Get Mystery Box with random crypto!

የቤተሰብ መድረክ @ Yebeteseb Kitir Adash

የቴሌግራም ቻናል አርማ yebetesebkitiradash — የቤተሰብ መድረክ @ Yebeteseb Kitir Adash
የቴሌግራም ቻናል አርማ yebetesebkitiradash — የቤተሰብ መድረክ @ Yebeteseb Kitir Adash
የሰርጥ አድራሻ: @yebetesebkitiradash
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 197
የሰርጥ መግለጫ

a channel created to save, sustain and support family.

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-28 20:49:43 https://fb.watch/eyxeD9vlYX/
የቤተሰብ ቅጥር አዳሽ @ahadu Radio
33 views17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 07:50:12
የጋብቻ ህመም ደግሞ የሚጀምረው ከጋብቻ የተዛባ እና ጎጂ ትርጓሜዎች ወይም እሳቤዎች ነው፡፡ የመዛባቱ እና የጎጂነቱ መለኪያዎች ባህል፣ወግ እና ሃይማኖት ብቻ ሳይሆኑ የተቋሙ ጤናማነት እና የእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ሁለንተናዊ ጤናማነት ነው፡፡ ለተለያየ ክርክር ከመጋበዛችን በፊት ቆም ብለን ማሰቀደም ያለብን ይህ ትርጓሜ ወይም እሳቤ ለባሌ ይጠቅማል ወይ? ለሚስቴ ይጠቅማል ወይ? ለልጀቼ ይጠቅማል ወይ? ለሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ መስጠትን ነው፡፡ እስከዛሬስ የተከተልናቸው ትርጓሜዎች ወይም እሳቤዎች ምን ያህል አዋጥተውናል? ትርፋቸውስ ምን ምን ነበር? ኪሳራቸውስ?
134 views04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 16:47:15 #ቤተሰብ የሀገር መሰረት ነው፡፡ በብዙ ፈተና ውስጥ ቢያልፍም ግን ቤተሰብ ዛሬም ጸንቶ የቆመ ግኑኝነት ነው፡፡ ያለ ቤተሰብ ወደዚህ ምድር የመጣ ፣ ቤተሰብ የሌለው እና በቤተሰብ ህይወት ውስጥ የማያልፍ ሰው የለም፡፡
ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ሰዎች በእድል ውጤታማ የሚሆኑበት ግንኙነት እንደሆነ ስለሚታሰብ ብዙዎች ተፈትነው የሚወድቁበት ግኑኝነት ነው፡፡ የዚህም ግልጥ ማሳያ የዘመናችን ፣ የትውልዳችን እና የሀገራችን ሞራላዊ ልሽቀት ፣ ግንኙነታዊ ድህነት እና ማኅበራዊ ጉስቁልና አንደኛው ምክንያት የቤተሰብ ግንኙነት ውድቀት መሆኑ የሚያሻማ ጉዳይ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ቤተሰብ የትውልድ የመጀመሪያ እና ወሳኝ ትምህርት ቤት ነውና፡፡ ትውልድ አብዛኛውን እውቀት እና ልምድ የሚቀስመው ሳይወድ በግዱ በውልደትም ሆነ በሌላ ምክንያት ካደገበት ቤተሰብ ነው፡፡ ስለዚህ የቤተሰብ ጉዳይ በአጽንኦት ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
@የቤተሰብ ቅጥር አዳሽ ጤናማ ቤተሰብ ጤናማ ሀገር!
122 views13:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 21:50:41 https://fb.me/e/1Szb4lBei
174 views18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-11 17:11:26 "A man and his wife went to the zoo. They found a Monkey who was passionately playing with his female. His wife said to him, "What a romantic animal."

Then, they found a Lion and his Lioness separated from each other; the silent Lion sat alone in his corner as if the Lioness doesn't exist. His wife said to him, "What a sad scene without love."

Her husband then said to her, “Throw that stone at the Lioness and watch.” When she threw the stone at the Lioness, the Lion roar to defend his Lioness, then she was asked to repeat it with the Monkey, the Monkey then jumped up and climbed the tree and abandoned his female to save his own skin.

Her husband then told her, “Do not be deceived by what you see as romance in outward show, often times, it is a deceptive appearance just to hide an empty heart; there are others on the contrary who are relaxed, but their hearts are full of sincere love."

Presently, we have so many in the monkey shadow, and few Lion nowadays."
Source: Oritsegbubemi Adrian Edema
227 views14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-16 05:36:15 ከባለቤቴ ጋር በትንሽ ነገር ላይ ተከራከርን። አለመግባባቱ እየተካረረ ሲሄድ “አንቺ እዚህ ቤት ውስጥ ከኔ ጋር ኖረሽም ሆነ ሳትኖሪ ምንም የሚፈጠር ነገር የለም። አንዲት ሰራተኛ ባመጣ አንቺ ከምትሰሪው በበለጠ አሳምራ ሁሉንም ነገር መስራት ትችላለች” አልኳት። እንባ ባቀረሩ አይኖችዋ አየት አድርጋኝ ወደ ሳሎን ቤት አመራች። እኔም ወደ መኝታ ክፍሌ አምርቼ ተኛሁ። በመነገው ባለቤቴ ሞታ ተገኘች የቀብር ስነስርአቱ ከተፈጸመ በኋላ ከሚያስተዛዝኑኝ ሰዎች ጋር ሆነን ወደ ቤት ተመለስን። ለተወሰኑ ቀናት ሰዎች ከጎኔ ስላልጠፉ ምንም አልመሰለኝም ነበር። ከቀን ቀን የሚያስተዛዝነኝ ሰው እየተመናመነ ሲመጣ ብቸኝነት ተሰማኝ፡ ቤቱ የሚውጠኝ መሰለኝ። እንደ ምንም ብዬ አልጋዬ ላይ ጋደም አልኩ። ባለቤቴ ትተኛበት የነበረውን
ቦታ ባዶ ሆኖ ሳገኘው ለመጀመሪያ ጊዜ የሀዘን ስሜት ተሰማኝ።

ከእንቅልፌ ስነቃ የስራ ሰአት ረፍዷል። ለምን እንዳልቀሰቀሰችኝ ልቆጣት ዞር ስል ለካ
ከእንግዲህ ላትመለስ ጥላኝ ሄዳለች። ከተጋባን ጀምሮ ቁርስ ደርሷል እንዳይረፍድብህ እያለች ለስራ
የምትቀሰቅሰኝ እሷ ነበረች። ቁርስ ሳልበላ ወደ ስራ ቦታዬ አመራሁ። ቀኑ በዝግታ እያለፈ ቢሆንም የሆነ ነገር ቅር እንዳለኝ ይታወቀኛል። ምን ይሆን? ስል አሰብኩ። የባለቤቴ የስልክ ጥሪ ነው።
ሁሌም ስራዬ ላይ ሆኜ ትደውልልኝ ነበር።
“ውዴ እንዴት እንደናፈከኝ ልነግርህ አልችልም ደግሞ እንዳትቆይ በጊዜ እንድትገባ! ” ትለኛለች እንዲህ ስትለኝ
ልትቆጣጠረኝ ፈልጋ እየመሰለኝ እናደድባት ነበር። ዛሬ ግን ድምጿ ናፈቀኝ። ሰአቱ ደርሶ ወደ ቤቴ ተመለስኩ። ያኔ በር ላይ ቆማ በፈገግታ ትቀበለኝ ነበር። በሰላም
ነው እንዲህ ያመሸኸው? እያለች በፍቅር አይን አይኔን ታየው ነበር። ዛሬ ግን ያ ነገር የለም።
ብቸኝነቱና ጭለማው ያስፈራሉ። ኦ አምላኬ!!! ለካ እስከዛሬ በዚህ በሚያስፈራ በዝምታ የተዋጠ ቤት ውስጥ ብቻዋን ሆና ነበር የምትጠብቀኝ። የኔን ፍላጎት እንጂ የሷን አንድም ቀን ከግምት ውስጥ አስገብቼ አላውቅም። አሳዘነችኝ። ያኔ ነው
ማሰብ የነበረብህ እንጂ ጊዜው ካለፈ በኋላ ማዘን ምን ይጠቅማል ? ስል ራሴን ወቀስኩ። አምላኬ በድያታለሁ ይቅር በለኝ! በዚህ ሁኔታ ላይ እያለሁ ክፉኛ ታመምኩ።
ከአጠገቤ ሆና የምታበረታታኝ፡ በእጆችዋ
እያሻሸች ፍቅርን የምትለግሰኝ፣ የምታጽናናኝ፣ የምታስታምመኝ እሷ ነበረች። ዛሬ ግን የለችም! እንዴት ይከብዳል! ይህችን መልካም ሴት በከፍተኛ ሁኔታ ስበድላት መኖሬ ከነከነኝ፡ እራሴን ጠላሁ፡ ስቅስቅ ብዬ እያለቀስኩ እያለ ድንገት "የኔ ውድ ረፍዷል ተነስ" የሚል ድምጽ ከእንቅልፌ አነቃኝ። ለካስ ይህ ሁሉ ጉድ
የሚታየኝ በህልሜ ነበር።

በድንጋጤ ተውጬ አጠገቤ ሆና በፍቅር አይን አይኔን የምታየኝን ባለቤቴን እቅፍ አደረግኳት። እግዚአብሔር ይመስገን! ውድዋ ባለቤቴ በሕይወት አለችልኝ። ከዚህ ቀደም ለበደልኳት ሁሉ ይቅርታ ታደርግልኝ ዘንድ ተማጸንኳት። ከእንግዲህ ላላስከፋት ለራሴ ቃል ገባሁ።
.
ነገሮች ካለፉ በኋላ ከመጸጸት አሁኑኑ ከአንተ
የሚጠበቀውን ነገር ለማድረግ ጥረት አድርግ። የሰው ልጅ በተፈጥሮው ምሉእ አይደለም። የተወሰኑ ድክመቶች ይኖሩበታል። ያንን ድክመቱን እንደማጥቂያ መሳሪያ እየተጠቀምክ ይበልጥ አታቁስለው። በተለይ የሕይወት አጋርህ በሆነችው ባለቤትህ ላይ ልቧን የሚሰብሩ ቃላትን ከመጠቀም ተቆጠብ።
239 views02:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-10 23:06:17
እንቁ በእርያ
እስቲ እንበልና! ከእለታት አንድ ቀን አንድ ሰውዬ በጣም ውድ እንቁ በእጁ ነበር፡፡ ነገር ግን ስለእንቁ ዋጋ ምንም የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ስለዚህ እንደ ተራ ድንጋይ በጋጣ ውስጥ አስቀመጠው፡፡ በእርግጥ እንቁው ገና ስላልጸዳ እና ስላልተጣራ ከተራ ድንጋይ የሚለይ አይመስልም፡፡ ግን እኮ እንቁው ግን አሁንም እንቁ ነው፡፡ ሰውየው አልገባውም እንጂ ኑሮውን የሚለውጥ ነገር በጋጣ በእርያ መካከል ተቀምጦለታል፡፡ ለምን? አላወቀማ፡፡ ለምን?ለማጣራት አልሞከረማ፡፡
እኛም እንደዚህ ሞኝ ሰውዬ ግለሰባዊ ፣ ትውልዳዊ ፣ ማኅበሰባዊ እና ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው እንቁዎች ማለትም ጋብቻ ፣ ወላጅነት እና ቤተሰብ እንዲሁ በአምላክ ደግነት ተችረውናል፡፡ ነገር ግን በአግባቡ ፣ በእውቀት እና በጥንቃቄ ስለማንይዛቸው እንኳንስ ለሌላው ልንተርፍ ለራሳችንም ሳይጠቅሙን ይቀራሉ፡፡ እስቲ ዛሬ ቆም ብለን እነዚህን ውድ ስጦታዎች እንዴት እንደያዝናቸው እንመርምር!
#ጋብቻ-ማኅበረሰብ
#ወላጅነት-ትውልድ
#ቤተሰብ-ሀገር
214 views20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-09 22:25:06
ትናንትን በነገ
ትዳር የትናንት ፣ የዛሬ እና የነገ ድምር ውጤት ነው፡፡ ትናንተ የትዳር ህይወታችሁን ለማሻሻል ብዙ ነገር ሞክራችሁ ይሆናል፡፡ ዛሬ ላይ ቆማችሁ ስታስቡ የትዳራችሁ ነገ ጠፍቶባችሁ ወይም ደብዝዞባችሁ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን አንድ እውነት አለ፡፡ ትናንትናም አልፏል ግን ብዙ ልትማሩበት ትችላላችሁ ፤ ዛሬ በእጃችሁ ነው ማለትም የትናንትን ስህተታችሁን አሻሽላችሁ ነገን መለወጥ ትችላላችሁ፡፡
ምናልባት ትናንት ስለጋብቻ መማር ወይም የተማራችሁትን ደጋግሞ መከለስ አላስፈላጊ ድግግሞሽ መስሏችሁ ከነበር ዛሬ ለመጀመር ትክክለኛው ጊዜ ነው፡፡ የትናንት ስህተታችሁን በእርግጠኝነት ለመረዳት እውቀት ያስፈልጋል፡፡ እንዲህ አይነት እውቀቶች ከመጽሐፍት ፣ ከጋብቻ አስተማሪዎች ወዘተ ማግኘት ይቻላል፡፡ ዋናው ጉዳይ በአስፈላጊነቱ ላይ መተማመን ነው፡፡ ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድምና!
177 views19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-08 16:55:01
ይሄኛው ግን ያልፍ ይሆን?
ትዳር ጉዞ ነው። በጉዞ ውስጥ ደግሞ ከፍታም ሆነ ዝቅታም አይጠፉም። ትዳር አንዳንዴ ገነት አንዳንዴ ሲኦል ፣ ሲሻው ለምለም ሲሻው ምድረበዳ ይሆናል።
በተለይ ምድረበዳ የሚያልቅ አይመስልም። ሙቀቱ ፣ አዋራው ፣ ነፋሱ ፣ ትውሃኑ … እጅግ አስጨናቂና እልህ አስጨራሽ ጉዞ…። ትዳርም እንዲህ ይሆናል-ምድረበዳ። ሰላም ሲጨፋ ፣ ንግግር ሁሉ ሬት ሬት ሲል ፣ ጫና ሲበዛ ፣ የቤቱ አየር በኩርፍያ ፣ በጠብና በነገር ሲሞላ ይከብዳል። እንደው ፈፅም ነገን አያስመኝም ፤ ቤትን አያስናፍቅም። ይሄ ሲሆን መንቃት ያስፈልጋል። መወቃቀስ መቃብርን የመቆፈር ያህል ነው። ዝምታም እሳቱን ለሚያባብስ ባዕድ አካል ዘዉ ብሎ እንዲገባ መፍቀድ ነው። ይልቁኑ:-
● ኃላፊነት መውሰድና ይቅርታ መጠየቅ፤
● ንግግርንና ድርጊትን መቆጣጠር፤
● እርዳታ መፈለግ
ምድርበዳውን ያሳጥረዋል ፤ ከከፋ ጉዳትም ይከላከላል።
#Family #Marriage #YebetesebKitirAdash
170 views13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-26 17:22:00
188 views14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ