Get Mystery Box with random crypto!

••● #ልቤ_ይጠብቅሻል ●••                  ,,,,,,,,,,,    ,,,,,, | የፍቅር ጎጆ

••● #ልቤ_ይጠብቅሻል ●••
                 ,,,,,,,,,,,    ,,,,,,,,,,,


እኔ አንቺን ስጠበቅ የሆንኩትን ስሚ፤
ፍቅርሽ እየጎዳኝ አጣው አስታማሚ፤
እኔ አንቺን ስጠበቅ
ዘመን ተገልብጦ በዘመን ሲታደስ፤
ዛሬም አላቆምኩም በጥበቃ ማልቀስ፤
እኔ አንቺን ስጠበቅ
ደሞ ካጋጠመሽ ምርጥ ወሬ ነጋሪ፤
ቀብሬንም ይንገርሽ አደራ እንዳትቀሪ፤
መኖር ምን ዋጋ አለው፤
ለነገሩ ተይው ለይምሰል
የቆመ ሀውልት መስያለው ፤
አንቺን ካጣው ወዲያ
ደከመ እንጂ እደሩ እኔኮ ሞቻለው፤
ይሄን ስልሽ ደግሞ አቤት
ዘመዶችህ ለዚ እንኳን አይበቁም፤
ብለሽ ከጠየቅሽኝ ቆሜ ባዩኝ ጊዜ
መኖሬን ነው እንጂ መሞቴን አያቁም፤
በያውቁማ መሞቴን ነበሩ ደመላሽ፤
እኔም ፈርቼ ነው አንቺን እንዳላጣሽ፤
ጥያቄሽ ከሆነ
ካጣሀኝ ቆይቷል ደሞ የምን ማጣት፤
እኔም እልሻለው
በምን አንድ ይሆናል መራቅና መምጣት፤
መምጣት ስልሽ ደሞ
ለየብቻ አይደለን ትዪኮ ይሆናል፤
መጣሽም ቀረሽም እኔ ስጠብቅሽ
ህልሜ አቆራኝቶን አብረን እኮ አድረናል፤
በናፍቆትሽ እባ አይኔ ተከርችሞ፤
ልቤ ይጠብቅሻል በትዝታ ቆሞ፤
             


     ,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,
         •═••• •••═•
  
    
    @Yefiker_Gojo    ,, @AbenaG
  ━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━