Get Mystery Box with random crypto!

ዲና{DINA} {ተከታታይ ልበወለድ} @yebirihan_lijoch ''''''''''''' | የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

ዲና{DINA}
{ተከታታይ ልበወለድ}
@yebirihan_lijoch

"""""""""""""""ክፍል """"""""""""""""

ገባን ና ሰላም ብለናቸው ቁርስ በልተን እዩና ማቲ መጡ እነሱም ሰላም ብለዋቸው ትምህርት ቤት ሄድን ።
ሰሞኑን እቤት መመላለሳቸውን ተያይዘውታል ጭራሽ ምሳ ተጋብዘው ዝኑ መአዚ ብሩክ ና እማ ሪቾ ፈቀደ ጋር ሊሄዱ ነው ሰዎቹ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የዘመናት ቂማቸውን ይቅር ተባብለው እርፍ እንዲህ እንዲያ እያሉ 4 ወራት ተቆጠሩ እኛም ኢንትራንስ ወስደን ውጤት እየተጠባበቅን ነው እረፍቱ ደስ የሚል ነው ታትዬ ሁሌ ነው ምትደውልልኝ እዛ የአጎቴ ልጆች ስላሉ ከነሱ ጋር ተመቻችታ መመለስም ሳይደብራት አልቀረም ።
@yebirihan_lijoch

ፍሬ ወደ አሜሪካ ተመልሳለች አባታችን እማን ወደ ቤቱ ሊያስገባት ጥረት ላይ ነው እማ ግን እኛን ፈርታን ይሁን የነዝኑ ጉርብትና አሳስቧት ይሁን አሻፈረኝ አለች እነ ዝኑ ግን እንድትሄድ ፈልገዋል ምክኒያቱም እኔ መጪ አመት አብሬአት አልሆንም ዝኑም በርግጥ ብቻዋን ናት
ግን እንድትገባ ዝኑም መአዚም ብዙ ጨቀጨቋት አሁንም እንደምትወደው ና አብራው መኖር እንደምትፈልግ አውቃለሁ በዚህ ሁሉ ጊዜ ለኛ ለወደፊት ህይወት በማለት ጠንክሮ ከመስራት በቀር ሌላ ህይወት አልጀመረም እኛ እንዳይደብረን ከሆነ ብለን ማቲ እኔና እዩ ለመንናት ኸረ እማ ታትዬ እንኳን ሰምታ ደስ ብሏታል ይቅር ብለሽው የለ አልኳት ይቅርማ ብዬዋለው እና በቃ ቂም ከሌለብሽ ለምን አብራቹ አትኖሩም አልናት በስተመጨረሻም ተስማማች

@yebirihan_lijoch

እኛም ውጤት መጥቶልን ወደ ጊቢ ልንሄድ ነው ማቲ አርባ ምንጭ እዩ አዲስ አበባ እኔ መቀሌ ተመደብን ለመሄድ ዝግጅት ጀምረናል ።
በጣም እየከፋኝ ነው ከሁለቱ ተለይቼ ሰው መልመድ እንዴት ችላለሁ እዩ ከብዙ ወራት በፊት ሊነግረኝ የነበረውን ነገ እንደሚነግረኝ ነግሮኛል ነገ እሁድ ነው
ማቲም ደግሞ እንቅልፍ አጥተሽ እደሪ አሉሽ አለኝ እናስ ግን ምን ሚነግረኝ ይመስልሀል አልኩት የሆነች ሚወዳት ልጅ አለች እንድታናግሪለት ነው ብሎ አቀፈኝና እየሳቀ ተከትሎት ሄደ ምን እዩ ሚወዳት ልጅ አለች በአንዴ ውስጤ ድብልቅልቁ ወጣ ለምን ከፋኝ አንዴ አለቅሳለሁ አንዴ በንዴት እቃ ወረውራለሁ ውብዬ ሁኔታዬ ግራ አጋባት ምነው ልጄ ነገ አባትሽ ጋር ልገባ ስለሆነ ነዋ አለችኝ ኸረ እናቴ እሱማ ደስ ነው ሚለኝ ብዬ የሆነውን ስነግራት ኸኸኸኸ አደግሽ ማለት ነው ገብቶኛል ድሮም የሱ ስም ሲነሳ የሚያረግሽን ሲያሳጣሽ ጠረጥር ነበር በይ በይ ከራሱ አንደበት ሳትሰሚ አትነፋረቂ ተኚ ብላ ግንባሬን ስማኝ ወደ ሳሎን ሄደች እውነቷን ነው ባልተረጋገጠ ነገር የምን ያዙኝ ልቀቁኝ ነው ። እስኪ ነጋ ጨንቆኛል .........


..........ይቀጥላል............

@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch