Get Mystery Box with random crypto!

ሲወደኝ ስኮራ፤ ሲቀርበኝ ስርቀው ክብር እየሰጠኝ፤ ደርሼ ስንቀው ሳጠፋ ታግሶ፤ ሳኮርፍም አባብሎ | የፍቅር ጎጆ


ሲወደኝ ስኮራ፤ ሲቀርበኝ ስርቀው
ክብር እየሰጠኝ፤ ደርሼ ስንቀው
ሳጠፋ ታግሶ፤ ሳኮርፍም አባብሎ
እኔን አስቀድሞ፤ እንዳልሽ ይሁን ብሎ

ሁኖልኝ ሳለ አልጋ
ስሆንበት ቀጋ
ደከመው መሰለኝ ብዙ መታገሱ
ታከተው መሰለኝ ጥፍቴን ማበሱ
የለም ጠፍቶብኛል ካየሁት ሰንብቷል
ስልኩንም ሞከርኩኝ፤አይሰራም ተዘግቷል
እንጃ ውስጤ ሰግቷል
ምናልባት እናንተ ድንገት ካያቹህት
አደራ አደራ ይህንን ንገሩት

"እያለህ ያልታያት የሰጠሀት መውደድ
ስትሄድ ገብቶታል ስትጀምር መንገድ!
አራቅ'ክ እንደሆነ ልብህ አልቆረጠህ
ተመለስ ልካስህ_ካንተ በበለጠ
ብላለች በሉልኝ ካያቹህት ድንገት
አደራ ንገሩት ካሁኑ አቅቶኛል
ያለሱ መኖሩ ዳገት ሆኖብኛል!
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
@yefiker_gojo @abelo_neww