Get Mystery Box with random crypto!

የአባቶቼን ርስት አልሰጥም

የቴሌግራም ቻናል አርማ yeabatochenrest — የአባቶቼን ርስት አልሰጥም
የቴሌግራም ቻናል አርማ yeabatochenrest — የአባቶቼን ርስት አልሰጥም
የሰርጥ አድራሻ: @yeabatochenrest
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 513
የሰርጥ መግለጫ

💒💒ለምጠፋ መብል ሳይሆን ለዘለዓለም ሕይወት ሊሆን ይገባል 💒💒💒የሐ.፫፥፭
እግዚአብሔር አምላካችን የዘለዓለም ሕይወት በምናገኝበት ጽኑ ክርስትና ራሳችንን የምንመረምርበት ንጹሕ ልቡና በምክረ ካህን በምንኖርበት ትህትና እንዲያጸናን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን አስተየት መልዕክት ካለዎት በዚ ቦት ያገኙኝ
👇👇👇👇
@Tadeyedingelbot https://t.me/yeabatoch
👆👆👆👆

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-07 21:59:34 https://youtube.com/shorts/jULgnJPmP-w?feature=share
36 views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 23:08:59
2.ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ
ቅዱስ ዮሐንስ ሀገሩ ገሊላ አውራጃ ሲሆን ከወንድሙ ከቅዱስ ያዕቆብና ከአባቱ ከዘብዴዎስ ጋር ዓሳ ያጠምድ ነበር፡፡ ማር 1÷19-20 ጌታ በመስቀል ላይ ሳለ እመቤታችንን እንዲያገለግላት አደራ የተሰጠው ለዮሐንስ ነው፡፡ ዮሐ 19÷26 ጌታ ይወደው የነበረው ዮሐንስ በፍልስጥኤምና በሌሎች ቦታዎች ክርስትና እንዲስፋፋ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር በመተባበር አስተምሯል፡፡ ሐዋ 4÷1-22 ፣ 8÷14 ከኢየሩሳሌም ወደ ኤፈሶን በመሄድ በታናሿ እስያ የነበሩትን አብያተ ክርስቲያናት በማስተማር ሲያገለግል ቆይቶ በድምጥያኖስ ዘመነ መንግስት ወደ ደሴተ ፍጥሞ ተሰዶ በግዞት ሳለ ራዕየ ዮሐንስን ጽፏል፡፡
83 views20:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 23:08:54
ጥላ

❖ በበርሃ ይሄድ የነበረ ሰው ወደ ኋላው ዞሮ ሲያይ ከእርሱ ሌላ አንድ ጥላ ይመለከታል፤ የዚህም ጥላ ነገር አሳስቦት የማን እንደ ሆነ ያመለክተው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እግዚአብሔርም

"ከኋላህ የተመለከትከው ጥላ የእኔ ነው፤ አንተን እየጠበኩህ እንደሆነ ታውቅ ዘንድ ይህን ምልክት አሳየውህ" አለው፤ ያም ሰው ፈጣሪው ከእርሱ ጋር እንዳለ በመስማቱ እጅግ ደስ እያለው ጉዞውን ቀጠለ፤ ጥቂትም እንደተጓዘ ወጣ ገባ የሆነ በጣም አስቸጋሪ መንገድ አጋጠመው፤ ሰውየውም ያን አስቸጋሪ መንገድ እንደ ምንም ብሎ ለመውጣት ታገለ፤ በትግሉ መካከል ግን ወደ ኋላው ዞር ብሎ ቢመለከት እንደ ቀድሞው ሁለት ጥላዎች ሳይሆን አንድ ጥላ ብቻ ቀርቶ ታየው፤ ከዚያ ፈታኝ መንገድ እንደ ምንም ብሎ ከወጣ በኋላም፣ በታላቅ ኃዘን ሆኖ እየተበሳጨ ፈጣሪውን እንዲህ ሲል ጠየቀው

"ምንም ችግር ባልገጠመኝ በሰላሙ ጊዜ "ከአንተ ጋር ነኝ ስትል ጥላህን አሳየኸኝ፣ የአንተ እርዳታ በሚያስፈልገኝ ጊዜ ግን ራስህን ሰወርክብኝ፤ ይከተለኝ የነበረውን ጥላም ዘወር ብዬ ባየው አጣኹት፤ ለምን ተውከኝ?"

❖ እግዚአብሔርም "በመከራህ ጊዜ ጥላዬን ያጣኸው ትቼህ እኮ አይደለም፤ ተሸክሜህ ነው!" ብሎ መለሰለት፤ ክፉውን ዘመን በክንፈ ረድኤቱ ተሸክሞ የሚያሻግረን እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ አይተወንም፤ አይንቀንም፤ እኛም ከእርሱ ውጭ ተስፋ የምናደርገው የለንም።

ምንጭ
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
58 views20:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 23:08:47 "ቅዱስ[በጎ] የሆኑ ሰዎች በኃጢአተኞች እጅ ተላልፈው ይሰጣሉ፤

ይህም የሚሆነው ክፉዎች ክፉ ችሎታ ስላላቸው ሳይሆን፣

በጎዎች ጽናታቸው ይፈተሽ ዘንድ ነው"

ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ
46 views20:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 23:08:39 ​​#ዝክረ_መነኮሳት
#ተሳሕያን_መነኮሳት

ቅዱስ ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊ
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

በዚህች ቀን ሕይወቱ እጅግ ታላቅ የሆነ ሙሴ ጸሊም በሰማዕትነት አረፈ። ይህ ቅዱስ መንግስተ ሰማያትን በኃይል ነው የወሰደው። ልክ ጌታችን በወንጌል እንዳለ:-

"...መንግስተ ሰማይ ትገፋለች ግፈኞችም ይናጠቋታል(በኃይል ይወስዷታል")__ማቴ 11:12

ቅዱስ ሙሴ በቀደመው ሕይወቱ ፀሐይን ለሚያመልኩ ሰዎች ባሪያ ነበር። አብዝቶ መብላት እና መጠጣት የሚወድ ኃያል ሰው ነበር። በመግደል፣ በመዝረፍ እና በክፋት ስራ ሁሉ ውስጥ ነበር፤ ማንም ሰው በፊቱ ሊቆምም ሆነ ሊቃወመው አይችልም ነበር። ብዙ ጊዜም አይኑን ወደ ፀሐይ አንስቶ "ኦ ፀሐይ አንተ አምላክ ከሆንክ አሳውቀኝ" ይል ነበር። ከዚያም በኋላ "የማላውቅህ ሆይ ራስህን ግለጥልኝ" ይል ነበር።

ከዕለታት አንድ ቀን የሆነ ሰው በገዳም ያሉ አባቶች እውነተኛውን አምላክ ያውቃሉ፣ ወደነርሱም ሂድ ይነግሩኃል ሲል ሰማ። ፈጥኖም ተነሳ ሰይፉን ታጠቀ ወደ አስቄጥስ በረሃ ተጓዘ። አባ ኤስድሮስንም አገኛቸው፣ ባዩትም ጊዜ ስለ አመጣጡ ፈርተው ነበር። ቅዱስ ሙሴ ግን መነኮሳቱ ስለ እውነተኛው አምላክ ለማወቅ እንዲያስተምሩት እንደመጣ ነገሮ አረጋጋቸው። ቅዱስ ኤስድሮስ ወደ አባ መቃሪዮስ ታላቁ ወሰደው፤ እርሱም ሃይማኖት አስተምሮ አጠመቀው። ካመነኮሰው በኃላ በገዳም መኖርን አስተማረው።

ቅዱስ ሙሴ በብዙ አምልኮ መትጋት ጀመረ፣ ከብዙዎቹ ቅዱሳን የበለጠ ጽኑ ተጋድሎን ተጋደለ። ነገር ግን ዲያብሎስ በቀደሙት ልማዶቹ አብዝቶ በመብላት፥ በመጠጥ እና ዝሙት ክፉኛ ተዋጋው። ሁሉንም በተጋድሎው የመጣበትን ነገር ለቅዱስ ኤስድሮስ ይነግረው ነበር። እርሱም ያበረታታዋል፥ የጠላትን ደባ እንዴት እንደሚያሸንፍ ይነግረዋል።

የገዳሙ አረጋውያን በተኙ ጊዜ እንስራቸውን ወስዶ ከገዳሙ ረዥም ርቀት ተጉዞ ውሃ ይቀዳላቸው ነበር። ከብዙ አመታት መንፈሳዊ ትግል በኃላ ሰይጣን ቀንቶበት እግሩን አሳመመው በዚህም የተነሳ አልጋ ቁራኛ አደረገው። ይህም ከሰይጣን መሆኑን ሲያውቅ አምልኮቱን እና ትሕርምቱን ጨመረ፥ በዚህም ሰውነቱ እንደ ተቃጠለ እንጨት ሆነ።

እግዚአብሔር ትዕግስቱን ተመልክቶ ሕመሙን እና መከራውን አራቀለት። የኢየሱስ ክርስቶስ በረከትም በርሱ ላይ ሆነ። ከተወሰነ ጊዜ በኃላ የ500 ወንድሞች አባት እና መንፈሳዊ መሪ ሆነ። እነርሱም ካህን እንዲሆን መርጠውት ነበር። ክህነት ሊቀበል ወደ ፓትርያርኩ ሲመጣ ትዕግስቱን ለመፈተን አረጋውያኑን " ይህን ጥቁር ማነው እዚህ ያመጣው? ከዚህ አውጡት" አሏቸው። ሙሴም ታዞ ወጣ ለራሱም እንዲህ አለ "አንተ ጥቁር ያደረጉልህ ነገር መልካም ነው(የውስጤን ጥቁረት ቢያዩስ ኖሮ እያለ በትህትና)"። ፓትርያርኩም መልሰው ጠርተውት ካህን አድርገው ሾሙት፥ እንዲህም አሉት "ሙሴ አሁን ውስጥህም ውጭህም ነጭ ሆነ"።

ከዕለታት በአንዱ ቀን ከአረጋውያን ጋር ወደ አባ መቃርዮስ ታላቁ ሄደ። እርሱም "ከእናንተ መሃል የሰማዕትነት አክሊል የሚቀበል እንዳለ አያለሁ" አላቸው። ቅዱስ ሙሴም መልሶ "ምናልባት እኔ እሆንን? 'ሰይፍን የሚያነሱ በሰይፍ ይጠፋሉ' ማቴ 26:52 ተብሎ ተጽፏልና። ወደ ገዳሙ ከተመለሱ በኃላ ብዙም ሳይቆይ በርበሮች ገዳሙን አጠቁት። ወንድሞችን "መሸሽ የሚፈልግ ይሽሽ" አላቸው። ወንድሞችም "አንተስ አባታችን ለምን አትሸሽም?" አሉት። እርሱም ይህን ጊዜ(ሰማዕትነቱን) ለረዥም ጊዜያት ሲጠብቀው እንደነበረ ነገራቸው።

በርበሮች ወደ ገዳሙ ገብተው ከሌሎች ሰባት ወንድሞች ጋር ገደሉት። ከወንድሞች አንዱ ተደብቆ ነበር፥ የጌታ መልአክ አክሊል ይዞ እየጠበቀው መሆኑን ሲመለከት ከተደበቀበት ወጥቶ ሰማዕትነትን ተቀበለ።

ተወዳጆች ሆይ በንስሐ ሀይል ላይ ተመሰጡ እንዲሁም ምን እንዳደረገ ተመልከቱ። አንድ አረማዊ፥ ነፍሰ ገዳይ፥ ዘማዊ እና ዘራፊ ባሪያ የነበረን ሰው ወደ ታላቅ አባት፣ መምህር፣ አጽናኝ እና ለመነኮሳት ስርዓትን የጻፈ ካህን እንደለወጠው። ስሙም ዘውትር በጸሎታት ሁሉ ይጠራል። ቅዱስ አጽሙ አሁን በወንድማማቾች ማክሲሞስ እና ዶማዲዮስ ገዳም(ኤል-ባራሙስ) ይገኛል።

ጸሎቱ ከኛ ጋር ትሁን፤ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን፤ለዘላለሙ አሜን
58 views20:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 14:41:53 Watch "የሊቀመላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ተአምር ይህ ነው " on YouTube


131 views11:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 06:39:32 የአባቶቼን ርስት አልሰጥም pinned «​​​​ሰኔ 12 #የቅዱስ_ሚካኤል ዓመታዊ በዓል! እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለእናታችን ቅድስት አፎሚያ አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። ሰኔ 12 ቅዱስ ሚካኤል እናታችን ቅድስት አፎሚያን ከጠላት ዲያብሎስ እጅ ያዳነበት ፣ እናታችን ቅድስት አፎሚያ እረፍቷ ነው ።እግዚአብሔር ከቅዱሱ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ፣ ከእናታችን ቅድስት አፎሚያ በረከት ተካፋይ ያድርገን ። በወርኃ ሠኔ መታሰቢያ ከሚደረግላቸው…»
03:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 06:37:10 ​​​​ሰኔ 12 #የቅዱስ_ሚካኤል ዓመታዊ በዓል!

እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለእናታችን ቅድስት አፎሚያ አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። ሰኔ 12 ቅዱስ ሚካኤል እናታችን ቅድስት አፎሚያን ከጠላት ዲያብሎስ እጅ ያዳነበት ፣ እናታችን ቅድስት አፎሚያ እረፍቷ ነው ።እግዚአብሔር ከቅዱሱ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ፣ ከእናታችን ቅድስት አፎሚያ በረከት ተካፋይ ያድርገን ።

በወርኃ ሠኔ መታሰቢያ ከሚደረግላቸው ቅዱሳን መካከል እግዚአብሔርን የሚፈራ የአስተራኒቆስ ሚስት የሆነች የቅድስት አፎምያን ታሪክ በአጭሩ እንዳስሳለን፡፡

ቅድስት አፎምያ በትዳር በነበረችባቸው ዘመናት እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ሴት ነበረች፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ እንደነበር ታሪካቸው ይነግረናል፡፡

ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው፡፡

ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፡፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ ባያት ጊዜ ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ፣ ሌላ ባል አግብታ፣ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት፡፡

ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ፤ እነሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ፤ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡

በሠኔ ፲፪ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ሞከረ፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን፣ ዳዊትን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶችን ታሪክ እየጠቀሰ ወደ ትዳር እንድትገባ ደጋግሞ ወተወታት፡፡

ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና “የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?” በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው፡፡

ለጊዜው “በኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም” ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ፡፡ ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን “ድረስልኝ” እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት፡፡

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሠኔ ፲፪ ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡
https://t.me/yeabatochenrestalsetm
ይህች የታመነች ቅድስት አፎምያ በሰላም እስክታርፍ ጊዜ ድረስ የተጓዘችበትን መንፈሳዊ ጎዳና አስተውለን ይሆን? አስቀድማ ከባሏ ጋር አንድ ሆና በታማኝነት ፈጣሪዋን አገለገለችው፡፡ በኋላም የባሏን ኑዛዜ አክብራ ምንም እንኳን ኃጢአት ባይሆንባትም በሁለተኛ ትዳር ራስዋን ማጠላለፍ አልፈለገችም፡፡ በጎ ሥራ አብልጣ በመሥራት እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ተፋጠነች እንጂ፡፡
https://t.me/yeabatochenrestalsetm
ሰይጣን ልጅ አለመውለዷን ተጠቅሞ ያቀረበላትን የጋብቻ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ “መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ መናፍስት ከእግዚአብሔር እንደሆኑ መርምሩ” ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የታዘዘውን መመሪያ ተጠቅማ ሰይጣንን በተወክሎ እግዚአብሔር ተቃውማ አሸነፈችው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን ርዳታ ያገኘችውና በሰላም ዐርፋ ወዳገለገለችው እግዚአብሔር በክብር የሔደችው በጽናት ተጋድላ ነው፡፡
https://t.me/yeabatochenrestalsetm
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በጸሎቷ ይማረን፤ የቅዱስ ሚካኤል የረድኤቱ ኃይል ሁላችንንም ይጠብቀን፣ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
128 views03:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 23:28:09 በጸሎት ውስጥ በመትጋት ብዛት ወደ እግዚአብሔር መድረስ ትችላላችሁ

❖ እግዚአብሔርን ከወደዳችሁት ትጸልያላችሁ፤ አብዝታችሁ የምትጸልዩ ከሆናችሁ ከቀን ወደ ቀን ለእርሱ ያላችሁ ፍቅር እየጨመረና እየጠለቀ ይሄዳል፤ ይህ ደግሞ የተለመደ ነገር ነው ምክንያቱም አንድ ሰው ከወደዳችሁ ከእርሱ ጋረ መነጋገርን ትወዱታላችሁና ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ጸሎት ነው፤ በመጸለይ እንዴት መጸለይ እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ ለማለት የፈለግሁት ወደ እርሱ ፍቅር በሚመራችሁ መንገድ ከእርሱ ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለባችሁ ትማራላችሁ ለማለት ነው ።

❖ በጸሎት ውስጥ በመትጋት በጸሎታችሁ ውስጥ ወደ ምትናገሩት ወደ እያንዳንዱ ቃል ጥልቀት ልትደርሱ ትችላላችሁ፤ ከዚህ በተጨማሪ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ ወደ እግዚአብሔር እየተጠጋችሁ ትመጣላችሁ ከእርሱ ጋር ለመነጋገርም ትናፍቃላችሁ፤ ስለሆነም ጸሎት እንዴት እግዚአብሔርን መውደድ እንዳለባችሁ ያስተምራችሗል፤ እንዲህ ባለ ጠባይ በጸሎታችሁ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገሩ አንደበታችሁ ከእርሱ ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለባችሁ እየለመደ ይመጣል፤ ይህ ደግሞ አዲስ ቋንቋ መማር የሚፈልግ ሰው ይመስላል፤ ይህ ሰው ይህን ቋንቋ በሚገባ ባያውቅና መጀመርያ ላይ ቢሳሳትም እንኳ ይህን ቋንቋ መናገር አለበት፤ ብዙ ጊዜ በመደጋገም ግን አንደበቱ ቋንቋውን ይለማመደዋል በሚገባ እስከሚጠቀምበት ድረስም ቀላል እየሆነለት ይመጣል ።

❖ በእናንተም ቢሆን እንዲሁ ነው ይበልጥ ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገራችሁ ስትመጡ አንደበታችሁ ይበልጥ ከእርሱ ጋር መነጋገርን እየለመደ ይመጣል፤ ከዚህ በኋላ በፍቅር ስሜት ውስጥ ሆናችሁ ከእርሱ ጋር መነጋገርን ታውቃላችሁ ።

ምንጮ
አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
93 views20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 20:35:49 አንዴ ብቻ ይንኩት አለማትን የፈጠረውን ጌታ
በሕይወት ያመስግኑ ፣ ስትነኩት የሚወስዳችሁ
ቦታ በጣም ይጠቅማቹሀል!

.            ✦              ‍ ‍ ‍ ‍                  ,    

.             .   ゚     .                    .           .            

 ˚                     ゚     .               .      ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ,                * .                    .           ✦           ˚              *                      .  

.             .   ゚     .             .

      ,       .                                                              *         .           .             .                                                               ✦      ,         *          ,    ‍ ‍ ‍ ‍               .            .                                   ˚          ,                              .                 

         

             *          ✦                                .                  .        .        .                .           .            

 ˚                     ゚     .               .
91 views17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ