Get Mystery Box with random crypto!

#ምርጡን_ዘር_ዝራ ውብ መናፈሻ ለመስራት ያገኘኸውን ዘር ሁሉ አትዘራም፡፡ አዎ! መጀመሪያ የምትፈ | ❤ የፍቅር ነገር ❤

#ምርጡን_ዘር_ዝራ

ውብ መናፈሻ ለመስራት ያገኘኸውን ዘር ሁሉ አትዘራም፡፡ አዎ! መጀመሪያ የምትፈልገውን የአበባ አይነት ትለያለህ፡፡ ቀጥሎ ዘሩን ትመርጣለህ፡፡ አበባው እንዲያብብ ትክክለኛውን መመሪያ በመከተል ትንከባከበዋለህ፡፡

ዘር ዘርተህ ለተወሰኑ ጊዜያት ምን እንደሚሆን ምንም መረጃ አይኖርህም፡፡ ነገር ግን ከተንከባከብከው እንደሚያፈራ ታውቃለህ፡፡

የዚህን ተመሳሳይ አመለካከት ለአእምሮህ አስተዋውቀው፡፡

አሉታዊ ልምዶች ካንተ ጋር ከርመዋል፡፡ አዎንታዊ አስተሳሰብ መስራት ይጀምራል፡፡ ግን ልክ እንደ ዘሩ ለመጽደቅ የተወሰነ ጊዜ ያስፈልገዋል፡፡ ስለዚህ ውጤታማና አዎንታዊ አስተሳሰብ ይዘህ ተጓዝ፡፡ ቀስ በቀስ የአዲሱን አስተሳሰብ መስመር ማንጸባረቅ ትጀምራለህ፡፡

ሁልጊዜም ያለማቋረጥ ምርጡን ዘር መዝራትህን ቀጥል።

@yefeker_neger