Get Mystery Box with random crypto!

ካሴናዉ ጎጃም [ቅምሻ] 'እናትዋ ጎንደር' ብሎ ዉቡን የጎንደር ህዝብ ጥንታዊ አኗኗር፣ ባ | Yalelet Wondye

ካሴናዉ ጎጃም
[ቅምሻ]

"እናትዋ ጎንደር" ብሎ ዉቡን የጎንደር ህዝብ ጥንታዊ አኗኗር፣ ባህል እና ሰዉ ወዳድነት በድምፁ ያስረቀረቀዉ ድምፃዊ።

ካሲናዉ ጎጃም የሚል ቅኔ ያዘለ ህዝብን የሚገልፅ ሙዚቃ ሊለቅ እንደሆነ አቀንቃኙ Aschalew Fetene Ardi እና አዘጋጁ Sewmehon Yismaw አስታዉቀዋል።


የፍጥረት ጅምር
የአፍላጋት መፍለቂያ
የዮቶር ሞገድ፤
ካሲናው ጎጃም ነው
ምድሪቱ ምጣድ።
ካሲናው (እንጎቻው) ጎጃም


ካሲና በጤፍ በተፍረፈረፈዉ የጎጃም ምድር እንጀራ ሲጋገር መጀመሪያ ከምጣዱ የሚወጣዉ እንጀራ ነዉ። ካሲናዉ ቀደምትነትን እና የመጀመሪያነትን የሚገልፅ ነዉ።
ይህ እንጀራ በጎጃም ጓዳዎች የተወደደ እና የተለመደ ነዉ። በበረት ከሚያረቧቸዉ ላሞች የሚገኘዉን እርጎ እና ቅቤ በቃተኛ መልክ እንጀራዉ ሲጋገር በቤቱ ላሉ በሙሉ ካሲናዉ ላይ ተደርጎ ይታደላል።

የጎጃም ህዝብ ማሩን ቂቤዉን፣ ጠላዉን ጠጁን፣ አንጀራዉን ዳቦዉን፣ አይቡን እርጎዉን ብሉልኝ ጠጡልኝ የሚል ሰዉ በልቶ የጠገበ የማይመስለዉ በግብርና የተመሰረተ ግብርናዉ ደግሞ መልሶ የሚከፍለዉ ለህዝብ እና ለአርበኛ ደጀን የሆነ ህዝብ ነዉ።

የጎጃም ምድር ከኤደን ፈልቆ ገነትን ያጠጣል ተብሎ በእግዚአብሔር ቃል ከተነገረለት ዘላለማዊዉ የሚስጥር አምድ ፈለገ ግዮን ወንዝ እስከ የዘሩበትን ሁሉ ፍሬ የሚሰጠዉ ዉብ መልከዓ ምድሩ....

ከዓባይ ምንጭ ሸለቆና ድልድዮቹ ፣ጮቄ ተራሮች
እስከ ዘንገና ሐይቅ፣ ጢስ ዓባይ ፏፏቴዎችና ጣና ሐይቅ ደሴቶቹ እና በሌሎቹም የታደለዉ የተፈጥሮ ሀብቶቹ።

እስኪ በስማም ብየ ልጀምር ምስጋና
ኮስትርን የሚያክል ምን ወንድ ተገኘና?
ተብሎ ስለተገጠመለት የለምጨኑ አምበሳ የፊላዉ ንጉስ ፣ጣሊያንን አንበርካኪዉ አርበኛ በላይ ዘለቀን ጨምሮ
አገሩ ጎጃም ያውም ዳሞቴ
በልጅጉም ይላል ያዘኝ በሞቴ
አንበሳው ሃይሌ አንዴ ቢነሳ
ነጩን አሳማ አረገው ምሳ!

ገና እየመጣ ነው ሲባል የፋሽሽቱ ጀሌ በፍርሃት ፈርጥጦ ገደል እየገባ አለቀ ተብሎ በአባቶች የተነገረለት ደጃዝማች ሃይለየሱስ ፍላቴ የደጋ የዳሞቱ እንቆቆ።

አርበኛ በላይ ዘለቀ እና ደጃዝማች ሃይለየሱስ ፍላቴ ለነፃነት ተጋድሎ የጎጃምን አርበኛ እየመሩ ሃገር ነፃ ካወጡት ጀግና አርበኞች መካከል ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው። ሌሎችም ጀግኖች እንዳሉ ሁነዉ።

ከእዉቁ ሀዲስ አለማየሁ እስከ ቀኝጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ በብዕራቸዉ አንቱታነትን ያተረፉ እልፍ አእላፍ ጥበበኞችን የያዘዉ ምድር ነዉ።

ጎጃም በማወደስ በላይ ዘለቀን በመዘከር የሚደምቀዉ የጎጃም ዘፈን እና ተዉኔት።
ነፍሱን ይማረዉ እና ማዲንጎ አፈወርቅ
ኤፍሬም ታምሩ
ቴዎድሮስ ካሳሁን
ንዋይ ደበበ
ዳኜ ዋለ የመሳሰሉት እዉቅ ድምፃዊያን ባህሉን እና ህዝቡን በሙዚቃቸዉ አወድሰዋል።

ለእኔ የምንጊዜም ምርጡ የንዋይ ደበበ [የበላይ ነኝ] የሚለዉ ሙዚቃ ቢሆንም ሁሉንም እወዳቸዋለሁ።

በመጨረሻም ከካሲናዉ ጎጃም ሙዚቃ በኋላ ምስክርነት የምንሰጥ ቢሆንም ለቅምሻ ይህን ብለናል።

በ Estifanos Mulu ተፃፈ!