Get Mystery Box with random crypto!

ህወትሃት በአማራ ክልል ያደረሰው የውድመት ጠቅላላ ጥናት ይፋ ሆኗል! ****** አምስት ወራት በፈ | Yalelet Wondye Gebeyehu

ህወትሃት በአማራ ክልል ያደረሰው የውድመት ጠቅላላ ጥናት ይፋ ሆኗል!
******
አምስት ወራት በፈጀው በዚህ የጉዳት መጠን ጥናት ይፋ እንደተደረገው አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች በጦርነቱ ተሳትፎ ያልነበረቸውን 7 ሺህ የሚጠጉ ንፁሃንን በጅምላ መረሸኑን ጥናት አመለከተ።

በአማራ ክልል ወረራ በፈጸመበት ወቅት 288 ቢሊዮን 16 ሚሊየን 448 ሺህ 452 ብር ግምት ያለው ቁሳዊ ጉዳት ማድረሱን ነው ጥናቱ ያመለከተው።

የአሸባሪው ቡድን ታጣቂዎች 1 ሺህ 782 የአስገድዶ መድፈር ጥቃት መፈጸማቸውን የገለጸው የጥናቱ ውጤት፤ በቡድን በመሆን በቤተሰብ አባላት ፊት አስገድዶ የመድፈር ድርጊት በመፈጸም አሰቃቂ ጉዳት ማድረሳቸው ተገልጿል።