

ይቀጥላል...