Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅር ፍቅር ብሎ ሰው ሁሉ ሲያወራ ይመስለኝ ነበረ የማይሆን ፉከራ ዛሬ ተራው ደርሶ ተያዘና ልቤ | ❤ የፍቅር ነገር ❤

ፍቅር ፍቅር ብሎ ሰው ሁሉ ሲያወራ
ይመስለኝ ነበረ የማይሆን ፉከራ
ዛሬ ተራው ደርሶ ተያዘና ልቤ
ሀሳቤ ሆናለች ሰውራኝ ከቀልቤ
ደፍሬ አልነግራት አይኗ ያስፈራኛል
በፍቅርሽ ሰቀቀን ወስዶ ይጥለኛል
ደፍሬ አልነግራት ውስጤ እንቢ ይለኛል
እንዳትጎዳብክ ዝም በላት ይለኛል
ፍቅርሽ ከነከነኝ አፌም ማውራት ፈራ
ማፍቀሬን መናገር ሆኗል ከባድ ስራ
እስቲ ብርታት ሁኚኝ ልብሽን ላግኘው
ጎጆዬን ልስራበት በፍቅሬ ላክመው

   @yefeker_neger