Get Mystery Box with random crypto!

የሀገረ አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ከነገ ጀምሮ የ2012 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞ | የኢትዮጵያ ልጆች🇪🇹🇪🇹🇪🇹

የሀገረ አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ከነገ ጀምሮ የ2012 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤትን አስመልክቶ የሚያቀርቡትን አቤቱታዎችን ማስተናገድ ይጀምራል።

ኤጀንሲው አቤቱታዎችን የሚያስተናግደው ከነገ መጋቢት 28/2013 ዓ/ም እስከ ሚያዚያ 5 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ ነው።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ከግምት በማስገባት ኤጀንሲው አቤቱታዎችን የሚያስተናግደው በድህረ ገፁ www.neaea.gov.et ላይ መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን ፤ አቤቱታ ያላቸው ተፈታኞች ዘውትር በስራ ሰዓት በድህረገፁ በመግባት 'compliant' የሚለውን በመጫን በሚፈጠረው ቅፅ አቤቱታ ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT