Get Mystery Box with random crypto!

የጋምቤላ በርካታ ክፍል በኦነግ ሸኔ እጅ ወድቋል! ************************* ህግ እ | Yalelet Wondye Gebeyehu

የጋምቤላ በርካታ ክፍል በኦነግ ሸኔ እጅ ወድቋል!
*************************
ህግ እናስከብራለን ይላሉ። ጋምቤላ ግን ብዙ ክፍል በኦነግ ሸኔ እጅ ወድቋል። የክልሉ መንግስት እንዳመነው ኦነግ የባለሀብቶችን እርሻ ወርሶ ይዟል። ሀብታቸውን ዘርፏል። ጭራሽ ልማት ባንክ ባለሀብቶቹን የተበደራችሁትን አምጡ እያለ ነው። ሀብታቸው በአሸባሪ እጅ እንዳይወድቅ ጥበቃ ማድረግ የነበረበት መንግስት ነው። መንግስት ግዴታውን ሳይወጣ ቀርቶም፣ ባንኮች ኦነግ የወረሰውን ሀብት መልሳችሁ አምጡ ይሏቸዋል።


በአሁኑ ወቅት ጋምቤላ ላይ በኦነግ እጅ የወደቀውን መሬት የሚያርሱት ኦነግና ትህነግን የሚያግዙ የትህነግ ባለሀብቶች ናቸው። እነዚህ ባለሀብቶች አልተወረሱትም። ኦነግን ይቀልባሉ። የኦነግን መልዕክት ወደ አዲስ አበባ መጥተው ለትህነግ ወኪሎች ያደርሳሉ። የትህነግን እቅድ ለኦነግ አድርሰው ያስፈፅማሉ።