Get Mystery Box with random crypto!

​​. ​           ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉      ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ | የፍቅር ጎጆ

​​. ​           ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉

     ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ

#ክፍል_55


ደራሲ:-ቤዛዊት ፋንታዬ (የሽዋ ልጅ)



... ከሄዋን ክፍል ውስጥ የመስታወት ስብርባሪ ድምፅ ተሰማ....ሁሉም በድንጋጤ እየተርበደበዱ ድምፁ ወደተሰማበት እየከነፉ በረሩ...አዳም የሚያየውን ማመን አቃተው የልብ ትርታው ለተወሰኑ ሰከንዶች መምታቷን አቆመች አለሙ በደም ተጨማልቃ ከመስኮቱ በተቃራና ተዘርራለች...ከሰውነቷ የሚፈሰው ትኩስ ደም ወለሉ ላይ ተዝረክርኳል....አዳም ከድንዛዜው እንደምንም ለመላቀቅ እየሞከረ ሄዋን ብሎ ጮኽ....ዲናም የምታየውን ማመን አልቻለችም መሬት ላይ ተዘርራ የምታያት ከደቂቃዎች በፊት ተነጋግረው የነበረችው ፍልቅልቋ ድምጿ ከጣራ በላይ የሚሰማው ደመ ግቡዋ ሄዋን አልመስልሽ አለቻት ገረጣችባት...ቦስም ቢሆን በድንጋጤ ክው ቢልም እንደዲናና አዳም ደርቆ አልቀረም ሄዋንን አፋፍሶ ወደ ሆስፒታል ይዟት ነጎደ...... "ነርስ ከዚህ በሁዋላ  የሄዋን በህይወት የመኖር እድሏ በከፍተኛ ደረጃ የተመናመነ ነው...ህመሙን ማሸነፍ አልቻለችም ይባስ ብሎ ይሄም ተጨመረባት....ሄዋን ከዚህ በሁዋላ በሂወት የምትቆየው ለጥቂት ጊዚያት ነው ግፉ ቢል የአንድ ሳምንት ጊዜ ነው" አሉ ዶክተሩ ፊታቸው ላይ የሚነበበውን የሀዘን ስሜት መደበቅ አቅቷቸው....."ዶክተር ይሄን ኬዝ ልክ እንደቅርብ ሰዎ ይዘው ልዩ ክትትል ሲያደርጉላት እንደነበረ አውቃለሁ መቼም ለዶክተር ታካሚው ሳይሽር ስቀር የሚፈጥረውን ስሜት አይደለም በሞያው ላይ ያለውት እኔ ቀርቶ ስለሞያው ምንም የማያውቀውም ሰው የሚረዳው ነው...ለማንኛውም ፈጣሪ ጥንካሬው ያችሮት"አለች ነርሷ ከዶክተሩ የህክምናውን ፋይል ተቀብላ መድሀኒቶችንንና የህክምና ፋይል የምታስቀምጥበት የምትገፋው ጋሪ  ላይ እየመለሰች...."አሜን ነርስ"ብለው ሲጠራ የነበረውን ስልካቸውን አንስተው ወደ አንዱ ጥግ ሄዱ...
ወደ ዶክተሩ ሲሄድ  የነበረው አዳም ንግግራቸው ጆሮው ላይ ተንቆረቆረ... የሚሰማውን ማመን አልቻለም ነገረ አለሙ ጨለመበት ደጋግሞ የአለሙ መሞትን በአይነ ህሊናው ሳለው መንታ መንታ ሆነው ከአይኑ ሲፈሱ የነበሩት እንቧዎቹን ለመጠራረግ ፉታ ሳያገኝ ነገረ እይታው በጭለማ ተቀየረ ወድያዋ ወደ መሬት ተዘረረ...
፨አዳም ሲወድቅ የሰሙት ዶክተር ስልካቸውን ጥለው ፈጥነው
ወደ በሩ ሄዱ። አዳም ወድቆል ሮጥ ብለው ከክፈላቸው ውሀ
አምጥተው ፊቱን እረጩት። ከዛ ፊቱን መታ መታ ሲያረጉት
ደቂቃዎች ተቆጥረው ነቃ ። ፍዝዝዝ እንዳለ በጭልምልም
አስተያየት ዶክተርን እያያቸው። "ዶክተር ምንድነው ያሉት ? ሄዋኔ
ልትሞትብኝ ነው? አለ። ዶክተር ወዲያው አዳም በስልክ ያወሩትን
ነገር በመስማቱ እንዲህ እንደሆነ አወቁ። "አይ አይ የተሳሳተ
መረጃ ነው የሰማከው አዳም እባክህ ተረጋጋ" አሉት።
፨ አዳም እንባውን እያጎረፈ "ተዉ ተዉ ዶክተር እባካቹ
አታፅናኑኝ፤ ልዘንና ልበድበት፤ አብጄ ምንም አላስታውስ አለና
ጮከ። ዶክተር "እውነት ነው የነገርኩክ አዳም እኔ በጭራሽ
አልዋሸውክም እንደዚህ አትሁን እያወራው የነበረው ስለ ሊላኛዋ
ታካሚ ነው። ሄዋን የምትባል ሊላ ታካሚ አለች። ከፈለክ ላሳይክ
እችላለው" አሉት። አዳም እያለቀስ "አትዋሹኝ እባኮት"
አለ።ዶክተር "እውነት አልኩክ እኮ ና ላሳይክ ከፈለክ" አሉት።
፨አዳም የዶክተርን ክንድ አጥብቆ ይዞ "እና ለምንድን ነው ታዲያ
የጠሩኝ?" አላቸው። ዶክተር ፈገግ ብለው "እንኳን ደስ አለክ
ለማለት እና ሄዋን ስትወድቅ እጆን የመስታወቱ ስንጣቄው
ስለቆረጣት ቁስሏ ኢንፌክሽን እንዳይፈጥር መዳኒት ገዝቼልላታው
፤እንዳባትክ እየኝ አዳም የተቻለኝን ሁሉ አረግላችዋለው" አሉት።
አዳም አሁን ደህና ሆነ ከዛም እራሱን ታዘበ "የሰው ነገር ግን
ሲገርም በዙሪያችን ያሉትን ስዎች ከሁሉም አስበልጠን ማየታችን"
አለ።በውስጡ ከዛ "እሺ አሳዩኝ" አላቻው።
፨ ዶክተር የቢሮ መቀመጫ ወንበራቸው ላይ ተቀመጡና አዳም
የእንግዳ( የታካሚ) ወንበር መቀመጫ ጋር እንዲቀመጥ
በእጃቸው ጠቆሙት።አዳም በአይኑ እሺታውን ገልፆላቸው
ተቀመጠ። ዶክተርም ሁለት ፈሳሽ የሽሮፕ ይዘት ያላቸው መዳኒቶች
ከመሳቢያው አውጥቶ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጡ። ተለቅ ያለውን
ወደ እሱ በአውራ ጣታቸው ገፋ እያረጉ "ይሄ የቁስሉ ማጠቢያ
ነው፤በቀስታ በጥጥ ታፀዳዋለክ አሉት።በመቀጠል ሁለተኛውን እና
በጣም ትንሽ ይዘት ያለውን ብልቃጥ በተመሳሳይ መንገድ
በአውራ ጣታቸው ገፋ አርገው "ይህንን ደሞ
ትቀባላታለክ።በጥንቃቄ በእየ 6 ሰአቱ" አሉት። "እሺ ጥሩ በጣም
አመሰግናለው" አላቸው። "እሺ አዳም በል ብዙ ያዝኩክ አደል
መሄድ ትችላለክ" አሉት። አዳም "እሺ ዶክተር አመሰግናለው"።
አለ ዶክተር የአዳምን እጅ ለመጨበጥ እየዘረጉ ከእዚህ በኋላ
አባትክ ነኝ ፤አባቴ ብለክ ልትጠራኝ ትችላለክ አንተም ልጄ ነክ
ልጄ ብዬ እጠራካለው" አሉት። አዳም በደስታ ወንበሩን በፍጥነት
ዞሮ ወደ ዶክተር ሄዶ አቀፋቸው። ዶክተርም አቀፉቸው
አመሰገናቸው "አመሰግናለው አባቴ ብሎ ፈገግ" አለ።
፨ዶክተርም ጮክ ብለው ሳቁ አዳምም ሳቀ።ከዛም ዶክተር "በቃ
አሁን ሄዋንን ይዘካት መሄድ ትችላለክ" አሉት። እሺ በቃ "ግን ነገ
ስመጣ ሌላኛዋን ሄዋን ያሳዩኛል" አላቸው ዶክተርም "እሺ በል
እንካ" ብለው መዳኒቱን ሰጡት ። በመቀጠል ተስማምተው
ተስናበቱ ዶክተርም ወደ ስራቸው አዳምም ወደ አለሙ ህይወቱ
ሄዋን ተመለሰ። ሄዋን ጋር ሲደርስ ሄዋንን እና ቦስን አገኛቸው።
"ዲናስ" አለ አዳም። ቦስም "ወጥታለች ስልክ ልታወራ" አለ።
በበሸቀ ድምፅ ወዲያው ዲና መጣች። አዳም "አሁን ሁላችሁንም
አንድ ነገር ልንገራቹ። ዛሬ አሁን ሄዋንን ወደ ቤት ይዘናት መሄድ
እንችላለን ዶክተር የሄዋን መውደቅ ጥቅም እንጂ ጉዳት
አላስከተለባትም አሉኝ። ስለዚህ በቃ እንሂድ ይህንን መዳኒት
ለቁስሏ ገዝተው ሰጡኝ እና ደሞ ልክ እንደ አባትክ እየኝ አባቴ
በለኝ አሉኝ" አላቸው...

                     ይቀጥላል...


.............. ••● ●•..............        

☛ በ 𝚈𝙾𝚄𝚃𝚄𝙱𝙴 ይከታተሉን
                    
           https://bit.ly/2XS2ecv

☛ በ 𝙵𝙰𝙲𝙴𝙱𝙾𝙾𝙺 ይከታተሉን
                     
            https://bit.ly/3ja9o3O

☛ በ 𝙸𝙽𝚂𝚃𝙰𝙶𝚁𝙰𝙼 ይከታተሉን
                      
            https://bit.ly/3rM2yop

☛ በ 𝚃𝙴𝙻𝙴𝙶𝚁𝙰𝙼 ይከታተሉን
                       
            https://bit.ly/3mDyzfx

                 ◎◦#ሼር◦◎
                 ◎◦#ሼር◦◎

@Yefiker_Gojo   ||       @AbenaG
━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━