Get Mystery Box with random crypto!

#NEAEA ትላንት የ2012 ዓ/ም ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉ ይታወቃል። የፈተናው | የኢትዮጵያ ልጆች🇪🇹🇪🇹🇪🇹

#NEAEA

ትላንት የ2012 ዓ/ም ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

የፈተናው ውጤት በተመለከተ አንዳንድ ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ቅሬታ እንዳላቸው እየገለፁ ሲሆን ይህንን ቅሬታም የሚመለከተው አካላ ምላሽ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል።

ቅሬታ ማስተናገጃ መድረክም እንዲፈጠር ጥሪ አቅርበዋል። በተለይም በክልል ያሉ ነዋሪዎች።

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና የፈተናዎች ኤጀንሲ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤትን አስመልክቶ ቅሬታ ካላቸው/አቤቱታ ካላቸው ከሰኞ መጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ማቅረብ እንደሚችሉ አሳውቋል።

በኤጀንሲው ዋና መስሪያ ቤት ደጃፍ ላይ የተለጠፈው ማስታወቂያ ግን በክልል ያሉ ነዋሪዎች እንዴት ቅሬታ እንደሚያቀርቡ ያለው ነገር የለም ፤ ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia