Get Mystery Box with random crypto!

ለማስታወስ ብቻ !!

የቴሌግራም ቻናል አርማ ychanut — ለማስታወስ ብቻ !!
የቴሌግራም ቻናል አርማ ychanut — ለማስታወስ ብቻ !!
የሰርጥ አድራሻ: @ychanut
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.52K
የሰርጥ መግለጫ

ጌታዬ ሆይ! ጥፋቴን አምናለሁ ወንጀሌንም
አውቃለሁ፡፡ ጥሩ ነገር ባልሰራ እንኳን ወደ በጎ ነገር
ያመላከተ ሰው ከሚያገኘው አጅር አታሳጣኝ፡፡
ለበጎነት በር ከስር ያለውን ይጫኑ
@ALIFCHARITY123
for any comment @hashimkhedir

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-18 18:21:08 ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የ ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ!
አልሀምዱሊላህ እስከመጨረሻው ያማረ አላህ ያድርግልን።
@ychanut
447 viewsሀሺም (ለማኖር እኖራለሁ!!), 15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 15:50:48 ሰዎች እንዲህ ናቸው!


,
ስንወለድ ይስቃሉ (ይደሰታሉ)
ስንሞት ያለቅሳሉ


ግና
በመሀል ያለው ህይወታችን ይረሳሉ። (ረዋኢዑን ሚነል-ፊክር)
@ychanut
588 viewsሀሺም (ለማኖር እኖራለሁ!!), edited  12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 14:29:03 «የምድራችን ህግ ሰጥቶ መቀበል ነው። ዋጋ ያላቸው ነገሮች ዋጋ ሳይከፈልባችው በጭራሽ ወደኛ አይመጡም።
ስለዚህ አሁን ዋጋ ክፈል በኋላ ተጫወት፤ አሁን ዋጋ ካልከፈልክ ግን እድሜ ልክ ትከፍላለህ!
ስለዚህ ለውጥ ከፈለግክ
፨ ከምቾት ቀጠና ውጣ፦ አለም ላይ ያሉ ምርጥ የሚባሉ ነገሮች ከምቾት ቀጠና ውስጥ የተገኙ አይደሉም።
፨ አዋዋልህን ቀይር፦ የት ነዉ የምትውለው? ከማን ጋር ነው ውሎህ? ማደግን ከሚያሰቡ ትችላለህ በርታ ከሚሉ ነው ወይስ በተቃራኒው?
ተግባር ውስጥ ግባ ፦ ለውጥ ተግባር ይፈልጋል። ስኬት ውቃቤ አይደለም መጥቶ አይሰፍርብህም። አልበርት አንስታይን እንዳለው ተመሳሳይ ነገር እያደረጉ የተለየ ነገር መጠበቅ እብደት ነው። ስለዚህ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ተግባር ያስፈልጋል።

ስለዚህ ዛሬውኑ ጀምር!»


መልካም ውሎ
@ychanut
983 viewsሀሺም (ለማኖር እኖራለሁ!!), 11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 10:30:02 መፍቀሬ– ሙፍቲዎቹ ዲያቆናት
★★★// //★★★

(በዐብዱልጀሊል ሸኽ ዐሊ)

ዲያቆናቱ ብሔራቸው የዛሬው አ§ማራ ባይሆኑኳ ዐም–ሓራ ናቸው። ለዚያ ነው ኦሮሞዎቹን ኤርሚያስ ለገሰን፣ ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴን፣ ፈንታሁን ዋቄን ከጎንደሬ በላይ አ§ማራ ሆነው የምታገኛቸው።

ዛሬ የሚያበሳጩህ ፖለቲከኛ፣ አክቲቪስት፣ ጋዜጠኛ፣ ምሁራን ዲያቆናት ትናንት የኦርቶ—ዐም—ሓራን ሔጅሞኒ ስርዓት ለመመለስ በገዥው ንዑስ ብሔርተኛውም ፓርቲ (ለምሳሌ ኤርሚያስ ለገሰ)፣ በተቃዋሚውም ፓርቲዎች (ለምሳሌ ዲ/ን ሀብታሙ አያሌው፣ እሰክንድር ነጋ ወዘተ)፣ በቤተ ክህነት ፖለቲካም (ለምሳሌ ዘመድኩን በቀለ፣ ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)፣ በጋዜጠኝነት፣ በምሁርነት ወዘተ ከቤተ–ክህነቷና ከደሴቷ የፖለቲካ ማዕከል ስምሪት ተሰጥቷቸው በሁሉም ቦታ የነበሩ ተናበው የሚሰሩ ኤጀንቶች ናቸው።

የአብዛኞቹ ፖለቲካዊ አሰላለፋቸው "ኢትዮጵያዊ" ብሔርተኛ ነው። አሀዳዊ ነው። የተቀሩት pseudo federalist ነው። የኢትዮጵያ ብሔርተኛ ስንል የየትኛዋ ኢትዮጵያ ብሔርተኛ ማለታችን ነው? የደሴቷ፣ የኦርቶ—ዐም—ሓራዋ ኢትዮጵያ ብሔርተኛ ማለታችን ነው።

የኦርቶ—ዐም—ሓራዋ ኢትዮጵያ መገለጫዎች እነኚህ ናቸው።

ሃይማኖቷ ኦርቶዶክስ የሆነ፣ ራሷ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን የሆነች ናት። ዜጎቿ —በክርስትና ሀርነትን የተጎናፀፉ፣ በእግዜር የተመረጡ ናቸው። ስርዓቷ—ሰለሞናዊ የሆነ፣ ህግ አውጪዋ የኢት/ኦ/ቤተ ክርስቲያን፣ ህግ አስፈፃሚዎቿ ከንጉሥ ሰለሞንና ንግስት ሳባ (አዜብ፣ ማክዳ) የተወለዱ፣ በክብረ ነገሥት፣ በፍትሐ ነገሥትና በኢ/ኦ/ቤተ ክህነት ህግ የተዳኘች ነች።

ታሪካዊ(ነባር) ጠላቶቿ:— የኦርቶ—ዐም—ሓራዋ ኢትዮጵያ ብሔርተኝነት ተፃራሪ የሆኑ ኃይሎች። በሃይማኖት እስላሞች፣ በነገድ ኦሮሞዎችና ብሔር ብሔረሰቦች።

ቅድመ ማንነታቸው:— በሴኪዩላር ስም በተለየ ተልዕኮ በተደራጁ ኦርቶ—ሀገራዊ ፓርቲዎች አባልና አመራር በመሆን ፀረ ኦርቶ—ዐም—ሓራ ናቸው ያላቸውን ንዑስ–ብሔርተኞችን (ኢህአዴጋውያንን) ሲታገሉ የነበሩ ናቸው።

በአሃዳዊው የኦርቶ–ዐም–ሓራ ብሔርተኛውና በንዑስ ዘውጋዊው ብሔርተኛ ኃይል መካከል ለባለፉት ሰላሳ ዓመታት በነበረው የሃይል ፉክክርና መነጣጠቅ ትግል ሒደት ድህረ 1997 የማይቀመስ የማይነካ የሆነባቸውን የኢህአዴግ መንግሥት አቅም በቅጡ ባለመረዳት አንዋር መስጅድ ሆኖ ማስጨነቅ የያዘውን እስላም (ታሪካዊ ጠላታቸው) ታክቲካሊ በመደገፍ በእስላሙ ተጋፋጭነት የኢህአዴግን ውድቀት ለማፋጠን ካልኩሌት አድርገው የሙስሊሙ ወዳጅ መስለው ከቀረቡ ኃይሎች መካከል የነበሩ ናቸው።

እነ ዲያቆን ዛሬ:—

ለሰላሳ ዓመታት ኦርቶ—ዐም—ሓራው ሀገራዊ ብሔርተኛ ኃይል የትኛውንም መንገድ ተጠቅሞ ንዑስ ብሔርተኛ ያለውን (የዘውግ ብሄርተኛ) ሥርዓት አጥፍቶ የአባቶቹን ስርዓት ለመመለስ በኢትዮጵያ ስም ሲምል ሲገዘት የነበረው የሀሳዊው ኢትዮጵያዊነት (ዐምሓራዎች "ት§ግሬና ዐ§ማራ") ብሔርተኞች እንቅስቃሴ ለሰላሳ ዓመታት ብዙ ውጣ ውረድ አይቶ፣ ብዙ ሃብትና ትውልድ ሰውቶ ሲጠብቀው ነበረው የድህረ ኢህአዴግ ውድቀት አብዮት ፍሬ ድንገት ባልጠበቀው መልኩ በንዑስ ብሔርተኛው ኃይል በተለይም በኦሮሞ ብሔርተኛውና በፕሮቴስታንቱ ኃይል ጥምረት ሲጠለፍ የታሰበው የተናፈቀው ሁሉ ተስፋው ሁሉ አፈር ዴቼ በላ።

ያኔ በሃሳዊው ኢትዮጵያዊነት ሽፋን ይንቀሳቀስ የነበረው ኢትዮብሔርተኛ ኃይል ሁሉ ቀድሞ በንዑስ ብሔርተኛው (በፌደራሊስቱ ኃይል) ይጠረጠርበት ወደ ነበረው የህዝብ፣ ተቋምና የኢዶሎጂ መሰረቱ ወደ ቤተክህንትና ዐ§ማራ ክልል ጠቅልለው መሸጉ። ተሰደዱ! የዐ§ማራ ብሔርተኝነትም ዋና መጠለያ ሆናቸው።

የህዝብ መሰረት ወደ ሆነው የዐ§ማራ ህዝብ ሲሰደድ በሃሳዊ ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት ስም ለዘለዓለም አገሪቱን ቀይደው የያዙባቸውን ትርክቶች፣ ተቋማት፣ አሰራር፣ ባህሪና ኦ/ቤተ ክርስቲያንን ጭምር ይዘው ወደ ዐማ§ራ ክልል ይዘው በመሰደድ ከዚያ ተስፈንጥረው ለመምጣት መከራውን የሚያየው ኃይል የአ§ማራ ክልል ስቴት ተክለ ቁመና ምቹ ሆኖ ጠበቀው። ቤተክርስቲያን ውስጥ ተሰብስበህ የምትመክረውና አማራ ክልል ፖለቲካ ምህዳር ውስጥ፣ ክልሉ ተቋማት ውስጥ ሆነህ የምትመክረው አንድ እሰኪሆን ድረስ ክልሉ ምቹ ሆኖ ጠበቃቸው።

የእነ ዲያቆን ታሪካዊ ጠላት እስላም ነው። አረብና ቱርክ ነው። ኦሮ—ጴንጤው ኃይል ሌላ ትኩሳት ዘመንኛ ጠላታቸው ነው። ለግራኝ ሺ አመት የተሰላ የጦር ታክቲክ ለኦሮ–ጴንጤው ኃይል አይሰራምና እንደ አጤ ሚናስ መደናገጣቸው አይቀሬ ነው። የእስላምና የአረብ ቱርክ ጭራቅ ተረክ በክልሉ ፍሬ አፍርቶ ከሞጣ እስከጎንደር በምርቱ ተደስተዋል።

ታሪካዊ ጠላታቸውን ለማዳከም ሱልጧኔቶቹ መውደም አለባቸውና ቴዎድሮስን ሆነው ማመዶች ስርዎመንግስት ይኖርህ ዘንድ በፍፁም አይፈቅዱልህም። ከቻሉ እንደ ቴዎድሮስ ሰባት ጊዜ ዘምተው መጅሊስህን ያፈርሱታል። ካልቻሉ ንዋዬ ክርስቶስ ሸኽ ዘከርያን (በሱፊ ስም ዛሬ እየተንቀሳቀሰ ያለውን አረም ኃይል) ልከው ያወድሙሃል! ለዚያ ነው መፍቀሬ— ሙፍቲ ሆነው የተገኙት።

ወዳጄ ታሪካዊ ጠላታቸው ሆነህ ሳለ፣ ተቋም ሳይኖርህ እየዋጥካቸው ተቋም ኖሮህ፣ ተደራጅተህ፣ በተቋም ታግዘህ ምን ልታደርጋቸው እንደምትችል የማያስቡ ቂሎች አይደሉምና እንኳን መፍቀረ ሙፍቲ ሆነው ሙፍቲህም ሆነው ከቻሉ ይመጡልሃል ስራቸውን እየሰሩ ነው። አትገረም

በየቀኑ ተገርመህ ደንግጠህ ትችለዋለህ? የቤት ሥራህን ሥራ

https://t.me/abduljelilshekhalikassa
1.0K viewsሀሺም (ለማኖር እኖራለሁ!!), 07:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 15:53:08 ወገኖቻችን ምን እያደረጉ ነው ያሉት?

ወገኖቻችን የአልሞት ባይ ተጋዳይ መንፈራገጥ ላይ ናቸው። ቡጭሪያቸው ወዲያም ወዲህም ነው። ያገኙትን ይነከሳሉ፣ ያረፈደ ብልጠታቸው እስላሙን የጦስ ዶሮ አድርጎ በሴራ ለማስበላት ብዙ ሞክረው ቀላል በማይባል ደረጃ ተሳክቶላቸዋል።

ይዞ ሟችነት እንዲህ ነው! ያላቸው አማራጭ ሁለት ነው። የገርገራ (የጣዕረ ሞት) ጊዜን ማራዘም (Decreasing at a decreasing rate) ላይ መሰንበት! ከመሞት መሰንበት! አሊያም እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይበቀልን መርህ አድርጎ ይዞ ሟችነት ላይ ምንችክ ማለት!!

ወዳጄ የክርስቲያን አክራሪነት እያስደነገጠህ ከሆነ አይግረምህ ነገሩ “ሀከዛ” ነው!

ግና መፍትሄው ምንድን ነው ካልከኝ አድምጠኝ።

የግሪቫንስ ፖለቲካ የሚባል አለ። የመጥፋት፣ የመረሳት ስጋት ያለባቸው አካሎች ወደ ተረትነት ከመቀየራቸው በፊት ማንኛውንም ነገር ያደርጋሉ። እሪሪሪታው እየየየው ይቀጥላል። ዓላማው መንፈሳዊ ሳይሆን ብሶተኛ፣ የተበዳይነት ስሜትን ያዳበረ በቀለኛ ኃይልን መሰብሰብ ብቻ ነው። ይህ ተወገርኩ ተቀጠቀጥኩ፣ ነደድኩ እየየው ለሚዲያ ማሳያ ይፈልጋል። በደሉ እውነተኛ ከሆነ እውነተኛ ታጋዮችን ያፈራል። ቤተ-ክርስቲያኗ ብትነጥፍ እንኳን እየተበደለች ከሆነ አላህ ከውስጧ በደልን የሚገፈትሩ ወንዶችን፣ ትውልዶችን ይፈጥራል። አላህ ሃይማኖትህን ሳይሆን መበደልህንና ጥረትህን ነው የሚመለከተው።

ግና እሪታውና ኡኡኡታው ማሳያ አልባ፣ ሀቅ የከዳው የሴራ ጩኸት ከሆነ ጊዜ ያከስመዋል። ግና በራሱ አቅም ማንሰራራት የተሳነው ያገኘው ጋር በመጋጨት፣ በመደቆስ፣ በመገፋት ውሥጥ እሮሮ የኳተረው አቅም ሆኖ ቀስ በቀስ ተመልሶ ለመምጣት “የጠላት ያለህ!” እያለ ይቦጭርሃል! ስለዚህ ወዳጄ እስከመጨረሻው ዝምብለህ ልታካትማቸው ከፈለግክ በፍጹም በፍጹም እትንካቸው፣ የመበደልን ጉልበት አትስጣቸው! ብቻ ይዘውህ እንዳይሞቱ ራስህን ከቻልክ ከጦስ ዶሮነት አግልል፣ ካልቻልክ ራስህን ተከላከል! ከዚያ ያለፈ ዝምምምምም በላቸው! ያኔ ልጆቻችን በተረት ተረት አሊያም ታሪክ መጽሀፍ ላይ ያውቋቸዋል። እነሱም የማይቀረውን ተፈጥሯዊ ሞታቸውን ከብዙ መንፈራፈር በኋላ ይሞታሉ። ያኔ የሮም ታሪክ ራሱን ይደግማል! ደወልና ደዋዩ ብቻ ይቀሩና ታርፋለህ!! እናም አትንካቸው! አጀንዳም አታድርጋቸው! ረስተሃቸው ዝምምም ብለህ በራስህ ላይ ሥራ!!
@ychanut
868 viewsሀሺም (ለማኖር እኖራለሁ!!), 12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 11:59:47 እኛ እንደናንተ ጨካኝ አይደለንም ሴትና ህፃናትን አናጠቃም፣ እንደናንተ ኃላ ቀር አይደለንም የእምነት ተቋም አናቃጥልም፣
እንደናንተ ሌባ አይደለንም የሰው ንብረት አንዘርፍም፣ እንደናንተ ፈሪ አይደለንም ባዶ እጁን ለቀብር የወጣን በጥይትና ቦንብ
አናጠቃም። ግን ደግሞ የደረሰብን ሳናወራርድ የምናልፍም አይደለንም። ወረበል ካዕባ እንደ ወንድ ፊት ለፊት የምንገናኝበት
ቀን ይመጣል። እንደ አፄ ቴዎድሮስ በድንጋጤ ጥይት ጠጥታቹ እንኳ አታመልጡንም። እያንዳንዱን ቆጥረን እናወራርዳለን።
@ychanut
956 viewsሀሺም (ለማኖር እኖራለሁ!!), 08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-07 14:53:08 ... « ዒሽሩነ ሷቢሩን…» መሆንና መፅናት ብቻ ነው መፍትሄው!

... ሲጥ ትላለህ እንጂ እኔ እንደሆነ ከትምህርት ገበታዬ አልቀርም በላቸው። እንደ ትናንቱም እንደው ልማርና ወደፊት ልቀይር ብዬ አልለማመጥም። በሀይማኖቴና በእኔነቴ የምትደራደረኝ ሀገር የለችኝም።

ይህችን ሀገር በጋራ እሴታችን ተዋደን፣ የግል እሴቶቻችንን ተማምነንና ተከባብረን እንሰራታለን እንጂ ሁለተኛ አማራጭ የለንም። በቀረፅከው ፓሊሲ ስር አጎንብሰን አናልፍም። የጋራ ፓሊሲያችንን ተማምነን እንቀርፃለን። አራት ነጥብ

የነገ ተስፋዎቼ! ፍፁም መንፈሳዊ ለመሆን ጣሩ፤ አድምታችሁ ተማሩ፤ ለሀገር ብልፅግና ዋልታ ትሆኑ ዘንድ ትጉ። ትናንት እኔ ያየሁትን ግን ፈፅሞ አታስተናግዱም። የሚከፈለውን ሁሉ እከፍላለሁ።

"በእኔነቴና በእምነቴ የማታከብረኝ ሀገርም ሆነ ስርኣት የለችኝም፣ አትኖረኝም!" ኢንሻአላህ ሊተህቂቅ!

Dr. Semhar Tekle
@ychanut
1.3K viewsሀሺም (ለማኖር እኖራለሁ!!), 11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 18:40:02 በበርካታ ቦታዎች የረመዳን ወር
መግቢያ ጨረቃ በመታየቷ
የሻዕባን ወር በዛሬው ዕለት
ጁምዓ ተጠናቆ ነገ ቅዳሜ
መጋቢት 24 (April 2) የረመዳን
ወር 1 ብሎ እንደሚጀመር
ታውቋል፡፡
እንኳን ለታላቁ የረመዳን ወር
በሰላም አደረሰን
ረመዳን ሙባረክ!
@ychanut
1.0K viewsሀሺም (ለማኖር እኖራለሁ!!), 15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 18:07:52 የሽዕባን ወር የመጨረሻው ጁምዓ ፀሐይ እየጠለቀች ነው።
አላህ ይህን የወር የረመዷን ወር ሰላሙ የበዛ፣ በኢማን
የተዋበ፣ በበረከት የተሞላ አድርግልን። የለውጥ እና
የምንሻሻልበት ወር አድርገው።
ረመዷን ሆይ እንኳን መጣህልን።
ደጋግሜ እንኳን አደረሳችሁ ብል እንኳን ዉስጤ አይረካም።
@ychanut
952 viewsሀሺም (ለማኖር እኖራለሁ!!), 15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 15:38:45 አዋጅ
ከሰማያት ራህመት ሊዘንብ፣ ምድር በበረካ ቡቃያ ሊያብብ፣ የወየበ ልብ በምህረት ጅረት ሊታጠብ፣ የሙዕሚኖች ልብ በሀሴት ሊቦርቅ፣ ሰዓታት ቀሩ
አቦ ራህመቱ ከደጅህ የሚፈስበት፣ ጓዳህ በፍቅር፣ ሳሎንህ በበረካ የሚያብብበት፣ ማንነትህ ለአላህ ፍቅር ልብህ ለረሱል ናፍቆት የሚንዘፈዘፍበት ረመዷን ይሁን… በዛ ላይ ዛሬ ጁሙዓ በዱአ ሰሉ አላ ረሱሉልላህ
@ychanut
870 viewsሀሺም (ለማኖር እኖራለሁ!!), 12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ