Get Mystery Box with random crypto!

#ለፍቅሬ.............. ምናልባት በዚህ ትልቅ አለም ውስጥ ትንሽ ነገር ልትሆኚ ትችያለሽ | የፍቅር ጎጆ

#ለፍቅሬ..............

ምናልባት በዚህ ትልቅ አለም ውስጥ ትንሽ ነገር ልትሆኚ ትችያለሽ በኔ ትንሽ አለም ውስጥ ግን ትልቅ ነገር ነሽ የኔ ፍቅር በአካል ብንራራቅም ዛሬም እውድሻለው ያላንቺ የማሳልፋት ሰከንድ የአመታትን ያክል ትረዝምብኛለች ቢሆንም ግን አይከፋኝም ምክንያቱም እልፍ አእላፍ አመታትን ላፈቅርሽ ስለምፈልግ ፍቅሬ ደስታ ልክ እንደ ቢራቢሮ ናት ካሯሯጥሻት ታመልጥሻለች
በእርጋታ ከተቀመጥሽ ደግሞ ምናልባትም እጆችሽ ላይ ልታርፍ ትችላለች። ለዚህም ነው በእርጋታ የምንገናኝበትን ቀን እየናፈኩ የምጠብቀው።

ውዴ ስላንቺ ሳስብ የተቃጠለ ልቤ ላይ ቀዝቃዛ ፍሳሽ የሚወርድ ያህል ያረካኛል እንደምወድሽ ስነግርሽ ልቤ ቦታውን የሚለቅ ያህል እስኪሰማኝ ይመታል ትንፋሼ ይቆራረጣል ባፍቃሪዎች ግጥም ላወድስሽ በፈላስፎች አባባል ላሞግስሽ አልቻልኩም ስላንቺ የሚል ድምፅ ሊያሰፍር ልቤ ቋምጠ አንቺን የሚግልፅ የልብ ምቴ እና የትንፋሼ መቆራረጥ እንጂ ቃላቶች አልሰበሰብ አሉኝ ቢሆንም ግን ፍቅሬን ከመግለፅ አያግዱኝም ዛሬን ብቻ ሳይሆን አመታትን አፈቅርሻለው።



    
,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,
        •═••• •••═•
  
    
@Yefiker_Gojo    ,, @AbenaG
━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━