Get Mystery Box with random crypto!

.......... ውዴ አፈቀርኩሽ ብላቸው ጠግበህ ሳትበላ ይሉኛል... ላገባሽ እሻለሁ ብላቸው ለ | ❤ የፍቅር ነገር ❤

..........

ውዴ አፈቀርኩሽ ብላቸው ጠግበህ ሳትበላ ይሉኛል...
ላገባሽ እሻለሁ ብላቸው ለራስህ ሳትሆን ይሉኛል....

ፍቅር ማለት ጠግቦ ለሠው መኖር አይመስለኝም..ለራስ ሆኖ ለሌላ ሰው ማሰብም አይመስለኝም..ማንነት ሳይኖረኝ አንቺን በማፍቀሬ ማንነት ኖሮኛል።።፣።


ሠላም ስልሽ በመጥፎም ይሁን በጥሩ አይተሽኝ ስታልፊ በህይወት መኖሬን አረጋግጫለሁ..እኔና ቤቴ ከጨለማ ወጥተን በፍቅርሽ ብርሃን ተንቆጥቁጠን፤ ልቤ ገነት ሆኖ ደምስሮቼ ወደገነት መግቢያ እንደሚወስዱ መንገዶች ቢጫ ቀለማትን ይዘው በተስፋ ተሞልተው፤ የመኖር ትርጉሙን ተረድተው ፤እጆቼ ጣቶችሽን ተመኝተው አይኖቼና ጆሮዬ አይንሽንና ቃላቶችሽን ናፍቀው
ቁጭ ብዬ እጠብቅሻለሁ......
የኔ ፍቅር ሠው የለኝ አማላጅ እንዳልክ እኔው እንዳልመጣ የማወጋሽን አላውቅም።
........... ••● ●•............
@yefeker_neger || @Abdu_ke
━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━