Get Mystery Box with random crypto!

ዲና{DINA} {ተከታታይ ልበ-ወለድ} @yebirihan_lijoch ''''''''''''' | የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

ዲና{DINA}
{ተከታታይ ልበ-ወለድ}
@yebirihan_lijoch

""""""""""""""""""ክፍል """"""""""""

እስኪ ነጋ ጨንቆኛል እስከ 10:24 እንቅልፍ እንቢ እንዳለኝ ነበር ማስታውሰው ስነቃ 5 ሰአት :20 ይላል ደንግጬ ቶሎ ተነሳው ሳሎን እነ ዝኑ እማን እያሳመሩአት ነበር የአባቴ ዘመዶች ከያሉበት መጥተው እዛ የቤተሰብ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል እኔ ግን ይሄ እያለ እዩ ሚነግረኝ እያለ ተጋድሜያለው ዝኑ አንቺ እናትሽ ስትሞሸር ትተኛለሽ አለችኝ እማ የሌለ አምሮባታል ውብዬ ሙች አፈሰሽ ስላት ሞጥሟጣ ብላ ፈገግ አለች ምን ትሽኮረመሚያለሽ በስተርጅና ሙሽርና ስላት ሂጂልኝ ለነገሩ አንቺን የምታክል አሮጊት አድርሼ እንዴት አላረጅ ዝኑ እናንተ ቀልዳቹ አያምርም ሆሆሆሆ ይልቅ እዩ አስሬ ሲመላለስ ነበር እቤት እየጠበቀሽ ይሆናል አለችኝ ምን እዩ ድንብርብሬ ወጣ ቶሎ ፒጃማዬን ቀየርኩት ሉለት ቦታ የተሰራውን ፀጉር ፈትቼ በተንኩት በህይወቴ ተፈቶ ተለቆ አያውቅም ሳላጋንን ፀጉሬ ረጅም ነው ።

አሁን ምን እንዲ ያረገኛል እራሱ ያኔ ለልደቴ የሰጠኝን ቀሚስ ለብሼ ሄድኩ ስሄድ ሁለቱም እቤት የሉም ተናድጄ ለማቲ ደወልኩና የት ናቹ አልኩት ውይ እኛ ቤት ነይ አለኝ ስሄድ ለሁለት መዝሙር ከፍተው እንደ እብድ እየሆኑ ነው አላዩኝም ነበር ድምፁ ጆሮ ይበሳል ረጅም ደቂቃ ሁኔታቸው ገርሞኝ ዝም ብዬ አየኋቸው ድንገት ማቲ አየኝና ቆመ እዩም ሲዞር ተገትሬአለው ምን እንዳስደነገጠኝ ባላውቅም ልቤ መታ መዝሙሩን ዘጉት ነይ ቁጭ በይ ወዷ እህቴ አለኝ ማቲ እነ እማ ጥለውን ሊሄዱ እኮ ነው አልኳቸው አይ ዲኑ አሁን ለዛ ነው እንዲ ልዕልት መስለሽ የመጣሽው እዩ ምነግርሽ ነገር አለ ስላለሽ ነው አለኝ ሂድ ወረኛ እናቴና አባቴ በድጋሚ አንድ ሲሆኑ ላልዘንጥ ነው አልኩት አአአ አትካጂ በቃ ተረድተንሻል አደል እዩ ሲለው ታዲያስ ነው እሺ ቻው ደህና ሁኑ ብያቸው ተነሳሁና ሶስት እርምጃ እንደተራመድኩ እንዴ ዲኑ ብሎ ከፊቴ መንገድ ዘጋብኝ ምነግርሽን መስማት አትፈልጊም አለኝ እንዴ ንገረኛ አልኩት እየተፍለቀለኩ ማቲ አቤት ወረኛ ልትሄጂ አልነበረ ሂጂአ አንተ ምቀኛ አፍህን ዝጋ አልኩት ።

@yebirihan_lijoch

እዩ ዲኑ ምን መሠለሽ እስከዛሬ ያልነገርኩሽ ለእኔ ያለሽ አመለካከት ተቀይሮ እህትነትሽን እንዳላጣ ነበር አንቺን ምገልፅበት ቃል የለኝም ብቻ ከቀረበከቸው ከማውቃቸው ሴቶች በሙሉ ትለያለሽ ተመስጬ እየሰማሁት ልቤን ልተፋው ነው እና ዲኑ እህቴ ብቻ ሳይሆን የወደፊት ሚስቴም እንድትሆኚ ነው ምፈልገው እወድሻለው ብሎ እርፍ


ሰው አይግደረደርም እኔ እህታቹ በአንዴ እኔም እወድሀለው ብዬ ጥምጥም አልኩበት የዚህኔ ማቲ በፉጨት አደነቆረን ከዚያ ወደ ቤት ስንሄድ ብሩኬም ሪቾም ዝኑም መአዚም ቤቢም ሁሉም ዘንጠዋል ተሰብስበን ወደ አባታችን ሙሽራው ቤት በመኪና እየሄድን ነው ማቲ ወይ ጌታ ማታሳየን ጉድ የለም እኮ አለና ስሚ አባቢ ባይመጣ ኖሮ እኔና እዩ እንፋለጥብሽ ነበር ምን አልባት አንቺም እሺ ብትይኝ እህቴን አግብቼ ነበር ሆሆሆሆሆ ብሎ ፈገገሸ አለ የምር ስለው እዩ እና ያኔ ተቀያይመን የነበረው በአንቺው ነው የኔ እናት አሁን ለሱ እህት ለኔ ደግሞ የወደፊት ሚስት መሆንሽ ነው እንግዲ ማቲ ግን እንኳንም ወንድሜ ሆንክ እንጂ ከስረህ ነበር እንዴት ሲለኝ እኔ 24ሰአት ስለዚ ደነዝ እንጂ አንተን እንደወንድም በትርፍ ጊዘሰ ባባስብህ ነው ብዬ ሳኩበት ተረፍኳ እዩ ራሱ በጉራ አቃጥሎ ይደፋኝ ነበር በሉ በሉ እዛው በፀበላቹ ስሙ ደግሞ ከኔ ትዛዝ ውጪ ንቅንቅ የለም ምክኒያቱም እህቴ ናት አለና ፈገግ አለ ክቡር ፍርድ ቤት ተቃውሞ አለን የ2ወር ታላቆት መሆኔን አይርሱ አልኩት ።
እንዲሁ ስንዛዛግ ደረስን የሚገርም አቀባበል ተደረገልን ሰርግ ነው ሚመስለው ያላወቅናቸውን አጎት አክስት ምናምን ተዋወቅን ብዙ የአክስትና የአጎታችንን ልጆች ተዋወቅን ደስ የሚል ቀውጢ እሁድ አሳለፍን እዩ ማክሰኞ ይሄዳል እኔ ሀሙስ ማቴ ደግሞ መጪው ሰኞ የጊቢን ህይወት ልንቀላቀል ነው ......



............ይቀጥላል........

@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch