Get Mystery Box with random crypto!

ባለፉት አምስት ዓመታት 40 ሺሕ የሚደርሱ የአማራ ተወላጆች ተገድለዋል ተባለ ። በኢትዮጵያ ባለፉ | Yalelet Wondye

ባለፉት አምስት ዓመታት 40 ሺሕ የሚደርሱ የአማራ ተወላጆች ተገድለዋል ተባለ ።

በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት 40ሺ የሚጠጉ የአማራ ተወላጆች መገደላቸዉን ካዉንተር ፐንች በድረገፁ ላይ አስነብቧል።

ግርሃም ፒቤልስ << Crushing freedom creating fear>> በሚል ርዕስ በድረገፁ ላይ ባወጣዉ ሰፊ ሀተታ

በ2010 ዓ/ም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ ህዝቡ ትልቅ ተስፋን ሰንቆ ነበር ያለዉ ፅሁፉ በጊዜ ሂደት የታዩት ተስፋዎች ተሟጠዉ የአገዛዙ እውነተኛ ቀለሞች በግልፅ መታየት መጀመራቸዉን ገልጿል።

በእነዚህ አምስት ዓመታትም ከ25,000 እስከ 40,000 የሚጠጉ የአማራ ብሄር ተወላጆች በኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን መገደላቸዉንም በድረገፁ ላይ ሰፍሯል እንዲሁም በሀገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣዉ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ድረገፁ ይፋ አድርጓል።

ዘገባው መሰረቱን በአሜሪካ ያደረገ “ፍሪደም ሃውስ” የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅትን መረጃ ጠቅሶ፤ በተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ፣ በጋዜጠኞች እና በሚዲያ አካላት ላይ የሚደርሰዉ አፈናና ክትትል መቀጠሉ ያስነበበ ሲሆን በተለይ መንግስትን ሚቃወሙ እና የሚተቹ አካላት ላይ በደህንነት አካላት ጭምር ክትትል እንደሚደረግባቸዉ እና በእነዚህ ሀይሎች ተይዘዉ ወዳልታወቀ ቦታ እንደሚወሰዱም ድረገፁ ይፋ አድርጓል።