​​​ ✿የተራራቀ ልብ✿         አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ         | የፍቅር ጥቅሶች [SCAM]

​​​ ✿የተራራቀ ልብ✿

        አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ 


             ክፍል 14

... እእ እና ታድያ ገብቶህ እንዳልገባህ ስትሆን ነዋ አልኩት እና ከአንደበትሽ መስማት ስለምፈልግ ነዋ አለኝ እንደውም አልነግርህም ስለው ኧረ ወደሽ ነው በግድሽ አልኝ ባልነግርህ ምን ታመጣለህ አልኩት እጮኻለው አልኝ ወንድ ስለው ሊጮህ ሲል እፉን ያዝኩት አበድክ ስለው አዎ አሁን ሳይሆን ገና አንቺን ያየው ቀን አለኝ ወረኛ አሁን አትፈላሰፉ አልኩት እየተፈላሰፍኩ አይደለም እውነት ነው አንቺስ አለኝ አይኖቹን አይኖቼ ላይ ተክሎ ምን ይመስልኸል አልኩት እኔ እራሴን ከምወደው በላይ አብልጠሽ እንደምትወጅኝ እእ ትክክል ነኝ ሲለኝ አዎ ብዬ ገፍትሬው እየሮጥኩ ልወጣ ስል እጄን ይዞ ወደ ደረቱ ልጥፍ አረገኝ እኔም እቅፉ ውስጥ ስገባ ሌላ አለም ውስጥ የገባው መሰለኝ የሆነ  የስልክ ጥሪ እኔንም እርሱንም ካለንበት መአበል ፈልቅቆ አወጣን አክስቱ ነበረች መኪናው እንደደረሰና እንዲወጣ ነገረችው እሺ አለና ሻንጣውን ይዞ እንደመውጣት አለና ተመልሶ መጥቶ ግንባሬን ስሞኝ ወጣ ከዛም ተከትዬው ወጣው ማም ልትሄድ ነው ስትለው አዎ ማም በቃ ቻው እየመጣው እጠይቃችኃለው አልና ተሰናብቶን ወጣ በአይኔ መኪና ውስጥ ገብቶ እስኪሄድ ከሸኘውት በኃላ እቤት ገባው እና ቁጭ እንዳልኩ ለካ ትላንት መቅዲ ያስከፉትን ነገር ሳትጨርስልኝ ነበር ስደውል ስልክ አታነሳም ድግሜ ስደውል ተይዝዋል ይለኛል በቃ ሚስኮል አይታ ትደውላለች አልኩና ስልኬን ቁጭ አረኩት ብዙም ሳትቆይ ደወለች ምንድነው ስልክ ማታነሽው አልኳት ኧረ ስደውል ተይዝዋል ብሎኝ እኮ ነው አለችኝ የት ነሽ ስላት እቤት ነኝ ፈለግሽኝ ስትለኝ አዎ መምጣት ትችያለሽ አልኳት የት እቤት አለችኝ አይ ሰፈር ወጣ በይ እኔም ንፍስ መቀበል አምሮኛል አልኳት እሺ በቃ ውጭ መጣው አልችኝ እና ተሰነባብተን ስልኩን ዘጋነው ከዛ ከ 15 ደቂቃ በኃላ ውጭ አለችኝ ደውላ እሺ ብያት ወጣን ከዛም በማርያም ቤተክርስቲያን በኩል ወክ እያረግን ማውራት ጀመርን ከዛም ከአንዱ መቀመጫ ድንጋይ ላይ ሄደን ቁጭ አለን እና መቅዲዬ የባለፈውን ቀጥይልኝ እንጂ አልኳት እሷም ለማውራት ትንሽ ካንገራገረች በኃላ ለመናገር ጉሮረዋን ጠረግ ጠረግ አርጋ በቃ ከናቲ ጋር በቴሌግራም ማውራታችን ቀጠልን ግን እኔ ምንም አይነት ነገር ለእርሱ አልነበረኝም ያው ጉረኛ ስለሆነ ትንሽ ላስተንፍሰው ብዬ እንጂ አንድ ቀን ግን ምሳ ሰአት ላይ ኪሩቤል የሚባል ልጅ ሊያወራኝ እንደሚፈልገኝ ነገረኝ እኔም እሺ ብዬው የምንገናኝበትን ቦታ ነግሮኝ እርሱን ለማግኘት ሄድኩ ኪሩቤል በጣም ደስ የሚል ተጫዋች የደስ ደስ ያለው ልጅ ነው ደግሞ ሲስቅ ድምፒሉ እንዴት እንደሚያምር እና እርሱ ጋርም እንደደረስኩ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ በጣም ትልቅ ነገር እንደሚነግረኝ ነገረኝ ምን እንደሚነግረኝ ብዙ ነገር እያወጣው እያወረድኩ ምን ሊነግረኝ እንደፈለገ ጠየኩት እርሱም እንዲህ በማለት ጀመረ ብዙ የፍቅር ጥያቄዎች ደርሰውሽ ይሆናል ብዙ ሰዎችንም ተተዋውቀሽ ይሆናል ግን አሁን የምነግርሽ ሰው በጣም ከልቡ የሚወድሽ እራሱን እስከመጣል የደረሰልሽ ሰው ነው ከአንቺ በፊት ብዙ ሴት ቢያቅም ነገር ግን የትኛዋንም ልክ እንዳንቺ ወድዶ አያውቅም አለኝ ምንም ማለት አቅቶኝ ዝም ብዬ እሰማው ነበር አሁን ላይይ አንቺ ለእርሱ ምንም ስሜት ባይኖርሽም እስከ መጨረሻው እንደሚጠብቅሽ እርግጥኛ ነኝ አለኝ እኔም በመደንቅ ይሄን ያክል ልጁ ማን ቢሆን ነው እንዲህ ስለሱ እርግጥኛ ሆኖ የሚያወራው አልኩና ማነው እርሱ አልኩት ከዛም መናገር ያቃተው ይመስል ዝም አለ እኔም አላስችል ብሎኝ ንገረኛ ማነው አልኩት አሁንም ምላሹን እየጠበኩ እእእ እባክሽ ስሙን ስነግግሽ እንዳደነግጭ ግን አንድ ነገር እወቂ መልስሽ ምንም ቢሆን እርሱ ከምታስቢው በላይ እንደሚወድሽ እሺ አለኝ እኔ ትዕግስቴ እያለቀ ማነው እርሱ አልኩት እእእ እሺ እነግርሻለው ግን ባትወጂው እንኳን አትጥይው አለኝ ሳላውቀው በመጀመሪያ ልጁ ማነው አልኩት እርሱም በጣም በመጨነቅ ስሜት ሆኖ እእእ እኔ እራሴ ነኝ አልኝ ድርቅ ብዬ ቀረው ምን አልኩት አዎ እኔ ነኝ መቅዲ አንቺ ሳታቂ ለብዙ ጊዜ ወድጄሻለው አንቺን ለመርሳት ከብዙ ሴት ጋር ሆኛለው ግን አልቻልኩም አንዴ ልቤ ላይ ተፅፈሽ የማይጠፍ እስክርፒቶ ሆነሽብኛል መቅዲ መልስሽ ምንም ቢሆን አንቺን መውደዴን አላቆምም አለኝ እልሻለው ስትለኝ የሆነ ፊልም የምትነግረኝ ነበር የመሰልኝ ቀጥይ በሚል አስተያየት እያየዋት ቅንድቤን ከታች ወደላይ ከፍ በማድረግ ቀጥይ አልኳት እርሷም ይሄን ነገር ኪሩቤል ከነገረኝ ቀን ጀምሮ ስለሱ ማሰብ ጀመርኩ ከዛ ግን ስልኬን ማን እንደሰጠው ባላውቅም ቴሌግራም ላይ ሀይ ብሎ ላከ እኔ መልስ ከመመለሴ በፊት ፕሮፍይል አይ ስለነበር የእርሱ መሆኑን አውቅኩ እና ከትንሽ ቀን በኃላ እኔም ሀይ ብዬ መለስኩለት ከዛ ለረጅም ጊዜ ማውራት ጀመርን ቀስ በቀስ በጣም እወደው ጀመር እና በመሀል ስለ እኔ እና ናቲ መወራት ጀመረ እኔ እና ናቲ አንድ ላይ እንደሆንን ማውራት ጀመሩ አንድ ቀን ግን ክፍል ውስጥ ያለመደባቸውን ትዕዛዝ እንጫወት ብለው ናቲ እኔን እንዲስመኝ ታዘዘ ከዛ ልሳምሽ አለኝ ላሳፍረው ስላልፈለኩ እሺታዬን አንገቴን በመነቅነቅ ገለፅኩለት ከዛ ልክ ገና ሲስመኝ የክላስ ተማሪዎች በጩኸት ክፍሉን ቅውጥ ግማሾቹ ፎቶ አነሱንና ቴሌግራም ላይ የአመቱ ምርጥ ፍቅረኛማቾች ብለው ግሩብ ላይ በተኑት ይመስለኛል ናቲ ጎበዝ እና ቆንጆ ጉረኛ ስለሆነ ይመስለኛል እንዲህ ያካበዱት ከዛ ግን...

   ✎  ክፍል አስራ አምስት  ከ50 Vote በኋላ ይለቀቃል....  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ማድረግ አይርሱ። 


┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄
             
 ╔═══❖• •❖═══╗
         #ፍቅር_ያሸንፋል

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                   #እውነተኛ ስሜት

ቻናላችንንይቀላቀሉ
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት
የፍቅር ጥቅሶች [SCAM]

የፍቅር ጥቅሶች [SCAM]

@yefeker_tiksoche
3.82K ተመዝጋቢዎች
ጥቅሶች ምድብ
✅ይህ ቻናል በ 0.00 ብር👌 እና ያለ ምንም MB package👌 ነፃ internet የምንጠቀምበት የቴሌግራም ቻናል ይሆናል💯 :: መልካም ቆይታ !❤️...