Get Mystery Box with random crypto!

እስቲ ለእኔ ለእህታችሁ ምክራችሁን ለግሱኝ _______ ከአገባሁ 3 አመት ሊሞላኝ ነዉ :: ከሟ | የፍቅር ጎጆ

እስቲ ለእኔ ለእህታችሁ ምክራችሁን ለግሱኝ
_______
ከአገባሁ 3 አመት ሊሞላኝ ነዉ :: ከሟግባቴ በፌት ምንም ከወንድ ጋር የፍቅር ግንኙነት ያልነበረኝ የቤት ልጅ ሆኜ ያደኩ ለቤተሰቦቼ ብቸኛ ልጅ ነኝ :: ዪኒቨርስቲም ገብቼ ቤተሰቦቼን ለለማሳፈር ስል አንገቴን ሰብሬ ተምሬ በArchitecture ተመርቄ ጥሩ ስራ እንደጀመርኩ በቤተሰብ በኩል የመጣልኝ ከኔ በእድሜ 4 አመት የሚበልጠኝን ሰዉ አገባሁ :: ባለቤቴ በጣም መልካም ሰዉ ነዉ አስመቺና ላኪ ስለሆነ ለቤተሰቦቼ የማያደርግላቸዉ ነገር የለም እና በትዳሬ ላይ ያለብኝን ችግር እንካን ለመንገር ለእናቴ ዳር ዳር ስል እንደሱ ያለ ባል የትም እደማላገኝ ነግራኝ አፌን ታዘጋኛለች :: ጉዳዩ ምን መሰላችሁ እህቶቼ ባለቤቴ ከፍተኛ የሆነ የወሲብ ፍላጎት አለው :: የወር አበባ እራሱ ላይ ሆኜ ለምኘዉ በስንት መከራ ነዉ አርፎ የሚተኛዉ , በቃ ምርር ብሎኛል :: ስራ ደክሞኝ ውዬ መትቼ ደክሞኛል ስለው በግድ ይገናኘኛል እኔም ተስፋ ስቆርጥ ስሜቱን ይጨርስ ብዪ ትግሌን አቆማለው :: በቀን ጠዋት እና ማታ ሁሌ የማይቀርልኝ ጉዳይ ነው :: አሁንስ ራሱን የቻለ የቤት ስራ ነው የሆነብኝ በዚ ጉዳይ በጣም ብዙ ግዜ አናግሬዋለዉ ግን ለዉጥ የለም ተመልሶ አዛዉ ነዉ :: ቢቸግረኝ መዘነጥ ሁላ ትቻለሁ እንደነገሩ ነዉ የምለብሰዉ ግን እደዛም ሆኜ ፋታ ሊሰጠኝ አልቻለም :: በዛ ላይ ይቀናል መኪና መንዳት እየቻልኩ እንካን የትም ቦታ በሹፊር እድሄድ ነዉ የሚፈልገዉ :: ብቻ ምን አለፈችሁ የቁም እስረኛ ሆኛለሁ :: አሁን ደግሞ የአምስት ወር እርጉዝ ነኝ የእናትነት ወጉን በማየቴ ደስ ብሎኛል ግን በዚህ አይነት ትዳር እስከመቼ እንደምዛለቅ አላውቅም :: አንዳንዴ ዉጪ ሀገር ሰበብ ፈጥሬ ሄጄ ለመጥፋት ሁላ አስባለሁ ግን ደግሞ ልጄን ያለ አባት ማሰቀረት ከበደኝ :: ችዬ እጻልኖር ጸግሞ እንደ ቆዳ በነጋ በጠባ ቁጥር መታሸት ሰለቸኝ :: ምሳ ሰዓት እንካን ከመጣ ቤት ካላደረግን ብሎ ግብግብ ይፈጥራል :: በዚህ ምክንያት ስራ ቦታ ከጋደኞቼ ጋር ነው የምበላው በፍፁም ምሳ ብዬ ወደ ቤቴ ድርሽ ብዬ አላውቅም :: ብቻ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ጨንቆኛል እና የእህትነት ምክራችሁን እሻለሁ እንደዉ ምን አባቴ ባረግ ይሻለኝ ይሆን ???