Get Mystery Box with random crypto!

“የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለ | feker songs

“የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።”1ኛ ዮሐ 5፥20

የመጣው የእግዚአብሔር ልጅ የተላከ ነው።የላከውም "አባት" ተብሎ የተገለጠው አብ ነው።
ኢየሱስ ስመጣ አይደለም ልጅ የሆነው ።ይልቁንም ልጅ ስለሆነ ነው የመጣው ።
የልጅነቱ ጅማሮ ሆነ ፍጻሜ የለውም።እርሱ ብቸኛ የእግዚአብሔር ልጅ ነው።ምክንያቱም እርሱ ብቻ ነው ከአብ ጋር የነበረ ፣ልገልጠውም የሚችል ፣ያልተፈጠረ እና በመለኮቱ እኩል የሆነ።
ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ልቡናንም የሰጠ ወይንም የሚሰጥ ነው።ከአምላክ በቀር ልቡናን ልሰጥ የሚችል ማን ነው!?ማንም። "የሚያበራው ብርሃን" በእርሱ ዘንድ ጨለማ የሌለው አምላክ ነው።
እውነተኛ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞም ሌሎችን የታመኑትን ደግፎ የያዘ ነው።ሰዎች ልታመኑበት የሚችሉት አምላክ ነው።
ኢየሱስ እውነተኛ አምላክ ነው።ደግሞም ለሁሉም የሚሆን ሕይወት ነው።የዘላለም ሕይወት ራሱ ኢየሱስ ነው ።
የዘላለም ሕይወት ማንነት ነው እንጂ ቦታ አይደለም ።ያም ኢየሱስ ነው።ኢየሱስ አምላክ ካልሆነ እንዴትስ የዘላለም ሕይወት ይሆናል !?

[[ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አምላክ ነው፤የዘላለምም ሕይወት ነው።]
...