Get Mystery Box with random crypto!

......#እኔም_ልረሳው..... በፍቅር ጎዳና አብረን እንዳልሄድን እጅሽን ከእጆቼ እንዳላቆላለፍን | ❤ የፍቅር ነገር ❤

......#እኔም_ልረሳው.....
በፍቅር ጎዳና አብረን እንዳልሄድን
እጅሽን ከእጆቼ እንዳላቆላለፍን
ዛሬ ቀን ጥሎነ...
በትዝታ ፍቅር መኖር ብቻ ሆነ
ለምን አንች እረስተሽኝ እኔ ልጨናነቅ
ባንዴ እንኳ ባልችል በጌዜ ቆይታ ከእቅፍሽ ልራቅ
መራቅ ይቻል ይሆን ለራሴ ጠየቅሁ
የፍቅርን ማዕበል እየሰነጠቅሁ
ያን ሁሉ አልፌ ለዚህም ደረስሁ
ለትንሽ ቀናትም አንች ጋ ነበርሁ

ዛሬ ግን ......

ስለ ተከተልኩሽ መራቅሽ ሳይገርመኝ
ያስጨንቀኝ ጀመር እኔን ሊረብሸኝ
በቃ እኔም ልርሳው ያን ሁሉ ትዝታ
በጊዜ እርዝማኔ በአመታት ቆይታ
ትውስታም ይጠፋል ህይወት ይጀምራል በአዲሱ ገፅታ...
በመንፈስ እርጋታ...




,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

@yefeker_neger ,,,,,, @Abdu_ke
━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━