Get Mystery Box with random crypto!

የብርሃን መንገድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yebirhan_fiker — የብርሃን መንገድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yebirhan_fiker — የብርሃን መንገድ
የሰርጥ አድራሻ: @yebirhan_fiker
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 856
የሰርጥ መግለጫ

@yebirhan_fiker
@yebirhan_fiker

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-07 17:27:38 የሰንበት ወግ
"ቃለ መጠይቃዊ ቅርበት"

(አልታየህ ኪዳኔ)

ቃላት ረቂቅ ናቸው። ቃላት ውስጥ ሃሳቦች አሉ። መፅሀፎች በቃላት ተገንብተዋል። ግዑዛን አይደሉም አፍ ባይኖራቸውም ያወራሉ። ቃላትና ሃሳቦች የአንድን መፅሀፍ ማንነት ይገልፃሉ። ከይመስላል ዘላለም መፅሀፍ ጋር ጥቂት ቆይታ አድርገናል።

አ ፦ በመጀመሪያ ለቃለ መጠይቅ ፈቃደኛ ስለሆንክ እናመሰግናለን።

* ይመስላል ዘላለም ፦ እኔም አመሰግናለሁ።

አ ፦ ይመስላል ዘላለም የሚለው መጠሪያህን እንዴት አገኘህ?

* ይመስላል ዘላለም ፦ ደራሲዬ ነው ያወጣልኝ። ምን መሰለህ ህይወት ውስጥ መንታ ተፃራሪ የህይወት ገፅታዎች አሉ። ደስታ አለ ፣ ሀዘን አለ። ሰላም አለ፣ ነውጥ አለ። ነፃነት አለ፣ ባርነት አለ። ሌላም ... ሌላም ብዙ ብዙ ነገሮች አሉ። አሁን እኔ ለመግለፅ የፈለግኩት እነዚህ የህይወት ገፅታዎች ውስጥ ያለ የጊዜን ሃያልነት ነው። ለምሳሌ አንድ ከባድ የሞራል ጉዳት የደረሰበት ሰው በወቅቱ የሚኖረው ስሜት ልክ ሰማይ የተደፋበት አይነት ነው የሚመስለው። ይህ ስሜት ዘላለም ይመስላል ግን አይደለም። ፍቅርም እንደዛው። ከምትወደው ሰው አጠገብ ስትሆን ፣ ከምትወደው ሰው ጋ እስከ እድሜ ማብቂያህ ድረስ ልትኖር ትችላለህ። ግን ዘላለም አይደለም። ደስታም ፣ ሀዘኑም ፣ ተድላውም ፣ ጉስቁልናውም ዘላለም ይመስላል ግን አይደለም።

አ ፦ የፊት ገፅህ ላይ በከተማችን የምናውቃቸው ህንፃዎች አሉ። ረዥም መንገድም ይታያል? ምንድነው ውክልናቸው?

* ይመስላል ዘላለም ፦ ምን መሰለህ ደራሲዬ የከተማ ሰው ነው። ታዲያ እዚህ ከተማ ውስጥ ሲኖር Observe የሚያደርጋቸው ነገሮች አሉ። በተጨማሪም እውነታውን አይቶ ነገሮችን የሚያዋህድበትና ለአከያየኑ ፈር የሚያበጅበት የራሱ መንገድ አለው። ደራሲ ለሚያየው ለሚሰማው እና ለእውነታው ቅን መሆን አለበት መሰለኝ። ህንፃዎቹ መቼቱን ለመግለፅ ነው የተቀመጡት። በተጨማሪም ደሞ የማያልቅ መንገድ አለ ፣ መዳረሻው የማይታወቅ ያ ደሞ አርእስቱን ይወክላል።

አ፦ ደራሲህ ከዚህ ቀደም 6 ስራዎችን ሰርቷል። ከእነርሱ (ወንድሞችህ) እበልጣለሁ ወይ አንሳለሁ ብለህ ታስባለህ ?

* ይመስላል ዘላለም ፦ እኔና ወንድሞቼ የየራሳችንን ሃሳብ ይዘናል። ሃሳብ ተዋረድና ደረጃ የለውም። ደረጃ ካወጣለትም አንባቢ ነው የሚያወጣለት። ሲያወጣለት ደግሞ አንባቢው የራሱ መለኪያ ሚዛን ይኖረዋል እንጂ ሃሳብ በራሱ አይበላለጥም። ለምሳሌ እዚህ እኔ ውስጥ ፀሀይ ለምን ቢጫ ሆነች የሚል አጭር ታሪክ አለ። እዛ ላይ ሰለሞን ደሬሳ ስራፈትነትም ስራ ነው ይላል። ምታስበው ምንም ይሁን ምን ሃሳብ ነው። የምታስበውን ጉዳይ መመደብ ሁለተኛ ደረጃን የሚይዝ ነገር ነው።

አ ፦ ፍፁም የተሰኘ አጭር ታሪክህ ውስጥ በሚከተለው የህይወት አኗኗርና ዘይቤ የጓደኞቹ መሳለቂያ የሆነ አንድ ገፀባህርይ አለ። ስለሱ ብትነግረን።

* ይመስላል ዘላለም ፦ ማህበረሰባችን የሚገዛባቸው ህጎች ፣ እሴቶች ፣ የአኗኗር ዘይቤዎች እንዳሉ ይታወቃል። socially construct የምትደረግበት መንገድም አለ። ማህበረሰብ ጥራትና ደረጃ መዳቢ ሲሆን አስቸጋሪ ነው። ተዋረድና መበላለጥ የሚፈጠሩት በማህበረሰቡ በሚያወጣቸው መስፈርቶች ነው። ብዙ ጊዜ በብዙ ድርሰቶች የለመድነው በማህበረሰቡ የተገፉ ሰዎችን ወደ መሀል የማምጣት ሜታፎር ነው። አሁን ደራሲዬ አንድ ሰይፉ የሚባል ገፀባህርይን ነው ወደ ተገፉት ሰዎች የሚልከው። በዚህ ድርጊቱ የሚደርስበትን ውግዘት እንዳነበብከው ነው። አንዳንዴ ማህበረሰቡን ካልመሰልክ የሚደርስብህ ጡጫ ከባድ ነው። የሚገርመው መካሪዎቹ ለመካሪነት የሚበቁ አለመሆናቸው ነው። አንባቢዎች ሙሉ ታሪኩን እኔ ውስጥ ያገኙታል።

አ፦ ስለ ግስ አርቢዎቹ የሚለው ታሪክ ብታጫውተን። የአንድ መፅሀፍ ውልደትና ሞት በአንዴ ይሆናል?

* ይመስላል ዘላለም ፦ አንድ ድርሰት ከደራሲው ከወጣበት ጊዜ በኋላ እድገቱ ያበቃለታል። ሊነካካ ፣ ሊታደስ ፣ ሊከለስ አይችልም። እድገቱ የሚያበቃው ተደራሲው ጋር ሲደርስ ነው። ሁለቱ ገጣሚና ፀሀፊዎች የስራዎቻቸው ውልደት እንደ ሞት ሆኖ እናያለን። ውልደት ሞትን አስከትሎ ሲመጣ እንደማለት ነው። ፍላጎት ብቻውን የምንፈልገውን ነገር ለማሳካት አያስችለንም። ትጋት እና ጥረት ከተሰጠንለት አላማ ጋር ሲጋቡ ነው ነገሮች የሚሰምሩት። ካልሆነ አንድ ቦታ ሙጥኝ በማለት የሚሆን ነገር የለም። ውድቀትም ቢሆን እየደጋገሙ መውደቅ ነው እንጂ ተስፋ መቁረጥ አያስፈልግም። ለዚህ ነው ጀርባዬ ላይ «የዶሮ እርባታውን የናቀው የግስ እርባታው ላይ በትጋት ተጠምዶ ቢሆን ኑሮ አንድ ነገር ነው። እሱ ዶሮውንም ግሱንም አያረባም። ወይንም የግስ እርባታውን ተጠቅሞ ለምን ዶሮ ማርባት እንደማይጠቅምም አይቀኝም» የሚለው ፅሁፍ የሰፈረው። በሌላ መንገድ ታሪኩ Sketch ነገር ነው። የግስ አርቢዎቹ ስራ Fail የሚያደርግበት መንገድ እንኳ አይነገርም።

አ ፦ መቼቱን የአረቄ ቤት ያደረገው የተጨማደዱት የሚለው አጭር ታሪክ ላይ ያልተጠበቀ ሰው እራሱን ሲያጠፋ እናገኛለን። ስለዛ ታሪክ ብታጫውተን።

* ይመስላል ዘላለም ፦ ህይወት አይገመቴ ነው። ድንገተኛ የሚፈጠሩ ነገሮች ውሳኔህን ፣ የህይወት አቅጣጫህን ይለውጣሉ። ነገር ግን የፈለገ እራስህ ላይ የመወሰን ስልጣን ቢኖርህም ቅሉ ልታደርግ የምትችላቸውን ነገሮች ነው እንጂ ሊፈጠሩ የሚችሉ ነገሮችን ማወቅ አትችልም። ህይወትን ጣዕም የሚሰጣት ደግሞ ያ ነው። አንዳንዴ በድርጊትህ ነው መሰለኝ እጣፋንታህን የምትወስነው። እነዛ አረቄ ጠጪዎች እገሌ ይሞታል እያሉ ሲጠቋቆሙ ነው የምናገኛቸው። ግን በውል ማን እንደሚሆን ሊያውቁ አይችሉም። ምናልባት ጠጪዎቹ እገሌ ቢሞት የሚል ምኞትም ሊኖራቸው ይችላል። ነፃ ፈቃድም ሊኖራቸው ይችላል። ግን የሚፈጠረውን ነገር ሊያውቁ አይችሉም። ምናልባት አንዲት ቅፅበት ያ ሰውዬ እራሱን እንዲጠያጠፋ ምክንያት ሆናው ሊሆን ይችላል። ክስተቱ የህይወት ድንገተኝነት ውጤት ነው።

አ ፦ ለነበረን ቆይታ አመሰግናለሁ።

* ይመስላል ዘላለም ፦ እኔም አመሰግናለሁ።

@yebirhan_fiker
@yebirhan_fiker
80 viewsedited  14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 17:26:44
82 views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 06:48:11 ታማኝነት መልሶ ይከፍላል

(አልታየህ ኪዳኔ)

ቆይ ስለዚህ ላይቤሪያዊ ታዳጊ ሰምታችኋል ወይ?
ከወራት በፊት ትልልቅ የአለም መገናኛ ብዙኋንን ትኩረት የሳበ ጀብድ ፈፅሞ ነበር።

ልጁና ቤተሰቡ ላይቤሪያ ውስጥ እልም ያሉ ድሆች ናቸው። ልጁ ዘየደ። "በዚህ ድህነት የምን ትምሮ ነው? " ብሎ ከትምህርት ቤት ወጣና ወላጆቹን በገቢ መደገፍ የሚያስችለውን ስራ ጀመረ።

ታዲያ ይሄ ምስኪን አንድ ቀን መንገድ ላይ በሞተር እየተጓዘ ሳለ በፌስታል ተጠቅልሎ የወደቀ አንድ እንግዳ ነገር ይመለከታል። ሄዶ ሲያነሳው 50ሺ የአሜሪካን ዶላር። ምቱት እስኪ በኛ :) መታችሁት ስንት ሆነ ?

ታዳጊው ድህነት ወዲያ ሰንብች ብሎ አገውኛ መጨፈር ሲገባው። ገንዘቡን ወስዶ ለባለቤቱ ምልስ። ይሄ ጅል አትሉም

ላይቤሪያ ውስጥ በዚህ ጉዳይ ያልተደነቀ የለም። የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ቤተመንግስት ድረስ አስጠርቶት አስር ሺ የአሜሪካን ዶላር ሸልሞታል። ዊሃ ታዲያ ቤተመንግስት ድረስ ያስጠራው ለምን ይመስላችኋል? ላይቤሪያ ውስጥ ምዝበራና ሙስና ጣሪያ ነክተዋል። እዛም ልክ እንደኛ ሀገር ባለስልጣኑ መዝባሪና ሆዳም ነው ለካ? ምናልባት እነ ሌቦ ከዚህ ልጅ መልካም ተግባር ቢማሩ ብሎ ነው ጠርቶ እውቅና የሰጠው። ሞተር ሳይክልም ጨምሮ ሸልሞታል።

... ምን ይሄ ብቻ ይህን ታማኝነቱን የሰማው አሜሪካን ሀገር ሰሜን ካሮላይና ግዛት ውስጥ የሚገኘው ሊቪንግ ስቶን ኮሌጅ የነፃ የትምህርት እድልን አመቻችቶለታል። የፀረ ሙስና አምባሳደር ሁሉ ተብሏል። በቃ ህይወቱ በአንዴ ነው የተቀያየረው ስልህ

እና ምን ልላላችሁ ነው። የኛ ሀገር ባለስልጣኖች እጃችሁን ሰብሰብ ብታደርጉልንና የህዝብ ሀብት ባትመዘብሩ። ምናልባት ምን ይታወቃል ለዚህ ተግባራችሁ እንደ ልጁ ወሮታ መክፈል ባንችል እንኳ ወደፊት መልካም ተግባራችሁንና ስማችሁን እያነሳን እናወድሳችሁ ይሆናል !!

@yebirhan_fiker
@yebirhan_fiker
250 views03:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 06:46:56
199 views03:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 15:20:13 1- አዳም አይገባንም የምትሉ ሰዎች በመጀመሪያ ከላይ በምድብ አንድ ውስጥ የመደብኳቸውን ስራዎች ማለትም ማህሌት ፣ ህማማት እና በገና ፣ ከሰማይ የወረደ ፍርፍር ፣ አለንጋና ምስር ን ብታነብቡ ጥሩ ነው። ቀላል ታሪኮች በተለመደው አፃፃፍ ስልት የተፃፉ ናቸው። ማጠንጠኛቸውም በእለት ተእለት ህይወታችን የምናያቸው ፍቅር ፣ ክፋት ፣ ምቀኝነት ፣ ኋላቀር ልማዶች፣ ማህበራዊ ጉዳዮች ... ወዘተ ላይ ያደረጉ ስለሆኑ ለመረዳት ምንም አዳጋች ነገር የላቸውም።

2- በሁለተኛው ምድብ ውስጥ ያስቀመጥኳቸውን የአዳም ስራዎች ማለትም ግራጫ ቃጭሎች ፣ እቴሜቴ ሎሚ ሽታ ፣ ይወስዳል መንገድ ያመጣል ፣ መረቅ ፣ የስንብት ቀለማትና ፣ አፍን ስታነቡ ስለ አፃፃፉ መንገዱ ፣ ስለ ቴክኒኩም ሆነ ስለመፅሀፉ ጠቃሚ ሊሆን የሚችል መጠነኛ የሆነ ግንዛቤ የሚያስጨብጣችሁን ነገር ለማግኘት ብትሞክሩ አሪፍ ነው። ለምሳሌ አዳም በተለያየ ጊዜ የሰጣቸውን ቃለመጠይቆች ብታዩና ብታነብቡ ፤ ስራው መሰረት ያደረገበትን የዘመን መንፈስ መረዳት የሚያስችላችሁን ነገሮች ለማየትና ለማንበብ ብትሞክሩ፤ በእርሱ ስራዎች ላይ የተሰሩ ዳሰሳዎች፣ ሂሶቹና ግምገማዎች ለማንበብ ብትሞክሩ ጥሩ ነው።

3- የንባብ ስልት ፦ አዳም በእኔ ንባብ ለዝርዝር ነገሮች ትኩረት ሰጥቶ ምናልባልት አንዳንዴ አንባቢን ሊያሰለች በሚችል መንገድ ነገሮችን ይተነትናል። አንባቢ በዚህ ጊዜ በእያንዳንዱ አረፍተ ነገር እና አንቀፅ ውስጥ ትርጉም እየፈለገ ከሄደ ችግር ነው። በሙሉ ትረካ ውስጥ ጠፍቶ መኳተንን የሚያስከትል ይመስለኛል። ስለዚህ የትረካን ድባብ እና Context በመረዳት ውስጥ ቢነበብ የተሻለ ሊሆን እንደሚችል ይሰማኛል።

በጥቅሉ ስነፅሁፋዊ ስራዎች ላይ የሚደረግ ውይይትም ሆነ ፣ በተለያየ ሚዲየም የሚደረግ ዳሰሳ፣ ሂሲ፣ ግምገማ ከባድ ነው የሚባለውን የሚያቀል፣ ሰፊውን ህብረተሰብ ለንባብ የሚጋብዝ እንዲሁም ለንባብ ባህላችን መዳበር ትልቅ አስተዋፅኦ ሊያደርግ እንደሚችል አምናለሁ።

@yebirhan_fiker
@yebirhan_fiker
280 views12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 15:20:13 መነሻ ሃሳብ - አሌክስ አብረሃም "አዳም ረታ በወዳጆቹ የታገተው ደራሲ" በማለት የፃፈው ፅሁፍ

(አልታየህ ኪዳኔ)

እንንደርደር ... የአዳም መጀመሪያ መፅሀፍ ማህሌት ነች። እንዳሁኑ ረዣዥም ልቦለዶች መፃፍ ከመጀመሩ በፊት ፅሁፍ የጀመረው በአጫጭር ታሪኮች ነው። ለብቻ ያሳተመው ማህሌት ሰማኒያዎቹ መጀመሪያ ነው የታተመችው። አዳም ለአሳታሚዎች ወስዶ ሲሰጥ አርእስቱ "ስዕል በብጥስጣሽ ጨርቆች ላይ" የሚል ነበር። በኋላ ላይ እዛ የሚሰሩት ሰዎች ናቸው ማህሌት ነው መሆን ያለበት አርእስቱ ብለው የለወጡት።

ከዛ በኋላ አዳም ሆላንድ ሄደ። አዳም ከማህሌት በኋላ በቀጥሉት አስራ ስድስት አመታት መፅሀፍ አላሳተመም። የህትመት ብርሃን አይዩ እንጂ በእነዚህ አመታት የበዙ አጫጭር ልቦለዶችን ፅፏል። አንዳንዶቹም በጋዜጣ ላይ ተነበዋል። ከግራጫ ቃጭሎች በኋላ በወጡት እቴሜቴ ፣ አለንጋና ምስር ፣ ከሰማይ የወረደ ፍርፍር ፣ ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ ፣ ህማማት እና በገና መፅሀፎች ውስጥ የተካተቱት አጫጭር ልቦለዶች የተፃፉት እንዳለ ሰባና ሰማኒያዎቹ ውስጥ ነው። አሁን መፅሀፎቹ እጄ ላይ ኑረው የእያንዳንዳቸውን አመቶች አልጥቀስ እንጂ ስራዎቹን ባነበብኩ ጊዜ ይሄንን የጊዜ Pattern እያጤንኩ ነበር። ምክንያቱም አዳም በየአጫጭር ታሪኮቹ መጨረሻና መጀመሪያ ላይ የሚያኖረው የግዜ ማስታወሻና ህዳግ አስረጂ ነው።
ቀጥሎም በ2007 ፣ 2008 እና 2010 መረቅ ፣ የስንብት ቀለማትና የመጨረሻው መፅሀፉ አፍ ላይ ደርሷል።

እስከዛሬ አዳም ረታ የመጣበትን የስነፅሁፍ መንገድ በ2 መክፈል የሚቻል ይመስለኛል።

ማህሌት ከወጣች በኋላ አዳም ግራጫ ቃጭሎችን እስኪያሳትም በነበረበት ጊዜ በርካታ አጫጭር ታሪኮችን እንደፃፈ ከላይ ጠቅሻለሁ። ሆኖም ግን በእነዚህ መፅሀፍ ባላሳተመባቸው አመታት አዳም ወደ ሌላ ስነፅሁፋዊ መንገድ እየሄደ እንደነበር ነው የሚሰማኝ።

አዳም የግራጫ ቃጭሎች መግቢያውን የፃፈው በ1983 ሆላንድ ሆኖ ነው። ይሁን እንጂ እስከማስታውሰው ድርሰቱ ስለተፃፈበት ጊዜ መፅሀፉ ላይ በውል አልተጠቀሰም። ይህንን ያነሳሁት ለምንድነው አጫጭር ታሪኮቹን ሰባና ሰማኒያዎቹ ውስጥ ይፃፍ እንጂ ግራጫ ቃጭሎችን ይዞ የመጣው አዳም ማህሌትን ከፃፈው አዳም እጅግ የተለየ ነው።

የግራጫ ቃጭሎቹ አዳም አከያየኑ ሌላ ነው ፣ ቋንቋ አጠቃቀሙ ሌላ ነው ፣ እንጀራን በሜታፎርነት የተጠቀመው አዳም ሌላ ነው ፣ አሁን ድረስ በሙክረት ላይ ያለውን ህፅናዊነት የሚለውን stylistic የፈጠረው አዳም ሌላ ነው። በአጠቃላይ አዳም በብዙ መልኩ የተለየ አዳም ሆኖ ነበር የመጣው።

ይህንን ይዘን የአዳምን ስራዎች በሁለት መመደብ የምንችል ይመስለኛል... [ ማህሌት ፣ ህማማት እና በገና ፣ ከሰማይ የወረደ ፍርፍር ፣ አለንጋና ምስር ] የመጀመሪያው ምድብ ውስጥ ሲገቡ ... ሁለተኛው ምድብ ውስጥ ደሞ [ግራጫ ቃጭሎች ፣ እቴሜቴ ሎሚ ሽታ ፣ ይወስዳል መንገድ ያመጣል ፣ መረቅ ፣ የስንብት ቀለማትና ፣ አፍ] ይገኛሉ።

እንግዲህ በምን መስፈርት ይህን ምድብ ሰራህ መባሉ አይቀርም።

አንደኛውና ዋነኛው አከያየን ነው። እዚህ አከያየን ውስጥ ደሞ ቅርፅ (form) ፣ ይዘት (content) ፣ እንጀራን ተከትሎ የመጣው የአፃፃፍ ስልት እንዲሁም ስነፅሁፉዊ ፍልስፍና (ህፅናዊነት) እና የተለያዩ ቴክኒኮችን መሰረት በማድረግ ይህን ምድብ መስራት የሚቻል ይመስለኛል።

እዚህ ጋር ሁሉም ሰው ሊገነዘበው የሚገባው ነገር የመጀመሪያ ምድብ ውስጥ ያሉት ማህሌት ፣ ህማማት እና በገና ፣ ከሰማይ የወረደ ፍርፍር ፣ አለንጋና ምስር ስራዎች ሁሉም የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ ናቸው።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ይህንን ምድብ ሳስቀምጥ ለምድብ አስቸጋሪ የሚሆኑ ስራዎቹ አሉ። ለምሳሌ እኔ የአዳም ልሂቅ ስራ ነው ብዬ የማስበው እቴሜቴ ታሪኮቹ አጫጭር ታሪኮች ሆነው እርስ በእርስ የተያያዙ መሆናቸው ለትርጉም አስቸጋሪ ያደርጋቸዋል። አጫጭር ልቦለዶች ወይስ ወጥ የሚል የትርጉም መቀናቀን ሊገጥመን ይችላል። ሆኖም የዚህ አይነት ቴክኒክ አንዱ አላማ አዳም እራሱ በአንድ ቃለመጠይቁ ላይ እንደገለፀው በአጫጭር ልቦለዶች እና በረዥም ልቦለድ መሃል የተቀመጠውን መበየኛ መስፈርት (Standard) አልያም ደሞ paradigm መቀናቀን ነው።

እንግዲህ የአዳም ስራዎች ከባድ ናቸው ወደ ሚለው እንምጣ። አንባቢ ከባድ ናቸው የሚባሉት ስራዎች ሁለተኛው ውስጥ ያሉትን ይመስለኛል። በተደጋጋሚ ሶሻል ሚዲያ ላይ ያየሁትም ይህንን ነው። [ግራጫ ቃጭሎች ፣ እቴሜቴ ሎሚ ሽታ ፣ ይወስዳል መንገድ ያመጣል ፣ መረቅ ፣ የስንብት ቀለማትና ፣ አፍ] ን ማለት ነው።

በተቃራኒው ደግሞ የመጀመሪያው ምድብ ውስጥ ያሉት . [ ማህሌት ፣ ህማማት እና በገና ፣ ከሰማይ የወረደ ፍርፍር ፣ አለንጋና ምስር ] ስራዎች ከባድ ሊሆኑ የሚችሉበት መንገድ አይታየኝም። ምክንያቱም ታሪኮቹ በአተራረክ መንገድ Linear የሆኑ ፣ በጭብጥ ረገድም በኋላ ላይ ከፃፋቸው ቀለል ያሉ ፣ የቋንቋ ትባታቸውም እንደኋለኛው ስራዎቹ ጠነን ያሉ አይደሉም።

የመጀመሪያዎቹ ምድብ ውስጥ ያሉት ስራዎች አንድ Story ለሚያነብ ሰው ምንም አይነት አባጣ ጎርባጣነት የሌላቸው ልሙጥ ታሪኮች ናቸው። ሁለተኛው ምድብ ውስጥ እንዳሉት የቅርፅ ፣ የቋንቋ እንግድነትም የሌላቸው ናቸው። ይህንን በድፍረት የምለው አዳም አይገባኝም ለሚል አንድ ወዳጄ አጫጭር ታሪኮቹን እንዲያነባቸው ሰጥቼው ያለምንም መደናገር መፅሀፉን ጨርሶ ሰጥቶኛል። ከዚህ ልምዴም በመነሳት ነው ይህንን የምለው።

እናም አሌክስ አብረሃም ያነሳው አዳምን የዚህ ሰፈር መበሻሸቂያ አድርገው ፣ አዳም የማይነካ አድርገው ሰቅለው ፣ አዳም ይከብዳችኋል እያሉ ሲንቦጣረሩ የነበሩ ወፈፍ የሚያደርጋቸው የፌስቡክ ሰዎች አንዳንድ አንባቢዎችን እንደገፉና እንዳራቁ ባምንም ከዛ ባሻገር ግን አዳም ያመጣው የአከያየን መንገድ (የቋንቋ ፣ የቅርፅ ፣ የይዘት...) እንግድነት ለአንባቢው ግርታን የፈጠረ ነው የሚመስለኝ። መክበዱም የመጣው ከዛ ጋ የተያያዘ ይመስለኛል። አከያየኑና ቴክኒኩ ሲቀየር ተያይዘው የመጡ ነገሮችም እንዳሉም እጠረጥራለሁ።

ሌላው የአይገባኝም ምክንያት ደግሞ የመቼት ጉዳይ ይመስለኛል። አንድን ልቦለድ ለመረዳት መፅሀፉ የተፃፈበት መቼት እና ስራው ከተሰራበት የዘመኑ መንፈስ ጋር ያለ ቅርበት ወሳኝ ነው። ይሄ ቅርበት በንባብ ፣ በመረጃ ፣ በይለፍ ይለፍ ወሬም ሊሆን ይችላል የሚኖረን ግንዛቤ ያንን ቴክስት ለመርዳት እጅጉን ይጠቅማል።

ለምሳሌ ጥቂትም ቢሆን የያ ትውልድ የዘመን መንፈስ መረዳቱ ለሌለው ሰው ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድን ፦ የ7 መንገዶች ወግ የሚለውን ታሪክ አልያም መረቅን እንዲያነብ ብታደርገው ስቶሪዎቹ Archetypal element ኖሮአቸው ሊነበቡ ቢችሉም አጠቃላይ ምስሉን ለማግኘት የሚቸገር ይመስለኛል። በተለይ በተለይ የአዳም አንዳንዶቹ ድርሰቶች ማጠንጠኛና መቼታቸውን የያ ትውልድ ላይ ስላደረጉ። እነዚህን ስራዎች ስናነብ የያን ትውልድ የዘመን መንፈስ ከግንዛቤ ውስጥ አስገብተን ብናነባቸው ጣዕም ጨምረው ሊሰጡ ግርታም ላይኖራቸው እንደሚችል አስባለሁ።

ለንባቡ አለመሳለጥ ችግር ሊሆኑ ይችላሉ ካልኳቸው ነገሮች ተነስቼ አዳም አይገባንም ለሚሉ አንባቢዎች ሃሳብ ላቅርብ።
211 views12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 19:22:31 ፍጡር መሆን እዳ

(አልታየህ ኪዳኔ)

ውድነህ ክፍሌን አብዛኞቻችን የምናውቀው በፀሀፊ ተውኔትነቱና በሬድዮ ድራማ ደራሲነቱ ነው። ነገር ግን አንድ ረዥም ልቦለድ መፅሀፍም ፅፏል። "ላማ ሰበቅታኒ" ይሰኛል። ከአራት አመት በፊት ነበር ያነበብኳት። ድብን ያለች ፋንጣዚ (የአዳም ረታ ቃል ናት ይህቺ) እና ሳታየር ናት።

ታሪኩ እንዲህ ነው። ወታደሩ ሀገሬን እከላከላለሁ ብሎ ጦርነት ሄደ። ሲመለስ አንድ አይኑን ፣ አንድ እጁን እና አንድ እግሩን እዛው ጦር ሜዳ ሰውቶት መጣ። ሞቷል ተብሎ ታምኖ ነበር። ታዲያ ሲመለስ ሚስቱ ሌላ ባል አግብታ ጡረታውን እየበላች ጠበቀችው። አማራጭ አልነበረውም መንገድ ላይ ወጣ። አንድ ቀን ምሽት መንገድ ዳር ቁጭ ብሎ ሳለ የተቀረው ብቸኛ እግሩ ላይ መኪና ሄደበት። የቀረው አንድ እግሩ በሃኪሞች ተቆረጠ።

ሰው በመሆኑ ተስፋ ቆረጠ። አንገሸገሸው። ብቸኛ ያለው ተስፋ አምላኩ ነው። ስለዚህ አምላኩን አምርሮ ለመነው። "ሰው መሆን አልፈልግም ስለዚህ ድመት አድርገኝ" ብሎ ተማፀነው። አምላክም ይሁን ደስ ይበልህ ብሎ ድመት አደረገው።

ግን ካልጠፋ ድመት የእትዬ አዘነጋሽ ድመት አደረገው። እሳዳሪው እትዬ ለራሷ የሚበላ የሌላት ነገረኛ አሮጊት ናት። ቤት ውስጥ አስራ በረሃብ ታንገላታዋለች። ተስፋ ያደረገው አልሆነምና። ከሴትየዋ ቤት ጠፋ። ከዛ አንድ ሀብታም ቤት ገባ። የተደላደለ ኑሮ መኖር ጀመረ። ህይወቱ በፍጥነት ተቀያየረ። በቃ ስራው እንደ ዘመናዊ ድመቶች ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ፊልም ማየት ነው። ገላው ይታጠብለታል። ፀጉሩ ይበጠርለታል። ሌላም ሌላም...

በዚህ መንደላቀቅ ላይ ሳለ የቀድሞ አሳዳሪው እትዬ አዘነጋሽ እርሱ መኖር የጀመረበት ቤት ድንገት ጥየቃ ትመጣና ታየዋለች። እትዬ አዘነጋሽ ቀደም ብላ ጆሮው ላይ ምልክት አድርጋበት ስለነበር በፍጥነት ለየችው። ድመቱ የኔ ነው ብላ አንባጓሮ ፈጠረች። ከቤቱ ባለቤቶች ጋ ተጯጩሀ ወደ ቤቷ ይዛው ሄደች። ያ ድመት ወደነበረበት የድህነት ህይወትና ጥቀርሻ ወደሞላው ቤት ተመለሰ።

"አምላኬ እንዲህ አይነት ህይወት እንድኖር እንዴት ትፈርድብኛለህ ?" ብሎ ተስፋ ያደረገው አምላኩን ወቀሰ። የዚህች ሴትዮ ድመት መሆን አልፈልግም ። ድመት ከምሆን ውሻ ብሆን ይሻለኛል። በቃ ውሻ አድርገኝ ብሎ አምላኩን እንደገና ተማፀነው። አምላኩም አላሳፈረውም። ያልከው ይሁን ብሎ ውሻ አደረገው። እንደገና በፈተና የተሞላውን የውሻነት ህይወቱን መግፋት ጀመረ። ታሪኩ እንዲህ እንዲህ እያለ ይቀጥላል ...

ፍጡር መሆን እራሱ ፈተና አይደል? አንድ ነገር ከመሆን ወደሌላ። እንደገና ከውሻነት ህይወቱም ቀይረኝ ብሎ አምላኩን ይማፀናል። መቅበዝበዝ... የህልውና መስመር ላይ ከወዲያ ወዲህ መቅበዝበዝ... ግን የድርሰቱ አስኳል ያለው እዚህ መቅበዝበዝ ውስጥ ነው። የፖለቲካ ሽሙጡ እንዳለ ሆኖ ፣ ፍልስፍናዊ ጥያቄ እንድታነሱም ይጋብዛችኋል። ኧረ በጣምም ያስቃችኋል (...) ብትወዱ ፈልጋችሁ አንብቡት።

@yebirhan_fiker
@yebirhan_fiker
222 views16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 19:22:23
178 views16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 15:03:04
የዘመኔ በረከቶች

(አልታየህ ኪዳኔ)

* አዳምን አነብበዋለሁ። ለተውህቦው ፣ ለቋንቋው ጉልበትና ርቅቀት ፣ ረቂቅ ስሜቶችን የሚገልፅበት መንገድ ይገርመኛል። ኢትዮጰያዊ ፍልስፍናን ከእንጀራ እየቀዳ ያለው አዳም የተለየ ከያኒ ነው።

* ሌሊሳን አነብበዋለሁ። ለሃሳቡ ጥልቀት። ነገሮችን የሚያይበት መንገድ ግሩም ነው። አጫጭር ታሪኮቹና ፍልስፍናዊ ወጎቹ የሚጠገቡ አይደሉም። ጥበብ ላይ ያለው መብሰልሰል ደግሞ የተለየ ነው።

* አለማየሁ ገላጋይን አነብበዋለሁ። ለማህበረሰብ ያለውን ተቆርቋሪነት ይገርመኛል። ቁጣው ያስቆጣኛል። ቁርፊያው ያስኮርፈኛል። አንደበቱ ይበረታብኛል። ድንቅ ብዕረኛና አንደበተርቱዕ ነው።

* በእውቀቱን አነብበዋለሁ። ለታሪክ አዋቂነቱ። ማህበራዊ ሂሶችን በቀልድ አዋዝቶ የሚያቀርብበት መንገድ ይማርከኛል። ግጥሞቹን ሳነብብ ደግሞ ቃላትን በማዘዝ አቅሙ እደነቃለሁ።

* እንዳለንጌታን አነብበዋለሁ። አጫጭር ታሪኮች መፃፍ ላይ የተለየ አቅምና ጉልበት ያለው ይመስለኛል። ያነበብኳቸው የእንዳለ አጫጭር ታሪኮች ምርጥ አጫጭር ታሪኮች ተርታ የማሰልፈው ነው።

* ዘነበን አነብበዋለሁ። Disciplined የሆነ የስነፅሁፍ ማንነቱ ይማርከኛል። የሚፅፋቸው መፅሀፎች የብዙ ጥረትና ድካም ውጤቶች ናቸው። ስነፅሁፋዊ ኮስታራነቱን አደንቃለሁ።

@yebirhan_fiker
@yebirhan_fiker
200 views12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 19:46:44 «ሁላችንም ትርፍ ስራዎች አሉን፡፡ ሞያ የምንላቸው፡፡ ገቢ የምናገኝባቸው። የምንኮራባቸው፡፡ ግን ዋና ስራዎቻችን አይደሉም፡፡ ዋናው ስራችን ታርጋ መለጠፍ ነው፡፡ ብዙ ታርጋዎች አሉን፡፡ ግን እነሱም አንዳንዴ ያልቁብናል» (ገፅ 107)

የዚህችን አጭር ታሪክ አንድምታ የዘመናችንን ታርጋ የመለጠፍና የመፈረጅ ደዌ ላይ የተሰነዘረ በትር እንደሆነ ይሰማኛል።

ከዚህ ጉዳይ ሳንርቅ ሌላ ታሪክ እናንሳ... የ "መኝታ ቤት show"... ይህቺ አጭር ታሪክ ሌላውን ትተን ከአርእስቱ ብንጀምር በቋንቋው ጉራማይሌነት ማለትም መኝታ ቤት እና Show የሚለውን አዳብሎ ባቀረበልንን አርእስት ተቃርኖን እንመለከታለን። እንደገና ተቃርኖውን በሾው አቅራቢዋ ስምና አቀራረብ ውስጥ እናያለን።

«እንደምን ከርማችኋል ክቡራትና ክቡራን የፕሮግራማችን ተከታታዮች … ይሄ ዘወትር ከዚህ የኮንዶሚኒየም እስቱዲዮ የማስተላልፍላችሁ “መኝታ ቤት Show” የተባለው ተወዳጅ ፕሮግራም ነው። ፕሮግራሙን ይዤላችሁ የምቀርበው ሚጣ አስጨናቂ ነኝ» (ገፅ 75)

ይህቺ አጭር ታሪክ በዚህ ጊዜ ሚዲያ ላይ ለምናያቸው አንዳንድ ዝግጅቶች ድብን ያለች ሽሙጥና ስላቅ መሆኗ ነው። ሌሊሳ የፈጠረው አሳቻ መቼት ተዝናኖትን የሚሰጥ ሆኖ ሳለ በመዝናናታችን ውስጥ ልናስተውላቸው የሚገቡን ጉዳዮች አሉ።

ስለ መቼት አመራረጥ ካነሳሁ አይቀር ሌሊሳ አንድ የሚለይበት ነገር ገፀባህርይ አሳሳል እና መቼት አመራረጥ ይመስለኛል። በጣም የተለየ መንገድ ነው ያለው። ለምሳሌ እስቲ ሙዚቃ ላይ ያለች አንድ አጭር ታሪክ ውስጥ እግዚአብሄርን ፌስቡክ የሚጠቀም ፣ ፍሬንድ ሪኩዌስት የሚቀበል ፣ እንዲሁም ከመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅስ እየመረጠ ፖስት የሚያደርግ አድርጎ ያቀርበዋል። ሲያሻው የጀዝቢያ ሃገር ብሎ ጀዝቦች ስለሚኖሩበት ቦታና ጊዜ ይነግረናል። ታዲያ ይሄ ተራ ማፈንገጥ አይደለም። ሪያሊቲውን አይቶ ገፀባህርይዎችንና መቼቱን portray የሚያደርግበት የራሱ መንገድ ነው። ሊሸኘን ባሰበው የሃሳብ ሃዲድ ላይ የሚጠቀመው አሳቻ መንገድ ነው (...)

* ነገረ ደራሲ

ይመስላል ዘላለም ውስጥ በተደጋጋሚ ተስለው ያገኘኋቸው ገፀባህርይዎች ደራሲዎች ናቸው። ሌሊሳ በዚህ ስራው ብቻ ሳይሆን በሌሎች ስራዎችም ደራሲ ገፀባህሪዎችን ስሎ ተመልክቻለሁ። በእኔ ንባብ በእርሱ ልክ ደራሲዎችን በተደጋጋሚ ገፀባህርይ አድርጎ የሳለ ደራሲ አልገጠመኝም።

በዚህ መፅሀፍ ውስጥ እንደ እያሪኮ የሚለው አጭር ታሪክ ከጥበብ አድባር ጋር እልህ የተጋባ ደራሲ አለ። ምናልባት ይህቺ የጥበብ አድባር አያ ሙሌ አስዬ ጨብራሪት የሚላት ትሆናለች። አልያም ደሞ በግሪክ አፈታሪክ Muse የምትባለዋ ልትሆንም ትችላለች። ደራሲው ከአድባሪቷ ትግል ይዟል።

«አድባሪቷ መጥታ ከእኔ ጋር ተቀምጣለች፡፡ እንደማላውቃት ያላየሁዋት ብመስልም አይቻታለሁ፡፡ ውበቷን አሰማምራ፣መቶ አምፖሏን አብርታ ነው የመጣችው፡፡ መፅሐፍ፣ ወረቀት እና ውድ እስኪርብቶ ገዝታልኝ መጥታለች እየተቁለጨለጨች አይን አይኔን ታየኛለች፡፡ የለበሰችው ጉርድ ቀሚስ ጭኗን ያሳያል፡፡ በጣም ለመፃፍ የሚያጓጓ ባት ነው» (ገፅ 228)

ደራሲው ተቀይሟታል። መምጣት ባለባት ጊዜ ለምን አልመጣችም ብሎ አኩርፏታል። ነገር ግን ካለሷ መኖር አይችልም። ቢያኮርፋትም በእርሷ ላይ አይጨክንም።

«ልታስተምረኝ የፈለገችው ነገር ገባኝ። ያለ እሷ መኖር አልችልም፡፡ ከሁለታችን ኩርፊያ ጉዳቱ የሚያደላው በእኔ ላይ ነው፡፡ ሊቀድመኝ ከሚያባብልብኝ ሰው እጅ አስጥዬ አቀፍኳት። ብዙም አልተግደረደረችም ተሳመችልኝ» (ገፅ231)

በዚህ ታሪክ ሌሊሳ የነፍሱን ጩኸት እየጮኸ ይሆን ? ምናልባት... እኔን ግን ይህ የሌሊሳ ታሪክ "ስነፅሁፍ ህይወቴ" የሚል አንድ የራሱን ወግ ያስታውሰኛል (...)

* ነገረ ጊዜ እና የመፅሀፉ አርእስት

የመፅሀፉ አርእስት ይመስላል ዘላለም የ 29 ታሪኮች ወወጠሪያ ክር ነው። እራሱን የቻለ የአጭር ታሪክ ውክልናን አልወሰደም። ግን ደግሞ ታሪኮቹን አያያዥ ነው። ነገር ግን እራሱን መወከል ካሻውም እኔና ጠላቴ የሚለውን አጭር ታሪክ መወከል ይችላል ብዬ አስባለሁ።

ሌሊሳ እኔና ጠላቴ በሚለው አጭር ታሪክ ውስጥ ዘላለም የሚመስል ነገርን ለመግለፅ ሰፊ የህይወት ትግልና ውጣውረድን አላነሳም። ከዛ ይልቅ "ቅፅበት ዘላለም ነው" የሚል Metaphor ውስጥ አንዲት ጥይት ተተኩሳ መዳረሻዋ ጋ ለመድረስ (በጥይቱ የሚመታው ነው የሚተርከው) በሚወስድባት ጊዜ አጭር ታሪኩን ይተርክልናል። የ Slow motion ትረካ በሉት ከፈለጋችሁ።

«ቃታው ሲሳብ የሚያወጣው ድምፅ ጆሮዬ ከመድረሱ አስቀድሞ ፣ ጥይት ባሩድ ሞቆት በረጅሙ አፈሙዝ ገጉዞ... ተጉዞ... ተጉዞ ማጅራቴ ላይ ከመድረሱ አስቀድሞ የማጅራቴን ቆዳ ፣ ስጋዬን በጥይቱ ቅርፅ እየበሳ ፣ አልፎ አጥንቴን ታኮ ፣ ደምስር አፈንድቶ ፣ ትንፋሼና ጩኸቴ ተደባልቆ የሚወጣበትን ቱቦ አቋርጦ... » (ገፅ 132)

ትረካ በቅፅበት ውስጥ ... ቅፅበት ውስጥ ትረካ... ኋላ ላይ የታሪኩ መጨረሻ ሊያስገርመንም ላያስገርመንም ይችል ይሆናል (...)

የጨፈገገው የህይወት ገፅታ ቆይታው ዘላለም ይመስላል፣ ተድላችን፣ ሀዘናችን ፣ ደስታችን ፣ ለቅሶአችን፣ መራሩ የህይወት ትግልም ዘላለም ይመስላል። ጣፋጯን ነፃነት ዘላለም የምናጣጥማት ይመስላል... በአጠቃላይ መንታ የሆነው (Dualistic) የህይወት ገፅታ ዘላለም ይመስላል። በአጫጭር ታሪኮቹ ውስጥ ለርእሰ ጉዳይ ተመርጠው ያስተከዙ ፣ ያስቆዘሙ ፣ ያስደሰቱ ሃሳቦችም ዘላለም ይመስላሉ። ህላዌም እራሱ ዘላለም ይመስላል። ልክ ገብረክርስቶስ ደስታ እንዳለው ነው (...)

አድማስ አልፎ አድማስ
ምጥቀት አልፎ ምጥቀት፥
ጠፈር አልፎ ጠፈር
ይመስላል ዘላለም ሰው ባ'ካል የሚኖር
(ገ/ክርስቶስ. ደስታ ከሞተች ቆይቷል)

ሁሉም... ሁሉም ነገር ... ይመስላል ዘላለም

በመጨረሻም ሌሊሳን በቀጣይ በቅርፅና ይዘት በበለፀገ ረዥም ልቦለድ ባየው ምኞቴ ነው።

አዲዮስ !!

@yebirhan_fiker
@yebirhan_fiker
216 views16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ