Get Mystery Box with random crypto!

#አለሁ.. መንገድ ዳር ቁጭ ብየ አግዳሚ እያየሁ የሚያስጠብቀኝን ይኸው 'ጠብቃለሁ አልፎ ሂያጅ | የፍቅር ጎጆ



#አለሁ..

መንገድ ዳር ቁጭ ብየ አግዳሚ እያየሁ
የሚያስጠብቀኝን ይኸው 'ጠብቃለሁ
አልፎ ሂያጅ መኪና መንገደኛ ጥንዶች
ብርድ ያዘለ ንፋስ ሚጓረሱ ወፎች
ጠቁሮ የተቆለለ አልቃሻ ደመና
ፀሐዩዎን ለመከለል እድሜው የማይፀና
መንገደኛ ዝናብ ምሽቱን አስታኮ
ጨረቃን እንዳላይ በሰይጣን ተልኮ
ሌተ ቀን መንገድ ዳር እንዲያም ሲል ከቤቴ
ተጎሳቁየ አለሁ ለዛች ልጅ ናፍቆቴ..



Daniel Mak


,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,
        •═••• •••═•
  
    
@Yefiker_Gojo    ,, @AbenaG
━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━