Get Mystery Box with random crypto!

እንቁ በእርያ እስቲ እንበልና! ከእለታት አንድ ቀን አንድ ሰውዬ በጣም ውድ እንቁ በእጁ ነበር፡፡ | የቤተሰብ መድረክ @ Yebeteseb Kitir Adash

እንቁ በእርያ
እስቲ እንበልና! ከእለታት አንድ ቀን አንድ ሰውዬ በጣም ውድ እንቁ በእጁ ነበር፡፡ ነገር ግን ስለእንቁ ዋጋ ምንም የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ስለዚህ እንደ ተራ ድንጋይ በጋጣ ውስጥ አስቀመጠው፡፡ በእርግጥ እንቁው ገና ስላልጸዳ እና ስላልተጣራ ከተራ ድንጋይ የሚለይ አይመስልም፡፡ ግን እኮ እንቁው ግን አሁንም እንቁ ነው፡፡ ሰውየው አልገባውም እንጂ ኑሮውን የሚለውጥ ነገር በጋጣ በእርያ መካከል ተቀምጦለታል፡፡ ለምን? አላወቀማ፡፡ ለምን?ለማጣራት አልሞከረማ፡፡
እኛም እንደዚህ ሞኝ ሰውዬ ግለሰባዊ ፣ ትውልዳዊ ፣ ማኅበሰባዊ እና ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው እንቁዎች ማለትም ጋብቻ ፣ ወላጅነት እና ቤተሰብ እንዲሁ በአምላክ ደግነት ተችረውናል፡፡ ነገር ግን በአግባቡ ፣ በእውቀት እና በጥንቃቄ ስለማንይዛቸው እንኳንስ ለሌላው ልንተርፍ ለራሳችንም ሳይጠቅሙን ይቀራሉ፡፡ እስቲ ዛሬ ቆም ብለን እነዚህን ውድ ስጦታዎች እንዴት እንደያዝናቸው እንመርምር!
#ጋብቻ-ማኅበረሰብ
#ወላጅነት-ትውልድ
#ቤተሰብ-ሀገር